• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል

December 26, 2012 12:25 pm by Editor 2 Comments

ሙስና በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ኢህአዴግ አይክድም። ኢህአዴግ ባለስልጣኖቹ በሙስና ስለመዘፈቃቸው ማመኑን የገለጸው “የመንግስት ሌቦች አስቸገሩኝ” በሚል ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሙስና የተለከፉ ዋጋቸውን ያገኛሉ” ሲሉ ስልጣን በያዙ ማግስት መዛታቸውን የሚያስታውሱ በስተመጨረሻ “ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል” የሚል ድምዳሜ ላይ ነው።

“ትልቅ ጫካ ሰርታችሁ የኛንም የናንተንም ሌቦች መደበቅ በመቻላችሁ ሁሉንም መመንጠር ስላልቻልን እየተተራመስን ነው” በማለት ጣታቸውን ወደ ነጋዴው ህብረተሰብ በመቀሰር ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአገሪቱ ያለውን ሙስና አስከፊነት በገለጹበት መድረክ “ስልጣን የመክበሪያ ብቸኛው መንገድ በሆነበት አገር ዘላቂ ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው። በኪራይ ሰብሳቢነት እንደ መንግስትም፣ እንደ ባለሃብትም መቀጠል አንችልም። እንደ ሶማሌ ነው የምንሆነው። እንተራመሳለን። በድጎማ እየኖርን ሙስናው ከከፋ አገር የሌለው ባይተዋር እንሆናለን” ሲሉ የጉዳዩን አሳሳቢነትና በኢህአዴግ ስሌት ሙስናው የሚያስከትለውን የመጨረሻ ጣጣ አመላክተው ነበር።

“በሁሉም አቅጣጫ እየታረድን ነው” ሲሉ የፖለቲካውና የሙስናውን መዘዝ ያመለከቱት አቶ መለስ፣ ተፈጥሯል ያሉት ጫካ አይጥና እባብ ብቻ ሳይሆን ዝሆንም እንደሚደበቅበት ሲገልጹ በማግስቱ “ዝሆኖቹን” ይለዩና እሳቸው በሁሉም ችግር ውስጥ የማለፍ ብቃት እንዳለው የሚገልጹት ኢህአዴግ ማንነቱን ያሳያል ተብሎ ሲጠበቅ ሁሉም ነገር ተረት መሆኑ የስርዓቱን ተያይዞ በሙስና መበስበስ አመላካች እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ይስማማሉ።

ይህ ሁሉ ካለፈ በኋላ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለህዝብ እንዲተላለፍ በመወሰን ያካሄዱት ስብሰባ እንደተባለው በይፋ ሙሉ በሙሉ መረጃ የማግኘት መብት አለው ከሚባለው ህዝብ ጆሮ እንዳይደርስ ቢደረግም በተባራሪ የተገኙት መረጃዎች አስገራሚ ነበሩ። ከሁሉም በላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ሚኒስትሩ ደብረጽዮንና የስኳር ልማት ድርጅት ፊት አውራሪ የሆኑት አባይ ጸሃዬ “ግንዱን ካልቆረጥነው፣ ግድግዳውን ካላፈረስነው ጣጣው ብዙ ነው” በማለት የተናገሩት ስለ ሙስና ነበር።

በኢትዮጵያ በሙስና የአገሪቱን ሃብት የሚጋልቡበት፣ የፍርድ ቤቶችን ውሳኔ የሚያዛቡ፣የራሳቸው አገር፣ ህግና፣ አስተዳደር የመሰረቱ ስለመኖራቸው በስፋት መነገር ከጀመረ ሰንብቷል። እነዚህ ከህግና ከስርዓት ውጪ የሆኑ አካሎች ከባለስልጣናት ጋር በሽርክና፣የባለስልጣን ሚስቶችን በድርጅታቸው ውስጥ በማስገባት፣ የባለስልጣን ዘመዶችን በየጥጋጥጉ በመወተፍ በቅምጥ ጋዜጦች፣ አርቲስቶችና በራሱ በኢህአዴግ መገናኛዎች ሳይቀር እየተወደሱ አገሪቱን ሲዘሉባት መመልከት እንደተባለው አገሪቱ እንደ አገር መቀጠሏ አሳሳቢ መሆኑንን የሚያረጋግጥ እንደሆነ በስፋት እየተተቸበት ነው። አቶ መለስም አስቀድመው የተናገሩት ይህንኑ ራሳቸው ገንብተው ራሳቸው ማፍረስ ያቃታቸውን የሙስናና ልቅነት አሠራር ነበር።

ህዝብ ሁሉንም ጠንቅቆ እንደሚያውቅ በተለያዩ አጋጣሚዎች ቢገልጽም ሰሚ ማጣቱ አሁን አገሪቱ ላይ ከሰፈነው የኑሮ ቀውስ፣ የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የፖለቲካ አለመተማመን፣ የሃብት ክፍፍል፣ የሃይማኖት የመብት ጥያቄዎችና “ማን እየበላ ማን ጦሙን ያድራል” ከሚለው የመኖርና አለመኖር ጥያቄ ጋር ተዳምሮ አቶ መለስ እንዳሉት እንደ መንግስትም፣ እንደ ባለሃብትም መቀጠል የማይቻልበት ደረጃ ሊደረስ ይችላል የሚለው ፍርሃቻ ሚዛን የሚደፋ እየሆነ ነው።

በተደጋጋሚ በሙስና ጉዳይ ላይ የሚጽፈው ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ጠንካራ ርዕስ በመስጠት በርዕሰ አንቀጹ “ትልቁ ጥያቄ ተግባሩ የት አለ? የሚል ነው፡፡ የመንግሥት ሌቦች ተራ ሌቦች አይደሉም፡፡ አደገኞች ናቸው፡፡ ምክንያቱም በገንዘብ የታጀቡ ናቸው፡፡ በሥልጣንም የተደገፉ ናቸው፡፡ ምግባረ ብልሹነት የተጠናወታቸው ስለሆኑ ሕገወጥ ገንዘብና ሥልጣናቸውን ላለማጣት ሕግን ከመጣስና ወንጀል ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፡፡ ሌላውን አስወግደው እነሱ ብቻ የሚቆጣጠሩትና የእነሱን ፍላጎት ብቻ የሚያረካ መንግሥት ከማቋቋም ወደኋላ አይሉም፡፡ የመንግሥት ሌቦች ካልተወገዱ የሌቦች መንግሥት ያቋቁማሉ ያልነውም ለዚህ ነው” ሲል የተግባራዊነት ጥያቄ አንስቷል።

ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያወገዙት የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ሙስናን አስመልክቶ ለተጠየቁት “… በዚህ አገር ላይ፡፡ ሲሾም ያልበላ የሚባል በጥረት ያልተደገፈ፣ በብልጥነት አስተምህሮ ላይ የተመሠረተ አካሄድ ነበር፣ ይሄን መስበር ያስፈልግ ነበር፡፡ ይሄንንም ለመስበር አመለካከቱን ደጋግሞ መውቀጥ መቀጥቀጥ ያስፈልጋል፡፡ በርግጥም የስርዓቱ አደጋ ነው፣ እንታገለዋለን፡፡ ዕድገታችንን የሚፈታተነን አንዱ አደጋም ይሄ ነው” የሚል መልስ ነበር የሰጡት።

የፌደራሉ የስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን “መንግስት በከፍተኛ ደረጃ ሙስና ላይ እንድንዘምት መመሪያ ሰጥቶናል” በማለት በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ተናግረዋል። ይህንኑ በተናገሩበት አንደበታቸው ከስዊዝ ባንክ እንዲመለስ የተደረገው ገንዘብ ለማን ተሰጠ ለተባሉት የሼኽ መሐመድ አላሙዲንን ስም መጥራት ፈርተው “ይለፈኝ” ማለታቸውን ተረድተናል።

ጎልጉል ያነጋገራቸው እንደሚሉት የፖለቲካውን የበላይነት በመጠቀም በብርሀን ፍጥነት ብር የሰበሰቡትን፣ ህንጻ የገነቡትን፣ አስመጪና ላኪ የሆኑትን፣ ኢንዱስትሪ የከፈቱትን፣ ኮንትሮባንድ የሚነግዱትን፣ ቀረጥ የማይመለከታቸውን “አይጥና ዝሆኖች” ከፍተኛ የአገሪቱን ፕሮጀክቶች በብቸኛነት የተቆጣጠሩትን፣ ጨረታውንና ግዢውን በብቸኛነት የተረከቡትን፣ ተለጣፊ የሚባሉትን፣ ጉቦ አቀባባዮቹን፣ አማላጅ ሆነው ጉዳይ በማስፈጸም የሚነግዱትን የመንግስት ሌቦች፣ በብድር ገንዘብ ባለስልጣን እያሳከሙ የሚዘመርላቸው፣የፓርቲዎች ንብረት ናቸው ስለሚባሉት “እርም ተቋሞች” ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ባለፈ ባገደመ ቁጥር ስም እየሰየመ የሚቆጥራቸው ሃብቶች መነሻቸው፣ መድረሻቸውና የማን እንደሆኑ ኮከብ ከደረደሩት ወታደሮች ጀምሮ በዝርዝር ያውቃቸዋል።

ጥያቄው ተራ ዜጎች የሚያውቁትን “እርም የተሞሉ” ሃብቶች በደህንነት የተደራጀው የጸረ ሙስና ኮሚሽንና የባልና ሚስት የመኝታ ቤት ወሬ ሳይቀር የሚለቅመው ኢንሳ ዝምታን የመረጡበት አግባብ ነው። “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ” በሚል ርዕስ ለጎልጉል ቃለ ምልለስ  የሰጡት የኢህአዴግ ሰው “የስርዓቱ አይነተኛ መገለጫ ሆን ብሎ በሙስና ማበስበስ ነው” ይሉና ስለዝምታው ሲናገሩ “አቶ መለስ ሁሉንም ያውቃሉ። ልንካው ቢሉ ለራሳቸውም አደጋ ነው። ሙስናው ውስጥ የደህንነት ኃይሉ፣ መከላከያው፣ ባለስልጣናቱ፣ … ተነክረውበታል። ስለዚህ ማን ማንን ይነካል?” ማንስ በማን ላይ ይመሰክራል?” በሚል በወቅቱ አስገራሚ የተባለ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በድርጀት ደረጃ ሙስና የስርዓቱ አደጋ ነው የሚል አቋም ቢያዝም ርምጃ ለመውሰድ ማን ማንን ይደፍረዋል የሚለው መከራከሪያ ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል ወደ ሚለው ድምዳሜ አድርሷል። የአዲስ አበባ አስተዳደር ጊዚያዊ ከንቲባ የነበሩት አቶ ብርሃነ ደሬሳ “ዜጎቿ ምግብ ማግኘት ባልቻሉባት አገር ውስጥ የሚከናወነው ሙስና ስጋ ከሌለው አጥንት ላይ ስጋ ፍለጋ የመጋጥ ያህል ነው” በማለት ሙስና የደረሰበትን አስከፊ ደረጃ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Alelign says

    December 26, 2012 09:09 pm at 9:09 pm

    በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሙስና እግዚአብሔር መፍትሄ እንደሚሰጠው ልነግራችሁ እወዳለሁ፡፡ ለድሆች የምስራች እነግር ዘንድ ጌታ እግዚአበሔር ቀብቶኛል ሲል ወደ ዚህ ምድር የመጣው ኢየሡስ የድሆች ፈጣሪያቸው ስለሆነ ትልቁ የሌቦች ዋሻ የሆኑት ጲላጦስና (ኢየሡስን የገደለው) ሊቀካህን (ቀያፋ )ኢየሱስን ያስገደለው ደየአይሁድ እምነትን ለመበዝበዢያነት የተጠቀመበት ሰዎች ሲሆኑ የኢትዮጵያውን (ጲላጦስና ቀያፋ መለስና አቡነ ጳውሎስን) እግዚአብሔር በተከታታይ ከቀጣ በአንድ ወር ውስጥ ቀብራቸውን ከደመደመው 7የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ «ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ። ዘካሪ 13፡7 መፈጸም ጀምሮአል፡፡ እናየዋለን፡፡

    Reply
    • Bek says

      December 26, 2012 11:32 pm at 11:32 pm

      Amen !!!!!

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule