ሕዝባዊ ንቅናቄው ከተቀጣጠለ አነሆ አመት አየተጠጋ ነው። በተለይም በጉልህ የኦሮሞ ሞቭመንት አና የአማራው ሞቭመንት በመባል የሚታወቁት ሁለቱ ንቅናቄዎች ሚሊዮኖችን ያሳተፈ በመሆኑ ሕዝባዊነቱ ሌላ ማረጋገጫ አያስፈልገውም። ወያኔ ኢሕአዴግ በሕዝባዊ ንቅናቄና በፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ መካከል ያለው ልዩነትና ዝምድና ከባህርዩ የተነሳ ሊገነዘብ ባለመቻሉ ሕዝባዊ ንቅናቄውን የጥቂት ፖለቲከኞች ወይም ጸረ ሰላም ሃይሎች አድርጎ በመቁጠር በተለመደ ጥቂቶችን የማጥፋት የጉልበት ስልቱ ሕዝባዊ ንቅናቄውንም ለማዳፈን ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ይህም እኩይ ተግባሩ በየቀኑ ከሕዝብ አየነጠለው እነሆ አሁን ጠመንጃውን የሚያዙ ጥቂቶች አየተንገዋለሉ ይገኛሉ። በቲዎሪም ሆነ በተግባር ለወያኔ ኢሕአዴግ የሚቀርበው የሌኒን የአብዮት ቲዎሪ አብዮትን ለማምጣት የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች ብሎ የገለጻቸው እንደ ቀድሞ መግዛት አለመቻልና ተገዥውም አነደቀድሞው ለመገዛት ፈቃደኛ አለመሆን የወቅቱ የሃገራችን ሁኔታ መገለጫ ነው። ሌሎች ሁኔታዎች ማለትም በተለይ ህወሃት ኢሕአዴግ በራሱ ሊያመጣ የሚችለው ስር ነቀል ለውጥ አስከሌለ ድረስ አብዮቱ መምጣቱ አይቀርም የሚመጣው አብዮት ደግሞ የአረብ አብዮት ቢጫ፣ ብርቱካን፣ ሰማያዊ አብዮት አያለ ስራቱ የሕዝብን አንቅስቃሴ መገለጫዎችን የሚቀልድባቸው አይነቶች ሳይሆን ኢትዮጵያዊ አብዮት እንዲሆን የፖለቲካ ድርጅቶችና አክቲቪስቶች ከወዲሁ ሊያደርጉዋቸው የሚገቡ ተግባራት አንዳሉ ሁኔታዎች አያስገደዱ ናቸው ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
ጸሃፊውን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይቻላል: shimelisw@yahoo.com
Leave a Reply