• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ

July 13, 2013 01:36 am by Editor 2 Comments

መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም

“በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም!”

አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌ ልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia’s unemployment “በኢትዮጵያ ስራ አጥንትን ለመሸሸ ” ያለው ዘገባ ስለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥ አሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል ። በዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ስራ ላቀረቡ ወጣቶች ስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ሽህ ዶላር ያበድራል ተብሎ ሰምቻለሁ። የተባለው በእኛ ሃገር ይሆን ? ስልም ጠየቅኩ ! ” ጀሮ ለራሱ ባዳ ነው ” ብየ አላየሁ አልሰማሁም ብየ ልለፈው! አሁን ሰምቻለሁና ይሰጣልም ብየ ለቀበለው ። ግናስ ለብድር አሰጣጥ መስፈርቱ ምንድን ነው? ይህ ግን አልገባኝም ! መስፈርቱ ወሳኝ ሆኖም ይህንንም አድልኦ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከት በሃይማኖትና በዘር ሳይለዩ እኩል ታይተው ድጋፉ ይደረጋል በሚል ልቀበለው ። የተባለው ሁሉ እውነት ቢሆን እንኳ የተጠናን ስራ አውርቦ ጠቀም ያለ ብድር የማግኘት እድሉ ተምሮ ስራ ላጣው አለያም ለነቃው እና ለተደራጀው የከተማ ወጣት እንጅ ለቀረው መፍትሄ አይደለም ። ይህ መፍትሄ በዘገባው ቀርበው ላየናቸው በማንኛውምወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራ ለመሰደድ ለተዘጋጁት እና ከህጋ የሃገራት ሁለትዮሽ ስምምነት ውጭ ለሰደዱት ከገጠሩ ክፍል የሚጋዙት ቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱት እህቶች የሚፈይደው ነገር የለም ።

በአረብ ሃገር በኮንትራት ስም የሚሰደዱ እህቶችን እንዳይሰደዱ ለማገድ አሸጋጋሪ ደላላዎችን ከመቆጣጠሩ ጎን ለጎን ዜጎችን ከድህንት የሚዎጡበትን መንገድ መንደፍ ፣ የዜጎችን ነጻነት ማክበር አና ሁሉንም ዜጎች እኩል በማየት መሰረተ ልማቶቸን በማስፋፋት የስራ እድል መክፈት ዋናው መፍትሔ ሊሆን ይገባል። “ኢኮኖሚያችን አደገ ተመነደገ” እየተባለ አቅማችን ይህunemployed 1 ማድረግ ካልቻለ ብቸኛው መፍትሄው ” አትሰደዱ” ብሎ መልፈፉና እና “ለሚሰሩት እድሉ ” አለ ብሎ መደስኮሩ ከመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም !

ስደት ክፉ ነገር ነው ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑት እያላቸው ካላቸው ለመጨመር ከሚሹ ስግንግቦች ውጭ ብዙው ስደተኛ ለመሰደዱ የስራ ማጣት ፣ የድህነትና የኑሮ ውድነት በቂ ምክንያት እናዳለው በስደቱ አለም ስኖር ካገኘኋቸው ስደተኛ ወገኖቸ የተረዳሁት ሃቅ ነው ። የኑሮ ውድነት ሳያንገሸግሽ ፣ ሳያጨናንቀው ስደትን የሚፈልግ የለም ፣ በሃገሩ ተምሮና ሰርቶ እሱንና ቤተሰቡን መደገፍ እየቻለ ስደትን የሚመርጥ የለም! የመንግስት ሃላፊዎች ለገጽታ ግንባታ የሚለቋቸውን መረጃዎች ገታ አድርገው በስደተኛው ችግር ላይ ቢያንስ ትክክለኛ መረጃ ቢሰጡን መልካም ነበር ።

ከሁሉም በላይ ወደ አረብ ሃገራት በኮንተራት ስራ ስም የሚላኩ ዜጎችን ጉዳይ ቆም ብለው ሊመረምሩት ይገባል። ሰው ” በሃገሬ ተቸገርኩ ፣ ተምሬ ስራ አጣሁ !” እያለ ስደቱን ማቆም ይከብዳል። ያም ሆኖ በህገ ወጥ ደላላ ተታልለው በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደዱትን ለማስቆም መንግስት በስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ስም እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥ የበከተ ድለላ በሰውር የሚሰራውን ስራ ሰንሰለቱን ከቁንጮው ሊበጣጥሰው ይገባል ። ስደትን ማሰወቆም ካልቻልን አማራጩ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሃገር እና ሊሰሩት ስለሚችሉት ስራ ትክክለኛ መረጃ እና ቅድም ዝግጅቶችን በትክክል አሟልቶ ማቅረብ አማራጭ ሊታይ ይገባል። ከዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ዜጎችን በሃገራት መካከል በሚደረግ የሰራተኛ ውል መሰረት በህጋዊ ኮንትራት ስራ ዜጎችን መላክ እና ከተላኩም በኋላ በመብት ማስከበሩ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስረትር መስሪያ ቤት በፖለቲካ ታማኝነት ሳይሆን ዲፕሎማሲው ጥብብ የተካኑትን ከሃላፊዎች በበቂ ሁኔታ በአረብ ሃገራት ሊመድብ ይገባል!

ያለንት የስልጣኔ ዘመን ነውና መረጃን በመደባበቅ እውነትን ማጥፋት አይቻልም። ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ማቀበል ያዋርዳል እንጂ አያስከብርም ፣ ከሃቅ የራቀ መረጃ ገጽታን ያጨለማል እንጅ ፈካ አድርጎ ቀይሮ አያሳይም ! በአልጀዚራ ዘገባ እንደተነገሩት አንዳንድ መረጃዎች አጋጣሚውን ገጽታ መገንቢያ አድርገን እውነቱን የምንሸፋፍን ከሆነ ትልቅ ስህተት ተሳስተናል ! እውነትን በውሸት ለመድፈን ስንቆፍር ነገም እንደ የትናንቱ ከመከራ መውጣት አይቻለንም ! ዛሬም ጉዟችን ቅጥፈት ከሆነ በምናየው የወገን ሮሮ ፣ የሰቆቃ ድግግሞሽ ስናለቅስ እንደኖርን ስናለቅስ እንኖራለን ! አባቶች “በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! ” እኛው ራሳችን በሽታችን ስንነግራቸሁ ስሙን ፣ መድሃኒቱንም ፈልጉልን ! የማለዳ ወጌን አበቃሁ !

በሽታችን ተረድቶ መድሃኒት ጀባ የሚል የህዝብ አገልጋይ ይስጠን!

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Askle belay says

    July 13, 2013 07:24 am at 7:24 am

    Amen ysten !

    Reply
  2. belayneh says

    July 13, 2013 11:21 am at 11:21 am

    lehageru ena lezegochu yemayasib mery balebet hager yezegoch meseded asgeramy ayhonim

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule