ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁሉም የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎችና የፖለቲካ አካላት ለሰላም ንግግር ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ያቀረቡት ግልጽ ደብዳቤ፣ በሱዳን አስከፊ ጦርነት ዙሪያ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ምኅዳር በአዲስ መልክ አነቃቅቶታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጥታ ለሱዳን ሕዝብ ጥሪ ማቅረባቸው በጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ወታደራዊ መንግሥት ላይ ዲፕሎማሲያዊ ሽብልቅ ሆኖ አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተታቸው እየተነገረ ነው። በዓረብኛ ቋንቋ ተጽፎ ለሱዳን ሕዝብ የቀረበው ይህ ደብዳቤ፣ የሁለቱን ሕዝብ የቆየ ታሪካዊ ትሥሥር እንዲሁም “ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ” የሚለውን መርህ አጉልቶ አሳይቷል። እዚህ ላይ ትልቁ ነጥብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ራሳቸውን የንግግሩ አሸማጋይ አድርገው አለማቅረባቸው ነው። ይልቁንም የኢትዮጵያ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባን እንደ ገለልተኛ የመወያያ … [Read more...] about የዲፕሎማሲ ሽብልቅ ሆኖ አልቡርሃንን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የጠ/ሚ/ር ዐቢይ የሰላም ጥሪ

