• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን (አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን)”

February 24, 2015 05:28 am by Editor Leave a Comment

በተለያየ ጊዜ በተለያየ የክህደት አስተምህሮ በመሰናከል በመውደቅ ከዚህች ሐዋርያዊት አንዲት ቤተክርስቲያ እየተለዩ በኑፋቄያዊ አስተምህሮ ጸንተው በመቀጠል ለዚህች አንዲት ሃይማኖት አንዲት ቤተክርስቲያን ጠላቶች የሆኑ ዲያብሎስን የሚያገለግሉ ከ40 ሽህ በላይ ይቆጠራሉ፡፡ ሃይማኖት ነንም ይላሉ፡፡ ክርስቶስ በወንጌሉ ሐዋርያትም በመልእክቶቻቸው እንደተናገሩት ግን ከአንዲቷ በስተቀር ይሄ ሁሉ ሃይማኖት ነኝ ባይ ዝግንትል ሐሰተኛና ዲያብሎሳዊ የክህደትና የጥፋት መንገዶች ናቸው፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ ሲቃረብ ብዙዎች ሐሰተኞች መምህራን በየ እልፍኙ የሚሰብኩላቸው ሐሰተኞች ኢየሱሶች ሐሰተኞች ክርስቶሶች ይመጡ ዘንድ እንዳላቸውና ከእነሱም እንድንጠበቅ አስጠንቅቆናል፡፡ ማቴ. 24፤1-28 “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ. 4፤5 “መንፈስ ግን በግልጥ በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንት ትምህርት እያዳመጡ ሃይማኖትን ይክዳሉ” ብሏል 1ኛ ጢሞ. 4፤1-2 “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም መንገድ ወዴት እንደሆነች ዕወቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች ዕወቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳቹህም ዕረፍትን ታገኛላቹህ እነሱ ግን አንሄድባትም አሉ” ኤር. 6፤16 “የመጀመሪያዋን እምነት እስከመጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና” ዕብ. 3፤14 “ነገር ግን ወንድሞች ሆይ እናንተ የተማራቹህትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና መሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንዳትመለከቱ እለምናቹሀለሁ፡፡ ከእነሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ እንደነዚህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ያታልላሉ” ሮሜ 16፤15-23 “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯቹህን ዋኖቻቹህን አስቡ የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታቹህ በእምነት ምሰሏቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ዘለዓለምም ያው ነው ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፡፡ ልባቹህ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና ” ዕብ. 13፤7-9  “በጠበበው ደጅ ግቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጁ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ወደ ሕይዎት የሚወስደው ደጁ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው” ማቴ. 7፤13-14

ቤተክርስቲያን ካቶሊካዊያኑ በክህደት ውስጥ እንዳሉና ሰሐትያን እንደሆኑ አረጋግጣ አውግዛ የለየቻቸው ገና ከመለየታቸው 451ዓ.ም. ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ካቶሊካዊያኑ ለኢትዮጵያዊው ካቶሊካዊ መነኩሴ ብርሃነ ኢየሱስ በቅርቡ በየካቲት 7 2007ዓ.ም. የካርዲናልነት ማዕረግ ሰጥተዋል፡፡ ይንን ሹመት ተከትሎ አቦይ ማትያስ (የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ነኝ ባይ) የእንኳን ደስ አለዎት የደስታ መግለጫ መልእክትን በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም  “…አሁን የተሰጥዎት ከፍተኛ ሐዋርያዊ ሥልጣን በቤተክርስቲያን ለፈጸሙት የረጅም ዘመን አገልግሎት ሁነኛ ማረጋገጫ ነው” በማለት አስተላልፈዋል፡፡

እንግዲህ ይታያቹህ! አቦይ ማትያስ ይሄንን የሚሉት በካቶሊካዊያኑ ክፉኛ የተደቆሰችን የተሰበረችን መራራና አረማዊ ግፍ የተፈጸመባትን ቤተክርስቲያን እመራለሁ እኔም የዚህች ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና አማኝ ተከታይ ነኝ እያሉና በካቶሊካዊያኑ ላይ ያስተላለፈችውን ግዝት በመተላለፍ ነው ይሄንን እያሉ ያሉት፡፡ ካቶሊካዊያኑ በዚህች ሀገርና ሕዝብ ቁሳዊ መንፈሳዊ ጥበባዊ ሥልጣኔና ሰብአዊ ሀብቶቿ ላይ እስከዛሬ ያልተጠገነ ወደፊትም የማይጠገን ከባድ ስብራትና ኪሳራ ያደረሱ ከንቀታቸው የተነሣም ለዚህ አረመኔያዊ ድርጊታቸውም እስከዛሬ ድረስ ተገቢውን ይቅርታ እንኳን ለመጠየቅ ያልቻሉና ያልፈለጉ መሆናቸውን እያወቁ ነው እንግዲህ አቦይ ማትያስ ይሄንን ያደረጉት፡፡ እንደቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ አስተምህሮ ቀኖናና ሥርዓት አቦይ ማትያስ በግልም ይሁን በቤተክርስቲያን ስም እንዲህ ዓይነት ቃል ከቤተክርስቲያን ለተለዩ ወገኖች ማስተላለፍ አይችሉም የተከለከለና የተወገዘ ነው፡፡ አድርጎት ለተገኘም በግዝት የታሰረና የኑፋቄ የክህደት ተባባሪ በመሆኑ ተወግዞ እስከመለየት የሚያደርስ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እዚህ ላይ አቦይ ማትያስን ልጠይቃቸው የምፈልገው ጉዳይ ቢኖር፡- አቦይ ማትያስ ሆይ! የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምእመናን ከዚህ ንግግርዎ ምን እንዲረዳ ምን እንዲማር ነው ምን እንዲወስድ ነው የሚፈልጉት? እርስዎ እንዳሉት ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሐዋርያ መሆናቸውንና ካቶሊካዊያኑም ሐዋርያዊ መሆናቸውን ነው? እናም እነሱን ተከተሉ ነው እያሉን ያሉት? ምእመናን በረታችንን ጥለን እንድንወጣና ወደ ተኩላት በረት ጥርግ ብለን እንድንገባ ነው? አየ አቦይ ማትያስ! ለካም ወያኔ ብቻ አይደሉም ካቶሊካዊ ተኩላም ነዎትና! ባለ ሁለት አፍ የጥፋት ሰይፍ ሆነው ነዋ የቤተክርስቲያንን አንገት ለመቁረጥ ተስለው የገቡት?

ቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ካላት ሕግና ሥርዓቷን ከማስጠበቅ መንጋዋን ከመጠበቅ አንጻር በዚህ በተፈጸመባት ክህደት የሚጠበቅበትን እርምጃ እንደሚወስድ እንጠብቃለን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule