• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!

April 23, 2014 10:26 pm by Editor 1 Comment

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ብትሆንም ቅሉ በተከታታይ ስልጣኑን የጨበጡት ጭፍን አንባገነኖች በሚያራምዱት አግላይ ምሁር ፖሊሲ ምክንያት እውቀታችሁን እና ገንዘባችሁን በምትወዷት ሀገራችሁ ኢንቨስት አድታደርጉ ሁኔታዎች ባለመመቻቸታቸው የስደትን መራራ ጽዋ እንድትጨልጡ ተገዳችኋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለይ ባለፉት 10 አመታት በተቃዋሚዎች መዳከም የሚያታግል ኃይል አጥታችሁ እንደቆያችሁም እናምናለን፡፡

ፓርቲያችን ሰማያዊ እያንዳንዱ ዲያስፖራ ሀገር ቤት ያለውን ዜጋ ያክል የኢትዮጵያዊነት መብት አለው ብሎ ያምናል፡፡ ይህ ይረጋገጥ ዘንድም አጥብቆ ይታገላል፡፡ በተለያየ ሁኔታና ወቅት አንባገነኖችን በሀገር ውስጥ እንደታገላችሁ እናምናለን፡፡ ለዚህ ትግላችሁና ለከፈላችሁት ዋጋም እውቅና እንሰጣለን፡፡ በስርዓቶቹ ጨካኝ ዱላ እና ሰቆቃ ብዛት ውድ ሀገራችሁን ትታችሁ የሥደትን ኑሮ ትገፉ ዘንድ ቢበየንባችሁም ስለ ኢትዮጵያ ከመብሰልሰል እንዳልዳናችሁና ሀሳባችሁ ሀገር ቤት ስለ መሆኑ መስካሪ አያሻም፡፡

ውድ የሀገራችን ልጆች እናንተ የሰው ሀገር በምታለሙበት በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ኢትዮጵያ የጉልበት ሰራተኛ ሳይቀር ከቻይናና ከህንድ በከፍተኛ ክፍያ እያስመጣች ትገኛለች፡፡ ይህ ደግሞ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ስለ መሆኑ ለእናንተ መንገር ለቀባሪ እንደ ማርዳት ያለ ነው፡፡ ይህ በእውነት ለአንድ ሀገር ወዳድ ዜጋ እንደ እግር እሳት ያንገበግባል፡፡ ልማታዊ መንግስት ነኝ በሚል የቃላት ጋጋታ ብቻ ከድሃው ወገናችሁ በሚሰበስበው ገንዘብ የሰከረው ጉልበታም መንግስት ዴሞክራሲና ልማት አንድ ላይ አብረው አይሄዱም በሚል ማሳሳቻ በየ ጊዜው ጉልበቱን እያፈረጠመ የሄደው በአብዛኛው እናንተ ከምትኖሩበት ከምዕራባውያን ሀገራት በሚቀበለው እርዳታ መሆኑ ሀቅ ነው፡፡

ዳያስፖራው በነጻነት መኖር ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ያውቀዋል፡፡ ነጻ ሆኖ መስራት ለሀገር ልማት ግንባታ ያለውን ጠቀሜታም ሀገር ቤት ካለው ህዝብ በተሻለ ሁኔታ ይገነዘባል፡፡ ድህነትና አንባገነንነት ባመጣው ጦስ ኢትዮጵያዊ ክብራችን ተገፎ በየ በረሃው ዜጎቻችን እንደ እንስሳት ሲታረዱ፣ እህቶቻንን በቡድን ሲደፈሩ፣ ወገኖቻችን ልብና ኩላሊታቸው ወጥቶ ለገበያ ሲውል እንደማየት ያለ ዘግናኝ ተግባር ምን አለ?!! ይህ ህገ ወጥ ተግባር ሊፈጸምባቸው አይገባም ብላችሁ ያሳያችሁት ለወገን መቆርቆር ይበል የሚያስብልና ሊበረታታ የሚገባው ነው ብለን እናምናለን፡፡

በተለይ የሳውዲ መንግስት በዜጎቻችን ላይ የወሰደባቸውን ህገ ወጥ ተግባር ለማውገዝ ያደረጋችሁትን ርብርብና ለሀገራችን በአንድ ሆ ብላችሁ መቆማችንሁን በድጋሚ እያመሰገንን አንባገነኑን ኢህአዴግ ለመታገል በሚደረገው ትግል አጋራነታችሁን ስለምንገነዘብ ከጎናችን በመሆን ለምታሳዩት ውጣ ውረድ እውቅና እንሰጣለን፡፡ ከዚህ በፊት ያሳያችሁትን የትግል ቁርጠኝነት እንደምትደግሙት በማመን ያላችሁን የገንዘብ አቅም፣ የእውቀትና የተሰሚነት ሚና በመጠቀም የአንባገነኑን ስርዓት አፈና በማጋለጥ ከጎናችን እንድትሰለፉ ስንል እንጠይቃለን፡፡ ዳያስፖራው ያለውን የኢኮኖሚ ነጻነት፣ የሚዲያ ነጻነትና፣ ሀገር ቤት ካለው ጋር ሲነጻጸር ያለው የለሻለ የትምህርት ደረጃና ልምድ፣ እንዲሁም በእርዳታ ሰጭ ሀገራት ያለው የተሰሚነት አቅም ተጠቅሞ ሀገር ቤት ያለውን ትግል በማገዝ ነጻ የምንወጣበትን ቀን ሊያፋጥን እንደሚገባ ፓርቲያችን ያምናል፡፡

ፓርቲያችን የህግ የበላይነትን ለማስፈን ሁሉንም የሀገሪቱን ዜጋ ያሳተፈ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ዘርፈ ብዙ ትግል ውስጥ ደግሞ ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልስ›› በሚል መሪ ቃል ታላቅና ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም ይህን ሁሉን አቀፍ የሆነ ሰላማዊ ትግል በሞራል፣ በእውቀትና በምክር፣ እንዲሁም በገንዘብ በማገዝ የትግሉ አጋር ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡

ከአገራችሁ እርቃችሁ የምትኖሩ በመሆናችሁ አዲስ አበባ ውስጥ አብራችሁን ባትቀሰቅሱ፣ ሰላማዊ ሰልፍ ባትወጡና ባትታሰሩም መረጃውን ለዓለም ህዝብ በማድረስ ከፍተኛ ሚና እየተጫወታችሁ ቆይታችኋል፡፡ በዚህ ሰልፍም አገር ቤት ለሚኖሩ ቤተሰብ፣ ጓደኛ እንዲሁም ሌላው ህዝብ በስልክ፣ በማህበራዊ ድህረ ገጽና የተለያዩ መልዕክት ማስተላለፊያዎች በመጠቀም ህዝቡን የማነቃቃት አቅምና አጋጣሚ ተጠቅማችሁ በትግል ጉዟችን ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ኑ ራሳችንን ነጻ በማውጣት የአገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. እስከመቼ says

    April 24, 2014 08:21 am at 8:21 am

    ለሰማያዊ ፓርቲ፤
    ጥሪያችሁ ድንቅ ነው። የበለጠ ጥሩ የሚሆነው ደግሞ፤ ትክክለኛ የሆነ ግንዛቤ ከሀገር ውጪም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለውን የትግል ምንነት ስታሳይኡ ነው። ዋናው ትግል በሀገር ውስጥ ነው። ታጋዩ ደግሞ ሀገር ውስጥ ነው። የትግሉ ምንነት ደግሞ፤ የወራሪ ጉልበተኛ ወገንተኛ አምባገነን መንግሥት ባንድ በኩል፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በሌላ በኩል የሆነበት ሀቅ ነው። ታዲያ ለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት መነሳት አለበት። በድርጅቶች መካከል ውድድር መኖሩ፤ ለጠላት መሰንበት ያመቻል እንጂ፤ ትግሉን ወደፊት በመግፋት በኩል ፋይዳ የለውም። ለምን በታጋዩ ክፍል ያላችሁትአንድነት ሆናችሁ አትጠሩንም? በአንድነት ከተሰለፋችሁ፤ ሕዝቡም ተስፋው ይሰፋና ቀድሟችሁ ይሠለፋል፤ እኛም ከጎናችሁ ልንቆም እንሯሯጣለን። ትግሉ በድርጅቶች መካከል አይደለም። “እኔን ውደዱ” “የለም እኔ እሻላለሁ” የምትባባሉበት ሰዓት አይደለም። ይኼንን ለማድረግ ህዝቡ ገና አልታደለም። አሁን የነፃነት ጥያቄ ነው። በጣም መሠረታዊ በሆኑ አራት አጥቦች ዙሪይ፤ እንቅስቃሴውን ልትመሩት ትችላላችሁ፤
    ፩ኛ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብን ሉዓላዊነት መቀበል ( የሕዝቡን የበላይነት )
    ፪ኛ፤ የሀገራችን የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነት መቀበል ( ዳር ድንበሯንና ለም መሬቷን ጭምር )
    ፫ኛ፤ የሕግ የበላይነትን መቀበል ( ማንም አካል ከሕግ በላይ መሆን እንደሌለበት )
    ፬ኛ፤ የያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ መታገል።
    እነኚህ በሁላችሁም ድርጅቶች መርኀ-ግብሮች የተዘረዘሩና በየመግለጫችሁም ተደጋግመው የተሰጡ ናቸው። የአሁኑ ሰዓት ትግል ደግሞ ይህ ነው። ታዲያ ውድድሩን ትታችሁ፤ በነዚህ ነጥቦች ዙሪያ ተሰባሰቡና ለአንድ ሀገር አንድ ትግል አድርጉና እኛ ድርሻችንን ባንወጣ ተወቃሾች እንሁን። በርግጥ እኔ ይኼንን ስል ማንንም ወክዬ አይደለም። ራሴን ብቻ ነው የምወክለው። እኔን የመሰሉ አይጠፉም የሚል እምነት ግን አለኝ።
    ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።
    ትግሉ ወገን የማትረፍና ሀገር የማዳን ነው።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule