
የተለያዩ ድርጅቶች የወያኔ/ ኢህአዴግን መንግስት በትጥቅ ሀይል ለማስወገድ በአስመራ ስልጣን ከያዘው ሻቢያ ጋር መቀራረብና ተባብሮ መስራትን መርጠዋል።
ይህን በተመለከተ ባንድ በኩል የወያኔ/ኢህአዴግን የግፍ ስርአት ለማስወገድ ከማንም ጋር ቢሆን ማበር አስፈልጊ ነው የሚሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ የወያኔን የግፍ ስርአት ማስወገድ አስፈላጊ ሲሆን ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚከተለው ፖሊሲ በብሄራዊ ጥቅማችን ላይ እና በመጻኢው ነጻነታችን ላይ እጅግ ታላቅ አደጋን ስለሚያሰከትል ድንገት ብቅ ያለው ተቋርቋሪነት ከምን የመነጨ እንደሆነ ጠንቅቆ መረዳትና ታላቅ ስህተት ከመፈጸም መታቀብ ያሻል ይላሉ::
በዚህ ጽሁፌ የሻቢያ “ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪነት” በተግባር ሲታይ ምን ማለት እንደሆነ ለማሳየት በጥቂት ውሱን ጉዳዮች ላይ በማተኮር ያለኝን አመለካከት አካፍላለሁ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
ይድረስ ለአቶ አክሊሉ ወንድአፈረው.
እኔ ምለው ከባዕዳን ነፃ የሆነ ትግል ለማኪያሄድ የሚቻለው የት ተሁኖ ነው? ዛሬ ደግሞ የአፋር ህዝብ ከኢትዪጵያውያን ወንድሞቹ ጋር አብሮ ለመታገል ከአራቱ ተፋላሚ ድርጅቶች አንዱ ሆናል።መልዕክትህ በሙሉ እንደ ተስፋዪ ገብረአብ ትጥቅ አስፈች ነው። አልኩ ለማለት ካልሆነ በቀር የወረቀት ነብር ከመሆን ሌላ እስከአሁን ድረስ ምን ሰራህ ምን የተጨበጠ ነገር አመጣህ? አሁን ኢትዮጵያችን የምትፈልገው ከፊቱአ የሚቆሙትን አደናጋሪ ፀሀፊዎችን ሳይሆን ተጨባጭና ሁሉን አቀፍ ትግል ነው። አሜሪካ ቁጭ ብሎ ሀምበርገር እየገመጡ ትግል አይመራም ስትሉ በርሃ ወርደው ትግሉን ሲቀላቀሉ ደግሞ ሌላ ሰንካላ ሀሳብ ትወረውራላችሁ።ይህ ፅሁፍ ከወያኔ ብዕር በምን ይለያል? ተግባር 1 ተግባር 2 ተግባር 3…ቀጥልበት።
አቡ ተሰማ ነኝ
Akilelu Wondeaferaw you change your name befor you used another name please creat
clean minde and think good for Ethiopian people .