በሚሌ ወረዳ የሀርሲስ ቀበሌ ነዋሪዎች በድርቅ መጎዳታቸውን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ጋብሩ በአፋር ክልል ተዘዋውሮ ዘግቧል።
ነዋሪዎቹንና የአፋር ክልል የመንግስት ባለስልጣኖችንም አነጋሯል። የሞቱ እንስሳት እንዳየና በህይወት የተረፉትም በምግብና በውሀ እጥረት ምክንያት እጅግ የተዳከሙ መሆናችውን ግርማይ ገብሩ ገልጾልናል።
መንግስት በበኩሉ ምግብና ውሀ እያቀረበ መሆኑን በሰመራ የክልሉ የአደጋ ዝግጁነትና የምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ዐይሻ መሐመድ እንደገለጹ በዘገባው ጠቅሷል።
(ሰሞኑን ከውጭ የመጡ ኢትዮጵያውያንን እያግባባ ያለው ኢህአዴግ የድርቁ ጉዳይ አሳስቦታል። ድርብ አሃዝ ዕድገት እየተባለ ሲሰበክ የነበረው ሁሉ ማጣፊያው ከመጠን በላይ አጥሮዋል። “ዴሞክራሲያዊ ፍትሃዊ እና ተዓማኒ የነበረውን ምርጫ” እንዳያበላሽ የተፈራው ድርቅ አፍንግጦ ወጥቶዋል። ኢህአዴግ ቢቸግረው ድርቁን ከደርግ ድርቅ ጋር እስከማወዳደር ዘልቆዋል – ቢሳካለት!? ስለ ድርቁና ችጋሩ ምላሽ እንዲሰጡበት የተጠየቁት ሃይለማሪያም “በካሊፎርኒያም በአውስትራሊያም ድርቅ አለ” በማለት ፈጣን ድንበር ዘለል ወንዝ ተሻጋሪ መልስ ሰጥተዋል)
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ያጥናቀረውን ዘገባው እዚህ ላይ ያድምጡ።
(ምንጭ: ዘገባና ፎቶ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ግርማይ ገብሩ)
Leave a Reply