• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴ ዘረኛውን ቡድን ወደ ተከላካይነት አውርዶታል!

September 20, 2016 10:11 am by Editor Leave a Comment

ትክክለኛ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ ግብ መዳረሻው ጽኑ መሠረቱ እንቅስቃሴው ሕዝቡን ማዕከል ማድረጉና ሁሉንም ወገን አሳታፊ መሆኑ ነው። በዚህ ረገድ በመላው የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶች የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እንቢተኝነት፣የወያኔን የአንድ ለአምስት የስለላ መዋቅር በጣጥሶ፣ ሞትን ፊት ለፊት በማጋፈጥ፣ ገዳዮቹን እየገደለ ለበርካታ ወራት የዘለቀው፣ ሕዝባዊ እንቢተኝነት፣ የዘረኛውን ቡድንና አጋሮቹን ከአጥቂነት ወደ ተከላካይነት እንዲወርዱ አስገድዷቸዋል።

አንድ ገዳይ ቡድን ከአጥቂነት ወደ ተከላካይነት ወረደ ማለት የውስጥ ጥንካሬው መዳከሙን፣ ሚስጢራዊ ሥራው በወንፊት ውኃ መቅዳት መጀመሩን፣ በቡድኑ መካከል አለመግባባት መንገሡን፣ የማስገደጃ ተቋሞቹ ግዳጃቸውን እንደጥንቱ ለመፈጸም ዝግጁና ፈቃደኛ አለመሆናቸውን አመልካች ነው። በዚህ ረገድ የወያኔ የማስገደጃ ተቋሞች እንደጥንቱ የማስገደድ ተግባራቸውን ለመወጣት ከማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን የግዳጅ አፈጻጸማቸው ደረጃ ያሳያል። የአፋኝ ቡድኑ ሚስጥሮች እንደድሮው የተጠበቁ ሳይሆኑ፣ በደቂቃዎች ውስጥ ወደ ማኅበረሰቡ ጆሮ መድረስ በቡድኑ ውስጥ አንጃ መፈጠሩንና ይህ አንጃ ወያኔ በሕዝብ ላይ ጉዳት ሳያደርስ ሕዝቡ አስፈላጊውን መሰናዶ እንዲያደርግ ሹክ የሚል በመሆኑ፣ ወያኔ ሳይወድ በግድ ወደ ተካላካይነት እንዲወርድ አስገድዶታል።

ወያኔ ይህን ተከላካይነቱን በግልጽ ወደ አደባባይ ያወጣው፣«የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም» የሆኑትንና ሆድ አደሮቹን የዐማራው ቀንደኛ ጠላቶች ሽፈራው ሽጉጤንና አዲሱ ለገሠን  ከገጠመው ተቃውሞ መከላከያ ይሆነኛል ብሎ ያሰበውን ከገጠመው ችግር ጋር ምንም ዓይነት ተያያዥነት የሌለውን፣ በወዶ-ገባ የውሻነት ባሕሪያቸው የሚጠበቅባቸውን የቤት አሽከርነት ተግባር እንዲወጡ እንደ ፊኛ ሞልቶ የላካቸውን ክህደትና ቅጥፈት «የትግሬ የበላይነት በየትኛውም መልኩ የለም» በማለት ትግሬዎቹ ቢያንስ ጄኔራል ፃድቃን ያልካደውን በመካድ ወያኔን  ምንጊዜም ከተሸናፊነት ሊያወጣው የማይችለልበትን የመከላከል ተማጽኖ እንዲያሰሙ አድርጓል።

በዚህ የሆድ አደር ተግባሩና በፀረ-ዐማራነቱ የታወቀው ሽፈራው ሽጉጤ በአገሪቱ እንደ  ሐምሌ ማዕበልና እንደቀትር  ሰደድ እሳት ከቦታ ቦታ እየተቀጣጠለ ያለውን ሕዝባዊ እንቢተኝነት የሚመሩትና የሚያቀናብሩት «ትምክህተኞችና ጠባቦች» እንደሆኑ ገልጿል። በሽፈራው ሽጉጤ አጠራር «ትምክህተኛ » ማለት ድሮ ነፍጠኛ የሚሉትና በእርሱ አመራር ከጉራፈርዳ ወረዳ ሀብት ንብረታቸውን ተነጥቀው የተባረሩትን የዐማራውን ነገድ ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው። በሽፈራው አባባል ትምክህተኞች ወያኔን የሚጠሉት«ለዘላለም እንዳይመለሱ ከሥራቸው እንዲመነገሉ ስላደረጋቸው፣ ሥራቸው ሁሉ የጥፋት መሆኑን ስላረጋገጠባቸው ነው» በማለት፣ ዐውቆትም ይሁን ሳያውቀው ወይም የአፍ ወለምታ ሆኖበት፣ የትግሬ ወያኔና አጋሮቹ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጀው፣ የዘር ፍጅት ያደረሱበት መሆኑን ምስክርነቱን ሰጥቷል። ይህ አባባሉ ሳሞራ የኑስ፤ ዐባይ ፀሐየና ሥብሃት ነጋ፣« ዐማራውን አካርካሪውን ሰብረነዋ፣ ዐማራው ላይመለስ ገድለን ቀብረነውል» ሲሉ ከሰጡት ምስክርነት ጋር ተመሳሳይ ነው። እነዚህ ሁለት ሰዎች ወያኔ ከገጠመው  ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ እንቢተኝነት መተንፈሻ እንዲያገኝ ለጊዜው መካላከያ ወረዳ ላይ ሆኖ፣ ለቀናት ዕድሜውን ለማራዘም  የሰጡት ምስክርነት ለኋላው የፍትሕ ሂደት ሁነኛ ማስረጃ ስለሆነ እያንዳንዱ ፍትሕ ፈላጊ ይህን መረጃ ጠብቆ መያዝ እንዳለበት መገንዘብ ተገቢ ነው።

ወያኔ ሞት የረሳቸውንና እርሱም የረሳቸውን ሆድ አደር ባንዶቹን እንዲከላከሉለት መድረክ መስጠቱ ተካላክለው ያድኑኛል ብሎ ሳይሆን፣ አጋሮቹ የቆመበት መሬት በመራዱ የተነሳ ለጊዜውም ቢሆን ከባንዶቹ መካከል ማን ከጎኑ እንደሚቆም ለማወቅና የራሱን ሰዎች ባለቀ ሰዓት ከሕዝብ ዕይታ ውስጥ ላለመጣል አስቦ ያደረገው እንደሆነ ይታመናል። በመሆኑም ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ በነዚህ ዓይነቶቹ ባናዶችና ሆድ አደር ግለሰቦች ላይ ዓይኑን ሊጥል ግድ ይለዋል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ድል ምንጊዜም የሕዝብ ነው!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ማክሰኞ ፲ ቀን ፪ሺህ፱ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፱


በ9/19/2016 በዋሽንግተን ዲሲ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት የተቃውሞ ሕዝባዊ ሰልፍ አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር  ያደረጉት ንግግር፣

  • የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ የእናት ኢትዮጵያ ልጆች!
  • ለወገናችን ድምፅ ለመሆን ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የመጣችሁ ውድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያዊያት!

ይህ የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ፣ የትግሬ ነፃ አውጭ ድርጅትን ዘረኛ አገዛዝ በመቃወም ብቻ የሚገልጽ ሳይሆን፣ የወያኔ ቡድን በልኩ ቀልሶ ካስገባን የጎሣ ጎጆዎች መውጣታችንና ወያኔ የቀማንን ኢትዮጵያዊ ማንነታችንና አንድነታችን መልሰን የተጎናጸፍን መሆንችን ለዓለም ማኅበረሰብ ያሳየንበት ሕዝባዊ ሰልፍ ነው። ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ «ነብር ዝንጉርጉርነቱን፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን» የሚለውጠው የለም ሲል የተገለጸው ቃል ኅያው መሆኑን ማሳያ ነው።

ውድ ወገኖቼ! በዚህ ታሪካዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቼ  የወገኖቻችን ብሦት ለመናገር በመቻሌ  የተሰማኝ ደስታ ታላቅ ነው። ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ላደረጉ በዐማራ፤ በኦሮሞ፣ በጋምቤላ፣በኮንሶ፣ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በአረመኔው የትግሬ ወያኔ አፋኝና ገዳይ ቡድኖች ለተገደሉት ሰማዕታት አጸደ ገነትን ለዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልን እመኛለሁ።

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን!

ዘረኛው የትግሬ ነፃ አውጭ ቡድን በወገኖቻችን ላይ ያደረሰውና እያደረሰው ያለው ግድያ፣ ሥቃይ፣ እስራት፣ እንግልት፣ ግርፋት፣ የኢኮኖሚ ነጠቃ፣ የመብት ገፈፋና የማንነት ረገጣ ሊያቆም ይገባል ብላችሁ ብቻ ሳይሆን፤ ይህ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያን የመሰለች ባለታሪክ፣ የጥቁር ሕዝብ መመኪያና የነፃነት ቀንዲል የሆነች አገር፣ ሊወክልና ሊመራት አይችልም ፣ መወገድ አለበት  ብላችሁ፣ ላገራችሁና ለወገናችሁ ድምፅ ለመሆን ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች መጥታችሁ በዚህ መሰል ኢትዮጵያዊ የአንድነት ስሜት  ድምፃችን ለዓለም ስናሰማ ምናልባች ከቅንጅት እንቅስቃሴ ወዲህ የመጀመሪያው ነው ብል ከዕውነቱ የወጣሁ አይመስለኝም። ይህም በመሆኑ እንዲህ ብየ እንድቆጭ አድርጎኛል። ይህ ድምፃችን፣ ይህ ቁርጠኝነታችን፣ ይህ የአንድነትና ኢትዮጵያዊነት ስሜታችን ከዛሬ 26 ዓመታት በፊት፣

  • ወያኔ የኢትዮጵያነት መገለጫ ከሆኑት አካሎቿ አንዷ የሆነችውን ምድረ ባሕሪን ሲያስገነጥል፣
  • አገራችን ያለመተናፈሻ ዝግ መሬት ሲያደርጋት፣
  • ሕዝቡን በቋንቋ ከፋፍሎ ሆድና ጀርባ የሚያደርግ የዘር ፖለቲካ ሲያራምድ፣
  • በቋንቋ ላይ የተመሠረተ የመንግሥት አደረጃጀት ሲከተል፣
  • በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ነገዶች በቁጥሩ፣በታሪኩ፣ በኢትዮጵያዊነት ስሜቱ ከፍተኛ ከሆኑት አንዱ የሆነውን ዐማራውን በዘር ጠላትነት ፈርጆ፣የኢትዮጵያ ዕጣ ፈናታ ሲወሰን ድምፁን እንዲያሰማ ያልተደረገበት ሕገመንግሥት ሲደነገግ፣
  • የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዐላዊነት ከመጉዳት አልፎ፤ አገራዊ ኅልውናዋን ተፈታታኝ የሆኑ ድርጊቶች ሲፈጸሙ፣
  • አገሪቱ በዘመን ፍሰት የገነባቻቸው የመከላከያ፣ የፖሊስና የደህንነት መዋቅሮች ፈራርሰው በአንድ አናሳ ነገድ ሲተካ፣
  • ዐማራው ኢትዮጵያነቱ ተክዶ በኢትዮጵያ ምድር የመኖር መብቱን ተነጥቆ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ሰለባ ሲሆን፣
  • ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት የቆሙ ግለሰቦችና ቡድኖች፣ጋዜጠኞች፣  የሃይማኖት እና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ ተሰሚነት አላቸው የተባሉ ግለሰቦች ታድነው ሲጨረሱ፤ ወዘተ ወዘተ ይህን የመሰለውን የተባበረ ድምፅ ብናሰማ ኖሮ፣ ዛሬ መርዶ ሰሚዎች ሳንሆን ብሥራት አብሳሪዎች እንሆን ነበር።

ይህ ፀፀት ነው። ፀፀት ግን ምንም ፋይዳ የለውም። ፀፀት ፋይዳ የሚኖረው፣ ከአለፈው ተምረን ለወዲፊቱ ለተሻለ ነገር ለመሥራት ዝግጁ መሆን የሚያስችለን ሲሆን ነው።   በመሆኑም ፈጽሞ ከመቅረት ዘይግይቶም ቢሆን መገኘት የተሻለ ነውና ይህ ዛሬ የምናየው አንድነትና የኢትዮጵያዊነት ስሜት ዳግም ላይቀለበስ በጽናት እንድንቀጥልበት አደራ ለማለት እወዳለሁ።

የወያኔ ጥንካሬ መሠረቱ የእኛ ድክመት ነው። የድክመታችን ምንጩም ከኢትዮጵያነት ማንነታችን ወጥተን፤ ወያኔ ባሰፋልን የነገድ ማንነት ውስጥ መግባታችንና ታላቋን ኢትዮጵያን ማየት አለመቻላችን ነው። ከዛሬ ላይ ሆነን፣ የልጅ ልጆቻችን በሰላምና በአንድነት ሊኖሩባት የምትችል የበለፀገችና የታፈረች ኢትዮጵያን ማየት አለመቻላችን ነው። አንድ የሚያደርጉንን ኢትዮጵያዊ የወል ዕሴቶቻችን አጥፍተን በሚለያዩን፣ነገር ግን ለአንድነታችን መጠንከር ዋስትና በሆኑትና ልናስወግዳቸው  በማንችላቸው የተፈጥሮ ማንነቶቻችን ዙሪያ  የተለየ ትኩረት ሰጥተን፣ እነዚህን ልዩነቶች ማጉላታችን ለወያኔ ጥንካሬ፣ ለእኛ ድክመትና ለአገራችን አጠቃላይ ጥፋት ምቹ መደላድል የሠራን መሆኑ ነው።

ይህ ላለፉት 26 ዓመታት የተጓዝንበት ጉዞ፣ የወያኔን የጭካኔ አገዛዝ ዕድሜ ከማራዘም አልፎ፣ የአገራችን ሕዝብ የመኖር ተስፋ ያጨለመ፣ ሰላሙንና አንድነቱን  ያሳጣ ሆኗል። በዐማራው በኦሮሞው፣ በሶማሌው፣ በሱርማው፣ በአኙዋኩ፣ በኑኤሩ፣ በጉራጌው ወዘተ ላይ የወያኔ ቅልብ የአጋዚ ሠራዊት የሚፈጽመውን የጅምላ ጭፍጨፋና የአፈሳ እስር ከእኛ ከባለቤቶቹ አልፎ የዓለም ማኅበረሰብ በትዝብት እንዲያየው ነው። ወያኔ ዐማራና ኦሮሞውን በገፍ አሥሮ፣ ማሰሪያው ሲጠበው፣ እስር ቤቶችን በእሳት በመለኮስ አያሌ ወገኖቻችን ነደው እንዲያልቁ የሆኑበትን አሳዛኝ ድርጊት ለማየት ተገደናል።  ባለፉት የወያኔ የግፍ አገዛዝ ዘመኖች ከአምስት ሚሊዮን  በላይ ዐማራ በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረገጽ ጠፍቷል። ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም በሚኖሩ ዐማራሮች ላይ በከፈተው የጅምላ ግድያ ከ300 በላይ ንፁሐን ዜጎች ተገድለዋል። ከ16 ሺ በላይ ወጣቶች በአፈሳ ታስረው በአጋዚ ሠራዊት የቁም ሲዖል ውስጥ ይገኛሉ።

ወያኔ  የጎንደርን ፣የቂልጦና የደብረታቦር  እስር ቤቶችን  ሆን ብሎ በማቃጠል፣አያሌ ወንድም እህቶቻችን  አቃጥሎና ለብልቦ የገደላቸውን ሰዎች ስናስታውስ፤ ወያኔ ጥቁሩ ፋሽስት መሆኑን በተግባሩ ያረጋገጠ እንደሆን እንረዳለን። ይህም ወያኔ የሞሶሎኒ ቅኝ ገዥ ኃይል በወገናችን ላይ ከሠራው ግፍ በእጅጉ የከፋና የሠፋ  ግፍ የፈጸመብን  መሆኑን ያላንዳች ጥርጥር እንድንገነዘበው ያስችለናል። ልጇን ገድለው ካስከሬኑ ላይ ተቀምጣ እንድታለቅስ የተደረገበትን ሁኔታ ያየ ሰው፣ ይህ ዓይነት ግፍ በማንና መቼ ተፈጽሞ ይሆን ? ብሎ መጠየቁ አይቀርም። መልሱ ግን ይህን ዓይነት ግፍ በሰው ልጆች ላይ የፈጸመ ወያኔ ብቻ እንደሆነ ሲገነዘብ፣ ወያኔ በትግሬ መጭ ትውልድ ላይ የቱን ያህል የቂም፣ የጥላቻና የመገለል ድግስ  የደገሰለት እንደሆነ ስለሚረዳ፣ ለትግራይ ሕዝብ መፃዒ ዕጣ ፋንታ  ያዝናል። አዎ! የትግራይ ሕዝብ ይህን ተግንዝቦ፣ ሰልፉን ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን አድርጎ የወያኔን የሥልጣን ዕድሜ ለማሳጠር የበኩሉን ሚና ካልተጫወተ፣ የመጭዎቹ ልጆቹ ሕይዎት አሳዛኝ ሊሆን እንደሚችል መናገር ነቢይነትን አይጠይቅም። አባቶቻችንም « ከተራበ ለጠገበ  አዝናለሁ! የሚሉት ጥጋብ ዛሬን እንጂ፣ ነገን ወይም መጭውን አሻግረን እንዳናይ የማድረግ ባሕሪይ ስላለው ነው።

ሚስት የባሏን የወንድነት መለያ አካል በገመድ አስረው እራቁቱን በአደባባይ እንድትጎትተው ያደረገ ወያኔ ነው። ሰዎችን አስሮ በገላቸው ላይ ሽንት ያሸና አረመኔ የትግሬ ወያኔ ነው። ለአገዛዜ አይመቹም ያላቸውን የነቁ ሰዎች አስሮ በማሰቃየት ከነርሱ አልፎ የወጡበትን ነገድ በማንቋሸሽ ነገዱን በጅምላ የሚሳደብና የሚያረክስ ቡድን እስካሁን ለታሪክ ከተመዘገበው ወያኔ ብቻ ነው።

ይህ ዘረኛና ከፋፋይ ቡድን ከኢትዮጵያውያን ጫንቃ ላይ መንጭቆ ማስወገጃው ብቸኛ መንገድ የኢትዮጵያውያን አንድነት ብቻ ነው። የዚህ የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍም ድምቀትና ግዝፈት ምንጩም  ኢትዮጵያዊ አንድነታችን  ነው። ስለሆነም ወያኔን በአፋጣኝ ከጨበጠውና ሙጥኝ ብሎ ከያዘው የሥልጣን ማማ ላይ አስፈንጥሮ መጣያው አስተማማኙ መንገድ የኢትዮጵያውያን አንድነት ነው።

የዐማራውና የኦሮሞ ኅብረትና ወደ ነበረበት ታሪካዊ አንድነት መመለስ ነው። ኦሮሞና ዐማራው አንድ መሆን ቀርቶ፣ አንድ ሊሆኑ ነው የሚለው ድምፅ የወያኔን ቡድን የቱን ያህል የረበሸውና ያሸበረው እንደሆነ፣ ጎንደር ላይ ጀግኖቹ «የኦሮሞው ደም የእኛም ደም ነው»፣ «በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የሚፈጸመው ግፍና ግድያ ያቁም» ሲሉ ያሰሙት ድምፅ፣ ወያኔ ለ26 ዓመታት ሲገነባው የኖረው የልዩነት ግንብ ከመሠረቱ የተናደ መሆኑን ያሳየ ነው። አሁን የእኛ ጥረት የጎንደር ሕዝብ የናደውን የልዩነት ግንብ ወያኔ መልሶ እንዳይገነባው ደብዛውን ማጥፋት እና ኢትዮጵያውያን እንደ ጥንቱ አባቶቻችን እጅ ለእጅ ተያይዘን፤ ትክሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የአገራችን ሰላም በማረጋገጥ ብልጽግናዋን ማፈጠን ወደ ሆነበት አቅጣጫ ለመጓዝ  ቁርጠኝነቱና ዝግጁነቱ  ሊኖረን ይገባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ?

ሞት ለወያኔና ላጫፋሪዎቹ!

አመሰግናለሁ።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule