• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ የስፖርት ጋዜጠኛ ወይስ ተርጓሚ ነው ያለው?

February 6, 2015 06:43 am by Editor Leave a Comment

“የምን ማራዶና የምን ፔሌ ፔሌ 

እኛም አገር አለ ገብረመድኅን ኃይሌ”

ደምሴ ዳምጤ ጎልታ የምትጠቀስለት መንቶ ግጥሙ ነበረች፡፡ ለአገሪቱ ስፖርት ዕድገት በተለይም እግር ኳሱ እንዲያብብ በሙያው ያደረገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ክሂላቸው ከማንም እንደማያንስ በማንፀባረቅ ነበር፡፡ በ1970ዎቹ መጨረሻና በ80ዎቹ መጀመርያ ጎልተው ወጥተው የነበሩት እነሙሉጌታ ከበደ፣ ሙሉጌታ ወልደየስ፣ ገብረመድኅን ኃይሌን ሲያወድስ ገጣሚ ሆኖ በመገኘት ነበር፡፡

ስፖርት እንደ አንድ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጉዳይ ራሱን የቻለ ሰፊ ርዕሰ ጉዳይ እየሆነ የመጣ ሲሆን ሊሰጠው የሚገባው ግምትም ያን ያህል እየከበደ መጥቷል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ምጣኔ-ሃብታዊ ጉዳዮች ብቻ የሚተነትኑ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዳሉ ሁሉ ስፖርታዊ ጉዳዮችን ብቻ የሚተነትኑ ጋዜጦች፣ ሬድዮኖች፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ ድረ-ገጾች እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን በርካታ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት በሃገር ቤት እየተተገበረ ያለው የስፖርት ጋዜጠኝነት ምን ያህል ሙያዊ እና ስነምግባራዊ ነው ለሚለው እኔም በርካታ አሉታዊ አስተያየቶች አሉኝ፡፡

eth football team1በአብዛኛው ለሃገርቤት መገናኛ ብዙሃን ስፖርት ማለት የእግር ኳስ ጨዋታ ሆኗል ያውም የአውሮፓ ክለቦች የእግር ኳስ ጨዋታ፡፡ የእግር ኳስ ጨዋታ ካለው አዝናኝነት፣ ከተመልካቹ ብዛት እና ከሚያንቀሳቅሰው ከፍተኛ ገንዘብ አንጻር በጋዜጣ ላይ የሰፋውን ቦታ እና በሬድዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ ደግሞ የበዛውን የአየር ሰዓት ቢይዝ የጎላ ጥያቄ ላያስነሳ ይችላል፡፡ ሆኖም በእኔ ዳሰሳዊ ግምት በተለያየዩ የኤፍ ኤም እና የኤ ኤም ሬድዮ ጣቢያዎች ከሚቀርቡ የስፖርት ዝግጅቶች ብዙውን ግዜ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ እና አንድ አንድ ግዜ ከዘጠና በመቶ በላይ የእግር ኳስ ጉዳይ የሚተነተን ሲሆን ከዚህም የሚበዛው የአውሮፓ የእግር ኳስ ክለቦች ጨዋታ ጉዳይ ነው፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት በተለያዩ ጉዳዮች ተፅዕኖ ሊሆን ይችላል አንደኛ የእግር ኳስ በተለይም ደግሞ የአውሮፓ ክለቦች የእግር ኳስ ጨዋታ ከሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የተሻለ አዝናኝ ነው ተብሎ ስለሚገመት፤ ሁለተኛ በሃገር ውስጥ አብዛኛው የስፖርት አድናቂ ማህበረሰብ የእግር ኳስን በተለይም ደግሞ የአውሮፓ ክለቦች የእግር ኳስ ጨዋታን የበለጠ ይወዳል ተብሎ ስለሚገመት፣ ሦስተኛ ደግሞ በተለይ ከአውሮፓ ሃገራት መገናኛ ብዙሃን የሚለቀቁ እጅግ ብዛት ያላቸው እና የየክለቦቻቸውን ሁኔታ የሚተነትኑ መረጃዎች በተትረፈረፈ ሁኔታ ማግኘት መቻሉ የጋዜጠኞችን ትኩረት በመሳቡ ሊሆን ይችላል፡፡ በእነዚህም ሆነ በሌሎች ምክንያት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን የአውሮፓ ክለቦችን የእግር ኳስ ጨዋታ ተንታኝ ሆኗል፡፡

ዋናው ርዕሰ ጉዳይ ተረስቶ ከጨዋታው ጋር የማይያያዙ ጉዳዮች በበለጠ ትኩረት ሲዘገቡ ይስተዋላል፡፡ እከሌ የተባለው አንድ የአውሮፓ ክለብ ተጫዋች የሴት ጓደኛ ስትደሰት እና ስትበሳጭ ምን እንደምታደርግ ጠቀመውም አልጠቀመውም ለኢትዮጵያዊ ስፖርት ተከታታይ ይቀርብለታል፡፡ አሁንም ጠቀመውም አልጠቀመው ስለተጫዋቹ አባት፣ እናት እና ሌሎች ዘመዶች ማንነት እና ምንነት እንዲያነብ ወይንም እንዲያዳምጥ ይደረጋል፡፡

የእኛ ሐገር የስፖርት ጋዜጠኞች በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ሊያሠለጥኑ በሚመጡ የውጭ ሐገር አሠልጣኞች ጭምር መሣለቂያ ሆነዋል የቅርቡን ብናስታውስ እንኳን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማሊ ብሔራዊ ቡድን መሸነፉን ተከትሎ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሐገር ቤት የሚገኙ የመንግስት እና የመንግስት ደጋፊ ጋዜጠኞች ለቡድኑ መሸነፍ አሰልጣኙን ተጠያቂ ለማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎችን የጠየቁ ሲሆን ለጋዜጠኞቹ ምላሽ የሠጡት የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ በጋዜጠኞቹ አቅም እና እውቀት ተሳልቀዋል፡፡eth football team2

አንድ የኢቲቪ ጋዜጠኛ አሰልጣኙን “ቀኝ ተከላካይ ቦታ ችግር እያለ ለምን ሌላ ተጫዋች አልቀየሩም” ብሎ ሲጠይቅ አሰልጣኙ በግርምት “እንግዲህ ጎበዝ የቀኝ ተከላካይ እጥረት እንዳለ አውቃለው በዚህ ቦታ ጎበዝ ተጫዋች የባርሴሎናው ዳንኤል አልቬስ ነው እርሱ ደግሞ ብራዚላዊ ሆነ እንጂ ኢትዮጵያዊ ቢሆን አሰልፈው ነበር በተረፈ ደካማ ተጫዋች ለመኖሩ ተጠያቂ የሐገሪቱ አሰራር እንጂ የእኔ አሰለጣጠን አይደለም” ሲሉ አክለዋል፡፡

ሌላው አስገራሚ ጉዳይ “እኛ የተሸነፍነው በማሊ ብሔራዊ ቡድን እንጂ በኦሮሚያ ብሔራዊ ቡድን አይደለም” ሲሉ ጋዜጠኞቹ ጫጫታ አሰምተዋል፡፡ አሰልጣኙ ትክክል ናቸው ምክንያቱም ለኦሮሞ ጎሳ ብሔረሠብ የሚል ስያሜ ከሠጠን ለአማራውም ጎሳ ብሔረሰብ የሚል ስያሜ ከሠጠን እና ብሔር ማለት ደግሞ የአንድ ሐገር ነዋሪ መሆኑን የሚያውቅ ጭንቅላት ካለን ለምን የኦሮሚያ ብሔራዊ ቡድን የአማራ ብሔራዊ ቡድን ሲባል ንዴት ውስጥ እንገባለን፡፡ ዘይትገርም ነው ነገሩ የመንግስት ጋዜጠኛው የብሔርን ትክክለኛ ትርጓሜ ሣያውቅ በየደቂቃው ብሔር ብሔረሠብ ሲል ይውልና የኦሮሞ የአማራ ብሔራዊ ቡድን ተብሎ ሲጠራ እምቧከረዩ ይላሉ ብሔር አለ ካላቹህ የአማራ ወይም የኦሮሞ ብሔራዊ ቡድን ሲባል ምን ያናድዳችኋል፡፡

eth footballአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የስፖርት ጋዜጠኛ የውጭ ሐገር ስፖርት ሲተነትኑ ለሚሰማቸው ኢትዮጵያዊ የስፖርት ታዳሚ አፍ የሚያስከፍት ቃላት ሲያወጡ ይሠማል በጥቂቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ላለው ግለሠብ ግን የእነርሱን ወሬ ከእንግሊዝ የስፖርት ታብሎይዶች የተተረጎመ መሆኑን እማኝ ሳያስፈልገው የመረጃውን ምንጭ በመግለፅ ያስረዳችኋል፡፡ ይህን ጊዜ እኛ ሐገር ያለው የስፖርት ጋዜጠኛ ሳይሆን የእንግሊዝ የስፖርት ጋዜጣዎችን ወደ አማርኛ እና ወደተለያዩ የሀገራችን ቋንቋ ተርጉሞ የሚያቀርብ የስፖርት ጋዜጣ ተርጓሚ መሆኑንን ልብ ይሏል፡፡

ለዚህም ይመስለኛል አንድ ኢትዮጵያዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ስለ ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ድክመት ከሚያወራ ይልቅ ስለ አርሠናል ድክመት እና ስለ ማንችስተር ቀጣይ እቅድ ቢያወራ ይቀለዋል፡፡ የቀለለው በርካታ መረጃን ስለሚያገኝ እንዲሁም ያንን መረጃ ወደአማርኛ ተርጉሞ ለማቅረብም ምቹ ስለሆነ ነው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ስለምን ለምን አታወሩም ሲባሉ መልሳቸው ስለ ቡና መረጃ ከየትም አናገኝም የሚል ነው፡፡ ይህ እጅግ አሳፋሪ እና አሸማቃቂ መልስ ነው የአርሠናልን ጉዳይ የእንግሊዝ ታብሎይድ ላይ የሚፅፍ አንድ ብሪታንያዊ ጋዜጠኛ መረጃው መጥቶለት ሳይሆን ሄዶ ጠይቆ ነው መረጃውን ያመጣው፡፡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ግን የቡና ወይም የኤልፓ ዜና እቤቱ ድረስ በኢንተርኔት መስኮት እንዲመጣለት ይጠብቃል፡፡ ከዛም ውጪ አዲስ አበባ ስታዲየም ገብቶ ጨዋታ አንብቦ ትንተና ለመስጠት ያለው እውቀት አነስተኛ መሆኑን ተረድቶ አልያም ለመሸፈን ሲል ስለ ሮናልዶ የወገብ ቁጥር ይነግረናል፡፡

በአንድ ወቅት ፌስቡክ ላይ “ብሔራዊ ቡድኑ ከተሸነፈ ለመንግስት ጋዜጠኛው ጥፋተኛ ፌዴሬሽኑና አሰልጣኙ እንጂ ፌዴሬሽኑን እና አሰልጣኙን በበላይነት የሚመራው የስፖርት ሚኒስትር አይደለም” የሚል ፅሁፍ ማስነበቤን ይታወሳል፡፡ ይህ ነገር ዛሬም ሳይቀየር የመንግስት ሚዲያውን ስከታተል እንደጠበኩት አሰልጣኙን ሲሰድቡ ነው የሚያረፍዱት፡፡ አሠልጣኑ ምን ማድረግ እንደነበረበት ግን አይነግሩንም ምክንያቱም ይህን ለማድረግ እውቀት ያስፈልጋል አልያም የገነነ መኩሪያ አይነት ስፖርታዊ እይታ ያስፈልጋቸዋል፡፡genene

እግር ኳሳችን እንዳያድግ እንቅፋት የሆነው የስፖርት ሚኒስቴር እንጂ አንድ አሰልጣኝ ሊሆን አይችልም አሰልጣኝ በመቀያየር ውጤት ሊመጣ አይችልም፡፡ አሰልጣኝ ከተቀየረም እንደ ገነነ መኩሪያ በእውቀት ተመርተን ሐሳብ ማቅረብ ይኖርብናል፡፡ ካልሆነ ግን ዘወትር የስፖርት ሚኒስተርን ችግር ይፋ ሳናወጣ እና እንደገነነ መኩሪያ ሊብሮ Genene Mekuria Libro የመሳሰሉትን ድንቅ ኢትዮጵያዊያን አቅም እውቀት ትተን የትም ልንደርስ አንችልም፡፡ በህይወቴ በሐገራችን ስፖርት ዙሪያ ሳስብ የገነነ መኩሪያን አቅም ኢትዮጵያችን እንድትጠቀም አለመደረጉ ሁሌም የሚያነገበግበኝ ጉዳይ ነው፡፡ ገነነ ብሔራዊ ቡድኑን ይመራ ዘንድ የግድ በባለስልጣናቱ ተወዳጅ መሆን የለበትም፡፡

እጅግ የሚከፋው ግን እንዲህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ስህተቶች በሙሉ ባካተተ መልኩ የሚተገበረው የስፖርት ጋዜጠኝነት ትክክለኛው ስፖርት ጋዜጠኝነት እንደሆነ እየተወሰደ መምጣቱ ነው፡፡ አንድ ጉዳይ በተሳሳት መልኩ በተደጋጋሚ ሲተገበር እና ለየት ባለ መልኩ በተስተካከለው መንገድ ጉዳዩን የሚያቀርበው ሲጠፋ ያ የተሳሳተ መንገድ በዘልማድ ተቀባይነት ያገኘ መንገድ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ስፖርት ጋዜጠኝነትም በዚህ መልኩ እየነጎደ ሲሆን ይኄ ሙያውንም ባለሙያውንም ቀስ በቀስ መጉዳቱ አይቀርም፡፡
‪#‎ሁኔ አቢሲኒያ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule