በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኘው የኩዩ ቀበሌ ግማሽ ያህል ነዋሪዎቿ አይነ ስውር የመሆን አደጋ የተጋረጠባቸው ናቸው ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ በዚሁ መንደር በሚገኘው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪ የሆኑ ህጻናት በቤተሰባቸው ውስጥ የዓይን ችግር ያለበት ሰው እንዳለ ሲጠየቁ 20 ያህል ህጻናት እጃቸውን ያወጣሉ ይላል ዘገባው፡፡
የዚህ ሁሉ መነሾው ደግሞ ትራኮማ ነው፡፡ ቢበዛ በ10 ደቂቃ የቀዶ ጥገና ህክምና ሊፈወስ የሚችለው ትራኮማ አንዳንዶች የድህነት በሽታ ይሉታል፡፡ በዓለማችን 2.2 ሚሊየን ህዝብ በትራኮማ ምክንያት የዓይን ብርሃኑን ያጣ ሲሆን በኢትዮጵያ ትራኮማ እጅጉን የተስፋፋው በኦሮሚያ ክልል እንደሆነ ይታወቃል፡፡
10 ደቂቃ የማይሞላውን ቀላል የቀዶ ጥገና ህክምና ካላገኙ 200 000 ያህል የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ የሚለው ዘገባ…ዓለምን በ2020 ከትራኮማ ነጻ ለማድረግ ያቀደው የብሪታኒያ የምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ጥምረት በኦሮሚያ ክልል እያካሄዱ ያሉትን የቀዶ ጥገና ህክምናና የባለሞያዎች ስልጠና ቢቢሲ በድረ ገጹ ዘግቦታል፡፡
ከቀዶ ጥገናው በኋላ እድን ይሆን በሚል ትዕግስት ማጣት እንቅልፍ አጥታ ያደረችው የ40 ዓመቷ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዋ ምስራቅ፣ እሽጉ ተነስቶላት ማየት ስትችል…“እንደገና የተወለድኩ ያህል ነው የተሰማኝ…” ትላለች፡፡
በዘገባው ላይ ባይገለጽም ለኦሮሚያ ጥቅም ቆመናል የሚሉ በፓርቲም፣ በነጻ አውጪም ሆነ በግለሰብ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ከሚያባክኑት ጊዜና ገንዘብ በጣም ጥቂቱን በዚህ ላይ ለማዋል ቢሞክሩና የሕዝባቸውን ስቃይ ለመታደግ ቢሠሩ በማለት በርካታ አስተያየት ሰጪዎች ለዝግጅት ክፍላችን በፌስቡክ በኩል በላኩት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ: BBC Report
ezra says
ጃዋር ሞሐመድ “ሜንጫዉን”ለመሳል ከሚያወጣው ገንዘብ ይልቅ ምነው ለእነዚህ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ዓይነ ብርሃናቸዉን እንዳያጡ መታደግ ላይ ጊዜ ቢኖረው?