ትውልድ አምካኝ ቤቶችን፣ ትውልድ አምካኝ ደላሎችን፣ በህጻናት የወሲብ ንግድ ገንዘብ የሚሰበስቡትን፣ ማጥፋት ቀላል ነው። ግን ተጠቃሚዎቹ ህግ አስከባሪዎቹ፣ ህግ አወጪዎቹና ዋናዎቹ “የአገሪቱ ህዳሴ ባለቤቶች” የሚባሉት በመሆናቸው አይታሰብም። አንዳንድ ዝግ ቤቶች በሲቪል ጠባቂዎች የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዴ ቤተመንግስቱንና ሟቹን የቤተመንግስት ነዋሪ ይጠብቁ የነበሩት በፈረቃ ይታደሙባቸዋል። ሃኪሞች፣ የህግ ባለሙያዎች፣ አገር የሚመሩት፣ ህግ የሚያስከብሩት፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖች፣ አውራ ባለስልጣናት፣ ህዝብ ፊት ቀርበው በልማት ስም የሚምሉት ሃብታም ተብዬዎች፣ የፖሊስ የበላይ አመራሮች፣ የስለላ አውራ ሰዎች፣ አጫፋሪዎች፣ የአቻ ፓርቲ አመራሮችና መካከል ጥቂት የማይባሉ ከዳር እስከዳር መመሸጊያቸው ዝግ ቤቶች ናቸው። አንዳንዴም ከዝግ ቤቶች ፍራሽ ላይ ሆነው የፖለቲካ መመሪያ … [Read more...] about አዲስ አበባ ረክሳለች!
የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች ተቋማዊ ድክመት ወይስ የራዕይና ስትራተጂ ልዩነት?
በቀዳሚው ጹሁፌ “የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ አይዲዮሎጂካል እና ስትራተጂካዊ ሁኔታዎች” እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ05/01/2013 በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ላይ በወጣው ላይ ተመስርተው አቶ አንዱ አለም ተፈራ በፈረንጆቹ አቆጣጠር 10/01/2013 በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ላይ “የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና የእቅድ ልዩነት” ብለው ባወጡት ጹሁፍ ላይ ገንቢና አስተማሪ ሃሳቦችን ስላቀረቡ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሰዎት እላለው:: የዚህ ጹሁፍ አላማ በዋናነት በመጀመሪያ ጹሁፌ ላይ ያቀረብኩትን ሃሳብ በበለጠ የሚያብራራ ሲሆን፣ በተጨማሪም በአቶ አንዱ አለም ከተነሱት ገንቢ ሃሳቦች መካከል በበለጠ መብራራት አለባቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ጉዳዮች ለመዳሰስ ነው:: (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል) … [Read more...] about የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች ተቋማዊ ድክመት ወይስ የራዕይና ስትራተጂ ልዩነት?
ENTC expressed solidarity with hero scribe, urged policy rethink.
Expressing its solidarity with firebrand Ethiopian journalist Abebe Gelaw, the Ethiopian National Transition Council has called up on the Obama administration to rethink its policy of friendship with the terrorist legions of TPLF warlords who are holding Ethiopia in thrall. (Read more) … [Read more...] about ENTC expressed solidarity with hero scribe, urged policy rethink.
አበበ ጉዑሽን በላ
ኢሳት ጃንዋሪ 8፡2013 ላይ እንዲህ የሚል አጭር የቪዲዮ ሰበር ዜና ለጥፎ ነበር፡ “የ FBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ(።) በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።” ‘ሴረኛ’ ከተባሉት ሰዎች አንዱ አቶ ጉዑሽ አበራ ነው። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ይገኛል) … [Read more...] about አበበ ጉዑሽን በላ
TPLF and the culture of violence
According to ESAT the FBI has foiled an attempt by the Ethiopian government to assassinate Ato Abebe Gelaw. Goosh Abera and his accomplices are under custody. Please note here I said the Ethiopian government since there seems to be no thin line between the TPLF party and the government. Why am I not surprised? I am not surprised because for the TPLF violence is sanctioned by the party leaders as a legitimate tool to achieve political, economic and military dominance. The following weeks as we … [Read more...] about TPLF and the culture of violence
“በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች
አዲሷ አገር ደቡብ ሱዳን እንደ መንግሥት ተመቻችታ አልቆመችም። የፋይናንስ ስርዓቱም የተረጋጋ አይደለም። የገቢና ወጪ ቁጥጥሩ ክፍተት ያለበት በመሆኑ ለሙስና የተጋለጠ ነው። የጁባ ነዋሪዎች እንደሚሉት ከሆነ የአገሪቱ ሃብት በግለሰቦች እጅ ነው። በተለያዩ መስኮችም የባለሙያና የአቅም ችግር አገሪቱ ምስጢርና የኔ የምትለው አስተዳደር እንዳይኖራት አድርጓታል የሚሉ በርከቶች ናቸው። ይህንኑ ክፍተት ለመሙላት በሚል ኢህአዴግ ደቡብ ሱዳንን ከተወዳጀ ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። የመከላከያ መኮንኖችን አሰልጥኗል፤ የፖሊስ ኃይሉን አደራጅቷል። በአማካሪነት በተለያዩ ዘርፎች የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆ አሁንም ይህንኑ ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል። የተመሰረተው ግንኙነት ወደፊትም እንዲሁ በቀላሉ ንፋስ የሚገባው አይመስልም። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ኢህአዴግ በህወሃት አማካይነት ደቡብ … [Read more...] about “በህወሓት ተወርረናል!” ደቡብ ሱዳኖች
እስራኤል ተጨማሪ ታዳጊዎች ለቀቀች
በእስራኤል አገር ታስረው ከሚገኙት ታዳጊዎች መካከል አራቱ መፈታታቸውን አቶ ሳሙኤል አለባቸው የኢትዮጵያ እናድን አንድነት ማህበር በእስራኤል ሊቀመንበር በተለይ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አስታውቀዋል። አሁንም እስር ላይ የሚገኙት ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ አስር ታዳጊዎችን ለማስፈታት አስፈላጊው ሁሉ እየተደረገ መሆኑንንም አስታውቀዋል። አቶ ሳሙኤል በጽሁፍ በላኩት መልዕክት እንዳስታወቁት ከጎንደር አስኮብላዮች ወደ ሲና በረሃ በመውሰድ ለከፍተኛ እንግልትና ህሊናን የሚፈታተን ስቃይ ከዳረጓቸው ታዳጊዎች መካከል እስራኤል መድረስ የቻሉት እዚያ ሲደርሱ የገጠማቸው እስር ነበር። በተለይም እድሜያቸው ከአስራስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በእስር ላይ እንደሚገኙ ከታወቀ በኋላ እርሳቸው የሚመሩት ድርጅትና የወገኖቻቸው ስቃይ እረፍት የነሳቸው አገር ወዳዶች ባደረጉት ትብብር … [Read more...] about እስራኤል ተጨማሪ ታዳጊዎች ለቀቀች
ከ33ቱ የአዳማ ፔቴሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
በምርጫ አስፈፃሚው፣ ከምርጫ አስተዳደርና በምርጫው ሂደት ላይ የሚታዩ መሠረታዊ ችግሮችን በማንሣት ችግሮቹ ስለሚፈቱበት መንገድ የውይይት /ምክክር/ መድረክ እንዲመቻች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና ለመንግሥት አካላት ጥያቄአችንን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የማያሣምኑ ምክንያቶች በመስጠት ጥያቄዎቻችንን ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉን በቃል የገለፀልን ሲሆን ለመንግሥት ላቀረብነው ጥያቄ ምላሹን እየተጠባበቅን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የተጣለበትን የአገርና የሕዝብ ኃላፊነት ወደጐን በመግፋት ምርጫውን ሠላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማድረግ የመወዳደሪያ ሜዳውን ከማስተካከል ይልቅ የገዢው ፓርቲ ወገንተኝነቱንና ጉዳይ ፈፃሚነቱን ባረጋገጠበት አቋሙ በመግፋት ወደ ምርጫ እንቅስቃሴ መግባቱን በይፋ አውጇል፡፡ እኛ በያዝነው … [Read more...] about ከ33ቱ የአዳማ ፔቴሽን ፈራሚ ፓርቲዎች የተሰጠ መግለጫ
ይድረስ ለፈጣሪ!
ተጣፈ ተኔ «ወተህ ወርደህ የላብህን ወዝ ትበላለህ» ብለህ ወደ መሬት ከላከው የአዳም የልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ ልጅ፤ … አንዱ፤ ላንተ በሰማዬ ሰማያት ላለኸው አምላክ:: እነሆ ይችን ደብዳቤ በመልክተኛህ በመላኩ ገብርኤል በኩል ላንተ ስልክ፤ ካገኘህ ለራስህ በእጅህ እንዲሰጥ፤ ካጣህም ለእናትህ ለወላዲት አምላክ፤ እንዲሰጣትና እሷ እንድትሰጥህ አደራ ብዬዋለሁ:: አምላክ ሆይ ! ከጭቃ አድቦልቡለህ የፈጠርከው ሰውን ያህል ጨካኝ ፍጡር አንቱ እያልኩ፤ አንተን አንቱታ በመንፈጌ ከድፍረት እንደማትቆጥርብኝና ቁጣህ እንደማይበረታ አውቃለሁ፤ አንተታዬ የመውደዴና ላንተ ያለኝ የክበር መግለጫ መሆኑን አንተው ታውቃለህና! ይኸውልህ ጉዳዩ እንዲህ ነው: ፈጣሪ በጆሮው ላይ ተኝቶ የሕፃናትን ለቅሶ፤ የዕናቶችን ዋይታ፤ ያባቶችን ጣር፤ አልሰማ ብሏል፤ … ሕዝብ መከራው በዝቶ፤ የበደል ገፈቱ ገንፍሎ … [Read more...] about ይድረስ ለፈጣሪ!
የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና እቅድ ልዩነት
“የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች በድረ-መለስ ኢትዮጵያ፣ ርዕዩተ ዓለምና የትግል ግብና ዕቅድ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ አቶ ጋሻው ዓለሙ ጥሩ የመወያያ ሃሳብ አቅርበውልናል። ማለፊያና ብዙ የምስማማባቸውን ነጥቦች የያዘ በመሆኑ፤ ላመሰግንና ድጋፌን መስጠት እፈልጋለሁ። መቼም ብዕሬን ያነሣሁ ተስማምቻለሁ ለማለት ብቻ አይደለም። የተስማማሁባቸውን መደረቱም አንባቢን ማድከም ነው። የማቀርበው ለየት ያለ አቀራረብ ሊኖረው ይገባ ነበር ያልኳቸውን ላመላክት ነው። በመጀመሪያ ደረጃ በኔ በኩል ድክመት ሳይሆን ልዩነት ነው ያለው። በርግጥ በተለያዬ መልክና ቦታ ይኼ ጉዳይ በጽሑፉ ውስጥ ተጠቅሷል። ነገር ግን ማዕከላዊ ቦታ መያዝ የሚገባው ጉዳይ ተለጣፊ በመሆን ቀርቧል ባይ ነኝ። እንዲህ ነው። የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎችን አንድ ተግባር እንዲፈፅሙ እንፈልጋለን። ይኼም ተግባር የዘረኛውን አምባገነን የወያኔ … [Read more...] about የተቃዋሚ ፖለቲካ ኃይሎች የተግባር ድክመት ወይንስ የግብና እቅድ ልዩነት