የተከበርከውና ጀግናው የዐማራ ሕዝብ ሆይ!
የትግሬ ወያኔ አገዛዝ «ዐማራውን አከርካሪውን ሰብረነዋል»፣ «ዐማራው ላይመለስ ገድለን ቀብረነዋል» በማለት ይሳለቅብሃል። በእርግጥም ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ገድሎ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደግሞ አሰድዶ ከመኖሪያ ቀያቸው አፈናቅሏል። ሆኖም ግን ከሞቱት በላይ፣ ካሉት በታች ሆነህ የምትኖረው የቀረኸው ዐማራ፣ ከገባህበት የቁም መቃብር ለመውጣት ዘወትር ትግልህን እንዳላቋረጥክ እኛ አብረንህ የምንታገለው ልጆችህ ቀዳሚ ምሥክሮችህ ነን። በተለይም ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ መግነዝህን ቀደህ እና በጣጥሰህ፣ የተጫነብህን የመቃብር ድንጋይ እና አፈር ፈነቃቅለህ ከፈጽሞ ጥፋት ራስክን ለማዳን እያደረግኸው ላለው ተጋድሎ እና የጀግንነት ተግባር ያለን አድናቆት እና አክብሮት እጅግ ከፍ ያለ ነው። ለምታደርገው ራስክን ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግ ተፈጥሮአዊ የመከላከል ትግል፣ እኛ በስደት የምገኝ ልጆችህ ምንጊዜም ከጎንህ የማንለይ መሆኑን ስናረጋግጥልህ በታላቅ አክብሮት እና ወገናዊነት ነው።
ዛሬ ይህንን ጥሪ እንድናስተላልፍልህ የተገደድነው፣ ጨካኙ፣ አረመኔው እና ፀረ-ዐማራ የሆነው የትግሬ ነፃ አውጪ ወራሪ ቡድን፣ በመላው የዐማራ ሕዝብ ላይ፣ ካለፉት ሁሉ በመጠኑና በስፋቱ የተለየ፣ ይፋ በሆነ ሁኔታ ጦርነት በማወጁ ነው። የጥቁር ናዚው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ በዐማራው ላይ እጅግ መጠነ-ሰፊ የሆነ የዘር ማጥፋት ዘመቻ መክፈቱን፣ በወያኔ ታዞ አዳሪ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ ለወታደሩና ለፀጥታ ኃይሉ ሙሉ የመግደልና የማሰር ሥልጣን መስጠቱን፣ በብዙኃን የመገናኛ መሣሪያዎች ሰምተናል። በዚህም መሠረት፣ የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን ለመጨፍጨፍ፣ እጅግ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ነፍሰ በላ ገዳዮቹን፣ በተለያዩ የትርንስፖርት መንገዶች ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር፣ ደባርቅ፣ ወዘተርፈ በማጓጓዝ ላይ እንደሆነ አውቀናል።
እኛ በስምህ ተደራጅተን፣ በአረመኔው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ እየተፈጸመብህ ያለውን የዘር ጥቃት ለዓለም ማኅበረሰብ በማሰማት ላይ የምንገኝ ልጆችህ፣ የምናቀርብልህ ጥሪ አለን። ይኸውም፥ አንተን በደመኛ ጠላትነት ፈርጀው፣ ፕሮግራም አዘጋጅተው እና ተደራጅተው፣ ላለፉት 41 ዓመታት የዘር ፍጅት ሲፈጽሙብህ የኖሩት የትግሬ-ወያኔዎች ዛሬም የጥፋት በትራቸውን እንዳልሰበሰቡት አንተም አሳምረህ ታውቀዋለህ። እንዲያውም ከሌሎች ነገዶች ያልተቀላቀሉበት፣ የትግሬ-ወያኔ ብቻ የሆኑ ነፍሰ-በላ ገዳዮች፣ የፌድራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት መለዮ ለብሰው፣ አንተን የዋሁን እና ደጉን የዐማራ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ከፍ ሲል በተዘረዘሩት ከተሞች የተሰማሩ መሆናቸውን ዕለት በዕለት የምትመሰክረው ሃቅ ነው። ስለሆነም ሌላ ከውጪ የሚመጣ ደጋፊ ኃይል ሳትጠብቅ፣ ራስክንና ቤተሰብህን ከጥቃቱ መከላከል እንድትችል አስፈላጊውን መሰናዶ ታደርግ ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን። ከታሪክም እንደምንገነዘበው፣ ዐማራው የራሱን እና የአገሩን ጠላቶች ከጓሮው ገብተውለት ቀርቶ፣ ከጉያቸው እየገባ የዶግ አመድ የማድረግ የቆየ የጀግንነት ታሪክ እና ባህል ባለቤት ነው። ስለሆነም ይህን በእብሪት ተወጥሮ፣ ከብብትህ የገባውን የትግሬ-ወያኔ መንጋ፣ በጎበዝ አለቆችህ በመመራት አስፈላጎውን መከላከል በማድረግ፣ ይህን የጣሊያን እንቁላል አቅራቢና አልጋ አንጣፊ የነበሩትን የባንዳ ልጆች ጥርቅም፣ በተለመደው ጀግንነትህ ፍላጎታቸውን የቀን ሕልም እንደምታደርገው እምነታችን ከፍ ያለ ነው።
በአሁኑ ሰዓት፣ አጥፊው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደሴ እና በደብረ ታቦር በሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ አልሞ ተኳሽ ነፍሰ ገዳዮቹን አሰማርቶ ለጅምላ ግድያ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም ነፍሰ በላዎቹ የትግሬ-ወያኔዎች በከተሞች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሚኒባሶች እና የሕዝብ ማመላሻዎች መኪናዎች መትረየስ እና ላውንቸር ጠምደው ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ላንተ መንገር «ለቀባሪው ማርዳት» ይሆንብናል። ስለሆነም፣ አንተ ጀግና እና ኩሩ የሆንከው የዐማራ ሕዝብ፣ ይህ የትግሬ-ወያኔ አጥፍቶህ ከመጥፋቱ በፊት፣ አጥፊውን ኃይል ቀድመህ ለማጥፋት ክንድህን አስተባብረህ ለመብትህና ለነፃነትህ ተዋደቅ። «ከዘላለም ባርነት እና ውርደት የአንድ ቀን ነፃነት» ይመረጣልና፣ አንተም እንደ አባቶችህ፣ ለልጆችህ እና ለልጅ ልጆችህ ኩራትን እና ነፃነትን ለማውረስ በወራሪው እና በዘረኛው ጠላትህ በትግሬ-ወያኔ ላይ የተባበረ ክንድህን አንሳ። «ጅብ ከሚበላህ፣ ጅቡን በልተህ ተቀደስ» ይባላልና፣ አንተን ሊያጠፋ የተፈጥሮ ድንበርክን ተከዜን ተሻግሮ የመጣውን፣ ይህ የሰከረ መርዘኛ እባብ እንዳያመልጥህ በር በሩን ዘግተህ መተናፈሻ በማሳጣት ለትውልዱ የማይረሳ ትምህርት ሰጥተህ እንደምትሸኘው እምነታችን ጽኑ ነው። የትግሬ-ወያኔ ያቀደልህን ሞት እና የዘር ዕልቂት ትውልድህን ከፈጽሞ ጥፋት እንድትታደግ ጥሪያችን ስናቀርብ፣ በእኛ በኩል ማድረግ የሚምንችለውን ሁሉ ለማድረግ የምንሰስተው አንዳችም ነገር አለመኖሩን ስናረጋግጥልህ በታላቅ አክብሮት ነው።
ለብአዴን አባላት እና አካላት!
ይድረስ «ለብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» አካላትና አባላት! የቆየው እና መልካሙ ባህላችን፣ እንደሚያስገነዝበን «ከባዕዳ ቆርሰህ ወደ ወገንህ ዙረህ ጉረስ» የሚል ነው። የትግሬ-ወያኔ ለእናንተ ባዕድ እንጂ፣ ወገናችሁ እንዳልሆነ፣ በየቀኑ የሚፈጸምባችሁን አድልዖ እና በደል ከእናንተ የተሻለ የሚያውቀው የለም። የትግሬ-ወያኔ እናንተን የሚያያችሁ፣ የወገኖቻችሁ መቁረጫ እና መፍለጫ የምሣር እጀታ (ዛቢያ) አድርጎ እንጂ፣ እንደትግል አጋር አድርጎ አለመሆኑን ትስቱታላችሁ አንልም። ይህም በመሆኑ ምንጊዜም አያምናችሁም። ባለመታመናችሁ ደግሞ ዘወትር በስለላ እና በክትትል ውስጥ ያላችሁ ናችሁ። አሁን የወልቃይት-ጠገዴን የማንነት ጥያቄን ተከትሎ የተቀጣጠለው የሕዝባዊ እንቢተኝነት ማዕበል የትግሬ-ወያኔን ጠራርጎ አፈር ሳይቀላቅል ይቆማል ብላችሁ የምታስቡ እና የምታምኑ ከሆናችሁ፣ የምታስቡት በአዕምሮአችሁ ሳይሆን፣ እንደሚባለው በሆዳችሁ ነው ማለት ነው። በአዕምሮአችሁ የምታስቡ ከሆነ፣ የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 41 ዓመታት በዐማራው እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ ገደቡን አልፎ በመፍሰሱ፣ እንደጎርፍ የፈሰሰው የንፁሐን ዜጎች ዕንባ ከፈጣሪ ደጅ የደረሰ መሆኑን አምናችሁ ተቀበሉት። ስለዚህ ምንጊዜም ከተበዳዮች ጎን የሚቆመው የዕውነት አምላክ ፍርዱን የሚሰጥበት ቀን ላይ በመሆናችን፣ የትግሬ-ወያኔ እናንተንም ሆነ እናንተ የወጣችሁበትን የዐማራ ነገድ አጥፍቶ፣ ወደ ምሽጉ እንዳይሄድ፣ ከወገናችሁ ጎን የምትቆሙበት ወቅት ላይ መሆናችሁን ልብ እንድትሉ አደራ እንላለን።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የገዳዩ አካል ብትሆኑ፣ ሥራችሁ በምድርም በሰማይም ይቅር የማይባል ከፍተኛ ወንጀል እና ኃጥያት መሆኑን ከወዲሁ እንድትገነዘቡት እንሻለን። ዛሬ በድብቅ የሚቀር አንዳችም ነገር የለም። ዕድሜ ለዘመኑ ቴክኖሎጂ፣ የምትሠሩትን ማናቸውንም መልካምም ሆነ መጥፎ ሥራ በድምፅ፣ በምስል፣ በሰነድ ተቀርጾ፣ በደቂቃዎች ውስጥ ለእኛ ከጉዳዩ ባለቤቶች ቀርቶ ለዓለም ማኅበረሰብ የሚደርስ መሆኑን አታውቁም ለማለት አንደፍርም። በመሆኑም፣ የእያንዳንዳችሁ እንቅስቃሴ በሕዝቡ ዕይታ ውስጥ ያለ ስለሆነ፣ ከአይቀሬው የትግሬ-ወያኔ ውድቀት በኋላ፣ ተበዳዩ ሕዝብ ለሚያቀርብላችሁ ጥያቄ የምትሰጡት ምክንያት ዋጋ አይኖረውምና፣ ከወዲሁ ከወገናችሁ ጎን እንድትቆሙ በወገናችን በዐማራው ስም ጥሪአችን እናቀርብላችኋለን። በመሆኑም ወገናዊነታችሁ ለወገናችሁ እንጂ፣ ለቅኝ ገዣችሁ ወያኔ እንዳይሆን አደራ እንላለን።
በተቃራኒው ይህንን ጥሪ ተላልፋችሁ፣ ከዐማራው ደመኛ ቡድን ጋር ቆማችሁ የወገናችሁ መቁረጫ ምሣር እጀታ ከሆናችሁ፣ ሞታችሁ አካላዊ ብቻ ሳይሆን፣ መንፈሣዊምም ጭምር እነደሚሆን ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ይህን ጥሪ ተላልፋችሁ በወገናችሁ ላይ አንዳች ጥፋት ብትፈጽሙ፣ በኋላ ላይ ለሚከተለው የከፋ እርምጃ፣ ሕዝባችን «እጄን በእጄ» የሚለው ፀፀት ተሸካሚ እንዳይሆን፣ ከወዲሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናቀርባለን።
በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ የዐማራ ነገድ ልጆች፥
የፖሊስ ሠራዊት ዋና ተግባር የሕዝብን ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ እንጂ፣ ሕዝብን ሰላም መንሳት እና ማሸበር፣ አልፎም ዘር ማጥፋት አይደለም። የመከላከያ ሠራዊት ዋና ተግባርም የአገሩን ሉዓላዊነት እና አንድነት ከውጪ ወራሪዎች መከላከል እንጂ በሰላማዊው የገዛ ወገኑ ላይ ጥይት በመተኮስ መጨፍጨፍ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። ይህንን የምታደርጉ ከሆነ ግን ከዚያ በኋላ ለሚመጣው ሕዝባዊ ምላሽ ተጠያቂዎቹ እናንተው እንጂ ሕዝቡ አይሆንም። በመሆኑም አፈሙዛችሁን በአሸባሪው የወያኔ ቡድን ላይ በማዞር ሕዝባዊ ወገንተኝነታችሁን እንድታሳዩ ከወዲሁ ትጠየቃላችሁ።
ለትግራይ ሕዝብ!
አባቶቻችን እንደሚነግሩን ትግሬና ዐማራ አንድ ዓይነት ሃይማኖት የሚከተሉ፣ ከግዕዝ የተቀዳ ቋንቋ የሚናገሩ፣ በታሪክ እና በመልከዐ-ምድር አቀማመጥ የተቆራኙ፣ የተጋቡ እና የተዋለዱ፣ በዚህም ምክንያት የወል የሆነ ሥነልቦና የገነቡ መሆናቸውን ነው። ካለፉት 50 እና 60 ዓመታት በኋላ ግን ያ የቀድሞ ታሪክ መልኩን ለውጧል። በተለይም ደግሞ ከአብራክህ የወጣው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ ላለፉት 25 ዓመታት በጨበጠው የፖለቲካ ጡንቻ ተጠቅሞ፣ ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ በዐማራው ላይ የዘር ፍጅት መፈጸሙን መቼም ቢሆን፣ የለም አልተደረገም እንደማትለን ተስፋ አለን።
የትግሬ-ወያኔ ቡድን የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ዋና ጠላቶች መሣሪያ በመሆን፣ ኤርትራን አስገንጥሎ፣ አገሪቱን ተፈጥሮአዊ የቀይ ባሕር ባለቤትነቷን በማሳጣት መተናፈሻ ያጣች፣ የበይ ተመልካች ያደረጋት መሆኑን ታውቃለህ። በዚህም የተነሳ፣ በትውልድ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በመከዐ-ምድር ወዘተርፈ አንድ ከሆነው የኤርትራ ሕዝብ ጋር ጥቁር ደም አቃብቶ ኑሮህ የሰቀቀን እንዲሆን ማድረጉን ትዘነጋዋለህ አንልም። ይህ ቡድን አንተን ማኅበራዊ መሠረቱ በማድረግ፣ በፈለገው ጊዜ የፈለገውን የሚያስፈጽምብህ ሁነኛ የጥፋት መሣሪያው እንደሆንክ በመቁጠር፣ ያለፈው አልበቃ ብሎት፣ ዛሬም በዐማራው ነገድ ላይ አጠቃላይ የሆነ የዘር ፍጅት ለመፈጸም በወታደርነት እና በደህንነት ሠራተኛነት የተሰለፉት ልጆችህ ዐማራውን እንደፈለጉ እንዲያስሩ እና እንዲገድሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
የትግሬ-ወያኔ ባዘዘው ትዕዛዝ መሠረት የትግራይ ሕዝብ ዛሬም የወያኔ መሣሪያ ሆኖ በዐማራው ላይ ተከታታይ የዘር ፍጅት ከፈጸመ፣ በትግሬ ሕዝብ እና በዐማራ ሕዝብ መካከል በተከታታይ ትውልዶች ምንጊዜም ሊታረቅ ከማይችል የጠላትነት ስሜት ውስጥ የሚገባ መሆኑን ልብ ልትለው ይገባሃል። ስለሆነም ከጊዜአዊ ስሜት እና «ወያኔ የእኛ መንግሥት ነው» ከሚለው የጧት ጤዛ እምነት ወጥተህ፣ የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን እንድታጠፋ የሰጠህን ትዕዛዝ ከመፈጸም እንድትታቀብ ወገናዊ ጥሪያችን እናቀርባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የትግሬ-ወያኔ ዓላማ አስፈጻሚ መሆንክን ከቀጠልክ፣ ትውልዱ እንደ እስካሁኑ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ እና ተንደላቆ በመላ አገሪቱ የመኖር ዕጣው የሚሟጠጥ መሆኑን ልናስገነዝብህ እንወዳለን። ዛሬ የትግሬ-ወያኔ የዘረጋው ዐማራን የማጥፋት ዘመቻ በሁሉም በትግራይ ልጆች ተቀባይነትን ካገኘ፣ በትግሬና በዐማራው መካከል ለዘመናት ተገንብተው የነበሩ ግንኙነቶች ድልድይ እስከ ወዲያኛው የማይጠግኑ መሆናቸውን መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። ስለሆነም ለጊዜአዊ ጥቅም እና ለልጆችህ ገደብ የለሽ አምባገነናዊ ሥልጣን መራዘም ብለህ፣ ከቋሚው እና ዘላለማዊው ወንድምህ የዐማራ ነገድ ጋር የተቃባኸው ደም «ባለፈው ይብቃ» ብለህ፣ ከሕዝቡ ጎን እንድትቆም የጠበቀ አደራችንን እናስተላልፍልሃለን። የዚህ ጥሪ ተቀባይነት ማግኘት፣ ጥቅሙ ለዐማራው ሳይሆን ፣ ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ የትግሬ ትውልድ መሆኑን ልብ ብለህ፣ ከአጥፊው የትግሬ-ወያኔ ቡድን ራስክን እንድትለይ ጥሪያችን እናቀርባለን!
በዐማራነት እና በኢትዮጵያ አንድነት ለምታምኑ የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች!
የድርጅቶቹ መኖር ዋጋው ሕዝብን ከጥፋት ለመከላከልና ወደ ተሻለ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሕይዎት ለመምራት መሆኑ ግልጽ ነው። ሕዝብ ከሌለ ድርጅቶች አይኖሩም። በመሆኑን የእነዚህ ድርጅቶች መኖር ፋይዳው፣ ቆምንለት ለሚሉት የኅብረተሰብ ክፍል ኅልውና መጠበቅ የሚችልበትን ሁሉ፣ ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር እያገናዘቡ ማድረግ ነው። በዚህ ረገድ ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን የዐማራውን ነገድ ዘር ለማጥፋት ይፋ የሆነ የዘር ፍጅት አዋጅ አውጇል። ይህ የዘር ፍጅት በስፋት እንዳይቀጥል፣ ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቅ አገርም ታሪክ እንዳትሆን፣ ይህ አጥፊ ቡድን የተያያዘውን የጥፋት ጉዞ ማስቆም የግድ ከሚለው ወቅት ላይ ተደርሷል። የትግሬ-ወያኔን ከጥፋት መንገዱ ማስቆም የሚቻለውም፣ ከያዘው የፖለቲካ ሥልጣን፣ በተያያዘው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ትግል አሽቀንጥሮ መወርወር ሲቻል ብቻ ነው። ለዚህም በመጀመሪያ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የዐማራው ነገድ ልጆ አንድነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዛሬ አስፈላጊ ነው። ቀጥሎም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ድርጅቶች፥ ልዩነቶቻቸውን አጣብበው፣ አንድ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ዙሪያ በመሰባሰብ፣ አጥፊው ቡድን አጥፍቶን ሳይጠፋ በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል። ለዚህ ዕውን መሆንም፣ ማንንም ያላገለለ የዘመቻ ሥራ ሊሠራ የሚችል ግብረኃይ ተቋቁሞ፣ የሚከተሉት ሥራዎች በአፋጣኝ እንዲሠሩ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።
አንደኛ፦ የዕለቱን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተለ ዝርዝር መረጃዎችንና ዘገባዎችን ወጥነት እና ተከታታይነት ባለው መልኩ ለዓለም ማኅበረሰብ፣ ለዓለማቀፋዊ እና አሕጉራዊ ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሚያቀርብ የመረጃ ሥርጭት አካል መሰየም።
ሁለተኛ፦ በዲፕሎማሲው መስክ መልካም ስም ያላቸውን ሰዎች በማቀናጀት ወያኔ አገሪቱንና ሕዝቡን ወደ ጥፋት ጎዳና እየወሰዳት መሆኑን ሳይሰለቹና ሳይዘናጉ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካሎች የሚሰጥና የሚያግባባ ቡድን መፍጠር፤
ሦስተኛ፦ በትግሬ-ወያኔ ግፈኛ ቡድን ለተገደሉ፣ ለታሰሩ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ የሚያሰባስብና የሚለግስ ቡድን መፍጠር፣
አራተኛ፦ ወያኔ አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች ባስቸኳይ ተገናኝተው፣ መጭውን የአገራችን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ወጥ እና ተደጋጋፊ የሆነ ሥራ በአስቸኳይ መጀመር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።
በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ነፃነት ወዳዱ እና ጀግናው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! «አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል» እንዲሉ፣ የዐማራው፣ የኦሮሞው፣ የሶማሌው፣ የአኙዋኩ ወዘተርፈ ችግር የእያንዳንዳችን ችግር ነው። የዐማራው ፍጅት ያንተም ፍጅት ነው። የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ሕዝብ ላይ እንዳደረሰው በደል ሁሉ፣ የበደሉ መጠን በዓይነት እና ሁኔታ ይለያይ እንጂ፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ፈጽሞታል። ይህ የአገር፣ የታሪክ፣ የባህልና የማንነት ጠር የሆነ ቡድን፣ እስከ ዛሬ በዐማራው ላይ ያደረሰው በደልና ግፍ አልበቃ ብሎት፣ በግልጽና በይፋ በአዋጅ፣ የዐማራን ዘር ለማጥፋት ለወታደሩና ለጸጥታ ሠራተኛው ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህ ጥፋት በዐማራው ላይ ተፈጽሞ የማይቀር፣ ሁሉንም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ነገዶች ለማጥፋት ወደኋላ የማይል መሆኑን ባለፉት ዘመናት በተለያዩ ቦታዎች የወሰዳቸው አስከፊና ዘግናኚ ርምጃዎች ምንነቱን አሳይቷል። እሳትን ማጥፋት በሩቁ ነውና፣ ይህ በዐማራ ሕዝብ ላይ የታወጀው የዘር ፍጅት በእያንዳንዳችን ደጅ ከመድረሱ በፊት ከዐማራው ወገንህ ጋር በመቆም እሳቱን ከዚያው ላይ ለማጥፋት የተለመደ ኢትዮጵያዊ ትብብርህንና ጀግንነትክን ዳግም እንድታስመሰክር ጥሪአችን ስናቀርብልህ በታላቅ አክብሮት ነው። የዐማራው መዳን የኢትዮጵያ መድኅነት ነው። ሞትና ስደት ባለፈው ይብቃ! ናዚያዊው የትግሬ-ወያኔ አጥፊ ቡድን ነውና፣ አጥፍቶን ሳይጠፋ ቀድመን ለማጥፋት ከተቀጣጠለው የዐማራ ነገድ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ጎን እንቁም!
በመጨረሻም፥ ከላይ የዘረዘርናቸውን ተግባሮች ካከናወንን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን የትግሬ-ወያኔ የጫነብንን የናዚ-ዓይነት አገዛዝ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አሽቀንጥረን ለመጣል እንደምንችል ጥርጥር የለንም። ለዚህም ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይርዳን።
ወያኔ አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ እርሱን ለማጥፋት እንተባበር!
ድል ለሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ረቡዕ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.
ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፮
ሞረሽ ለዐማራ ሕዝብ!!!
Leave a Reply