• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሽሽት እና አባዱላ ገመዳ

October 8, 2017 04:36 pm by Editor 2 Comments

ከሰሜን እና ከበስተ-ምስራቅ አቅጣጫ እየነፈሰ ያለው አውሎንፋስ መርከብዋን እያናጋት ይገኛል።  ጫፍ ላይ ጉብ  ያሉትን አስተናጋጆች እያንጠባጠበ የሚገፋው ሃይል እየበረታ መጥቶ፣ አሁን ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ይመስላል። ይህ ሁላችንንም የሚያስማማን መራራ ሃቅ ነው። ችግሩ እዚህ ላይ አይደለም። ግን … እየሰመጠ ካለው ከዚህ መርከብ ለማምለጥ የተገኘችውን ቀዳዳ እየተጠቀሙ የሚሾልኩትን ሁሉ “ጀግና” ብለን ለመጥራት እንደምን ይዳዳን?

ራስን ማዳን እና ሃገርን ማዳን፤ በሰማይና በምድር መሃከል ያለ ርቀትን ያህል የተለያዩ ነገሮች ናቸው።

ዘንግተነው ከሆነ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ይህ ስራዓት “በስብሷል” ብሎ ከተናገረ 10 አመታት አልፈውታል። ከ 26 ዓመታት በኋላ ደግሞ እነሆ ህወሃት ከርፍቶ መርገፍ ጀመረ። ችግሮቹ ግን እጅግ እየተባባሱ እንጂ እየተሻሻሉ አልመጡም። ይህ ስርዓት ዛሬ እንደ ውሃ እና መብራት ያሉ መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጅ ፍላጎቶችን እንኳን ማሟላት ተስኖታል።  “በመለስ ግዜ በፈረቃ፣ ደብረጽዮን ግዜ በደቂቃ” እያለ ከተሜው የስርዓቱን ቁልቁል እድገት የሚነግረን ያለ ምክንያት አይደለም።

ታዲያ በዚህ ሁሉ ረጅም ጉዞ አብረው ዘልቀው፣ አብረው በልተው፣ አብረው ጠጥተው፣ አብረው ዶልተው፣ አብረው ፈስተው፣ አብረው ሰርቀው፣ አብረው ዋኝተው፣ አብረው ቀልተው፣ አብረው አርደው፣ አብረው ቀብረው … አሁን ከድተናል ሲሉ በእርግጥ “ሃገርና ሕዝብን አስበው ነው? ወይንስ ራስን ለማዳን?” ብለን መጠየቅ ግድ ይለናል። ሃገርና ሕዝብ ለ26 ዓመታት እንደ አህያ ሲረገጡ እነዚህ ሰዎች መርከብዋ ውስጥ አብረው ነበሩ። እጃቸውን ሳይጠመዘዙ ከተዳሩበት  የህወሃት የጋብቻ ትስስር በኋላ “ሰዎቹ አሜሪካ አገር ሲገቡ ውሉን ለምን አፈረሱት?” ብሎ የሚጠይቅ ብዙ አይታይም።

እናም የብርጋዴር ጀነራል መላኩ እና የአቶ ሃይለማርያም ፕሮቶኮል መኮብለል፣ “ሰበር ዜና” ብለን የምንጠራው ነገር ሊሆን አይችልም። የሰዓቱ መፍረድ እንጂ፣ የነዚህ ሰዎች ሽሽት ፈጽሞ አይጠቅምም ማለትም አይቻልም። ቢያንስ የፖለቲካ ትኩሳቱን የግለት መጠን ይነግረናል። ሰበር የምንለው ግን ጀነራል ሳሞራ የኑስ ወይንም አይቴ ደብረጽዮን ቢኮበልሉ ነበር።

ወትሮም ቤት የእግዚአብሄር፤ ቪላ ሁሉ የገብረ-እግዚአብሄር እየተባለ የሚተረትበት ሃገር፣ ባህር ማዶ ዘልቆ መጠለያ መፈለግ እንግዳ ነገር አይሆንም። ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆኑ አገልጋዮች ሁሉ እንደ ብጻይ ደሳለኝ ከባዱን የሸክም ስራ ሰርተው ሲያበቁ፤ ደከሙ እንጂ ከዱ አይባልምም። የእነዚህን ቦታ በሌሎች ተሸካሚዎች ለመሸፈን፤ የ”ጥልቅ ተሃድሶ መተካካት” እንኳ የሚያሻ አይመስለኝም። እንደሰው ሳይሆን እንደ እንሰሳ ስለሚያዩዋቸው በመሄዳቸው ቅንጣት ያህል አይበርዳቸውም፣ ቅንጣት ያህልም አይሞቃቸውም።

እኛ ግን ሳምንቱን በሁለት ሰበሮች እያሟሟቅን አሳልፈን፤ በሳምንቱ መዝጊያ ላይ ደግሞ የአባዱላ “ሰበር” ዜና ማህበራዊውን ድረ-ገጽ አጨናነቅነው። በጉዳዩ ላይ ጽዮን ግርማ በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ያቀረበችውን ዜና ልብ ብሎ ላዳመጠ፤ እዚያ ሰፈር አንድ የሚሸት ነገር እንዳለ ይገነዘባል። ከሽፈራው ሽጉጤ መርበትበት እስከ ስልክ ዘግቶ መሸሽ፣ በአንዱ አቅጣጫ የሚሰማው ነገር፣ ከሌላው ጋር መጣረዝ፣ ከስብሰባው ጋጋታ እስከሽምግልና መሯሯጥ፣ … ሁሉ የሙቀቱ መጠን መለክያዎች ናቸው። ህወሃት ለክፉ ግዜ ብሎ ያስቀመጣት የሶማልያ ጥይትም የከሸፈችበት ይመስላል። አሁን ለርዓቱ እድሜ ማራዘምያ የቀረ ነገር የለም። ሁሉም ካርዶች ተመዝዘዋል። ይህ የመጨረሻው ካርድ ግን በክሽፈት ብቻ አላበቃም፤ ይልቁንም በራሱ በስርዓቱ ላይ መዘዝ ይዞ የመጣ ነው የሚመስለው። አባዱላን ሳይቀር አዳልጦ ያስተነፈሰ መዘዝ።

አባዱላ ገመዳ ለአሜሪካ ድምጽ ራድዮ የዘጋውን በር ለዛሚዋ ሚሚ ስብሃቱ መክፈቱ በራሱ የሚጠቁመን ነገር አለ። ትላንት ክቡር፣ ዶክተር፣ ጀነራል አባ ዱላ ተብሎ ሲጠራ በነበረበት ራዲዮ ዛሬ እንደ ገላባ መቅለልን ይመርጣል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። አያሌ ከጠረጴዛ ስር የሚደረጉ ስምምነቶችን ላስተዋለ ሰው ግን  “እባብን ያየ ልጥ ይፈራል” ማለቱ አይቀርም።

እዚህ ላይ ይሰመርበት። አባዱላ ከስፍራው ለቀቀም፤ አልለቀቀም በህወሃት የፖለቲካ አሰላለፍ ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። የተባለውን ደብዳቤ እርግጥም አባዱላ ከሆነ የጻፈው፣ የህወሃት መልስ የሚሆነው፣ “ድሮም አልነበርክም፤ አሁንም የለህም!” ነው። አባዱላ የስርዓቱ ጭምብል እንጂ ምሰሶ እንዳይደለ ቄሮም ቢሆን ያውቃል። ይልቁንም ይህ የስንብት ማስታወሻ፣ ኦነግ “ከሽግግሩ መንግስት ራሴን አግልያለው” ሲል ያወጣውን መግለጫ ያስታውሰናል። 20 ሺህ የኦነግ ሰራዊት፣ በጦር ካምፕ ውስጥ እንዲታጎር ካደረጉ በኋላ ነበር እነ ሌንጮ ለታ መግለጫውን የሰጡት። ህወሃቶች በክስተቱ ፈጽሞ አልተደናገጡም ነበር። ራስን በራስ የመግደል ያህል ለፈጸሙት ለዚያ ጅላጅል ውሳኔያቸው፣ አገዛዙን ጮቤ አስረገጠው እንጂ አላበሳጨውም። በቦሌ በኩል እንዲሸኙ ተደረገ እንጂ ፤ በፈቃዳቸው አቅመቢስ በሆኑት በእነ ሌንጮ ላይ እጃቸውን አላነሱም ነበር።

ቄሮ ግን የቅርቡ እልቂት እንኳን ረስቶት፣ የአባዱላን ጀብድ ማውራት ጀመረ። የአባዱላ ከህወሃት መፋታት እኮ ብርቅ ነገር አይደለም። ከዚህ ቀደም ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ታፋትተዋል፣ ጀነራል ባጫ ደበሌም ገለል ተደርገዋል፣ ሃሰን አሊ ተሰድዷል፣ አልማዝ መኮ እና ጁነዲን ሳዶም ወደ አውሮፓና አሜሪካ አምልጠዋል። አንዱ ሲሄድ ሌላው ሲተካ እነሆ ኦህዴድዳቸው ሳይሸረፍና ሳይቀነስ ቀጥሏል። ምክንያቱም ኦህዴድን ጠፍጥፎ የፈጠረው ህወሃት መሆኑን ሁሉም በሚገባ ያውቀዋል። ኦህዴድን የሚያኖረውም፣ የሚያቆየውም ሆነ የሚያጠፋው፣  አባዱላ ሳይሆን ህወሃት ነው።

የመልቀቅያ ደብዳቤ የማስገባቱ ትርክት በህወሃት ቀጭን ትእዛዝ ነው የሚሉ ወገኖች የሚያቀርቡት ምልከታም ሆነ መላ ምት ውሃ የሚቋጥረውም ከዚህ የተነሳ ነው። በአውሬ ጥርስ ውስጥ ሆኖ አውሬውን መተናኮስ የሚሻ ካለ፤ ይህ ጅል ብቻ ነው። አባዱላ ደግሞ እጆቹም ሆኑ እግሮቹ መስና ውስጥ የተዘፈቁበት ሰው ነው። ወያኔ ይህንን ሰው ሸቤ ለማስገባት አንድ ሚሊዮን ፋይሎችን መምዘዝ እንደሚችል ይታወቃል። “አፍ ስላበዛህ በገዛ ፍቃድህ ልቀቅ!” መባሉ አዲስ ነገር አይሆንም። ቀይ መስመር ሊያልፍ ይችላል ተብለው ለሚጠረጠሩ “ሹሞች” አስቀድሞ የተዘጋጁ የወንጀል ፋይሎች አሉ።

የአባዱላ መልቀቅያ ደብዳቤ ግማሽ እውነት ነው። ግማሽ እውነት ማለት ደግሞ ሙሉ ውሸት ነው። የሚደንቀው ይህ ሳይሆን የዲያስፖራው ጭብጨባ ነው። ልክ እንደ ቤተሰብ ጨዋታ፤ ጥያቄያቸውን በትክክል ሲመልሱ ይጨበጨባል፣ ሲሳሳቱም ይጨበጨባል። አባዱላ የቀድሞ ሰራዊት ምርኮኛ  መሆኑን ለአፍታ እንኳን ብናስታውስ፣ ከዚህ የተሳሳተ ግምታችን እንታረም ይሆናል።

ዝቅ ብለው እንዲበሩ ተነግሯቸው የነበሩ “ባለስልጣናት” ጉዳይ እንግዳ ነገር አይደለም። እነዚህን ሰዎች አስቀድመው ስኳር የሚያልሱዋቸው፣ ከህወሃት ራዳር እንዳይወጡ ለማድረግ ብቻ ነው። ከፍ ብለው ለመብረር ከሞከሩ ውርድ ከራስ ይሆንና ቀሪው አማራጭ እጅ መስጠት ይሆናል።

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    October 9, 2017 06:36 pm at 6:36 pm

    ___ አባ ዱላ ትርጉሙ ባይገባኝም “ዱላ ከእጃቸው የማይጠፋ ሽማግሌ አባት ይመስለኝ ነበር። እኝህ ሰው ለዲሞከራሲ ብሔርተኝነት ሲባል የቀድሞው ደርግ ወታደር ምርኮኛ ምናሴ ተክለሃይማኖት በኋላ አባዱላ ገመዳ በጦር ጄኔራልነት ተሾመው የነበሩና በህወሃት ክፍፍል ወቅት ከውትድርናው ተነስተው የኦሮሚያ ፕሬዚዳትነት የተሾሙ ሲሆን፡ ሰውዬው በፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በአቶ መለስ ባለመወደድ ከኦሮሚያ ፕሬዚዳንትነት እንዲነሱ ተደርገው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው የተሾሙ ናቸው።…
    አፈጉባኤ ማለት ፬፶፬ አባላት የተከበሩ ተብሎ በቀጭን ትዕዛዝ የተቀበሩ ለማለት ነው አደለም እንዴ?
    **ፈንቀሎ ያስወጣቸው የራሳቸው ጉዳይ እስኪመጣ ሕዝቤ እንዲህ ሲል ይቆዝማል። ለቀቁ..በረጅም ገመድ ታስረው ተለቀቁ ? በብቃት ማነስ ወደ ክልል ወረዱ? ኅይለመለስም ፓርቲዬ ከፈለገ ወረዳ እሄዳለሁ አላለምን? በግርግሩ ወቅት “ቤተመንግስት በር ላይ ደርሰናል!” ያሉት በፓርቲያቸው ስም ምንም ዓይነት መግለጫ እንዳይሰጡ፣ ከቤት እንዳይወጡና ሥራ እንዳይሠሩ ከተደረጉ ፩ዓመት ከ፱ ወር እንደተቆጠረ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ“ታፍኜ እቤት ውስጥ እንድቀመጥ ከተደረኩ በኋላ ተረስቻለሁ”–አሉ የአባ ዱላ አይሻሉም!? ህወሓት ውለታ አክባሪነቱን የኦነግ መሪዎች ለቅሶና ለፓርቲ ምሥረታ እንዲገቡ እንዲወጡ ማድረጉ ያስመሠግነዋል።
    ፩) አፈ ጉባኤው አባዱላ ገመዳ በኦሕዴድ ውስጥ በገነቡት ፈርጣም ኅይል በመተማመን እና የህወሓትን ኅይል መዳከም በማየት በምስራቅ ኢትዮጵያ ከ፻ሺህ በላይ የኦሮሚያ ተወላጆች ተፈናቃይ የሆኑበትን የሶማሌ ግጭትን በውጭ ሆነው ለመምራት ከማሰብ የመነጭ ነው ሲሉ…
    ፪) ምክንያት ደግሞ ገዢው የህወሓት ኅይል በስራ መልቀቅ ስም የተበላሸውን የኦሕዴድ ስራን እንዲያጸዱለት ለማመቻቸት ነው ተብሎ ተግምቷል።
    ፫) ለኢህአዴግ ታማኝነታቸውን ያክል ግጭትና ፌደራላዊ በዓላት ባሉበት ሁሉ እንደሚላላኩትን ያህል ወደ ዲያስፖራ ጽንፈኛ ብሔርተኞች አቅንተው በህወሓት ላይ ምንም ተቃወሞ እንዳያሰሙ ምን ይደረገላችሁ? ሲሉ ለህወሓት ይዘው የመጡትን የአዲስ አበባ ከተማ አለመስፋፋት!፡ የፊንፊነ የኦሮሚያ ናት!..ኦሮሚኛ የፌደራል ተደራቢ የሥራ ቋንቋ ይሁን! ጥያቄዎች ነበሩ የተሳካም የተሰኩበትም እንዳለ የፖለቲካው ተንታኝ አብሮ እንደሚሰራ መስከሯል። አባዱላ ለቀቀ ማለት ፌደራሉ ፈረሰ የሚሉም አድናቂዎች በዝተዋል። ያ ማለት እንደበቀለ ገለባና መራራ ጉዲና መሰከሩበት እንጂ አላስተባበሉለትም። ኦሚኔ (ኦርሞ ሚዲያ ኔትዎርክ) በኣባዱላ ተጠልፏል ሲል የአብዲ ፊጤን ፎቶ ከአባዱላ አያይዞ የመሠከረው የዲሲ ኦሮሞ ዜግነት ያለው ተስፋዬ ግብረእባብ(ገዳ) ነበር።

    ** የዚህ ሰሞን የከጅዎች ቁጥር መበራከት ተዓምር አደለም! “እየሰደቡ፡ እየተፉብኝ፡ ውስጥ ውስጡን በሲቪል ሰርቪስ ብዙ ነገር ሠርቻለሁ (ሰርስሬአለሁ) ያለው ጁነዲን ሰዶ ኦህዴድ ውስጥ ድሮም አሁንም ማንም ምንም እንዳለሆነ ሲናገር፡ ለማ መገርሳን ዲሞክራሲ መኖሩን እራሱን በራሱ እንደሚመራ አስለፈለፉት በአፉ ልክ ፻፶ ሺህ ኦሮሞ ከሰው ሰፈር አፈናቀለና ጭራሽ የደርግ ሥርዓት ናፋቂ ተባለና አረፈው!። አብዲ ኢሌ የኦህዴድን የምርኮ አፈጣጠራቸውን ያውቀዋላ!!
    ይህ ከዳ፡ ወጣ፡ ገባ፡ የሚባል የተሰባበረ ዜና ኢህአዴግን የከዱ ከተራ ሠራተኛ፡የፓርቲ አባል፡የሰፈር ልጅ፡ መምህር፡ካደሬ፡ ዳኛ፡ ሳይቀር ያንኑ የህወሓትን ማኒፌስቶ(ሕገመንግስት) ከማቀንቀን ሌላ የሚሰሩት አለን?ይልቁንም እኛ ብንሆን መገነጣጠልን እናፈጥነው ነበር ሲሉ ይሰማሉ። ድንቄም ታጋይ!
    ” መለስ ኖር አልኖረ..ፋጡማ ኖረች አልኖረች…ዘርይሁን ኖረ አልኖረ…ኢህአዴግ በጸና መሠረት ላይ ቆሟል”የነፍስ አባታቸው ስብሃት ነጋ ታዲያ አባዱላ ፓርላማ ኖረ አልኖረ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ቤተመንግስት ተገኘ አልተገኘ… አዜብ ቤት አላት የላትም የትግራይ እንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ በፀና የህወሓት ቤተሰባዊ የወሮ በላ ቡድን ቁጥጥር ሥር ውሏል።አዳሜ ሰባራ ሸክላ ይቆጥራል ልበል!?

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    October 11, 2017 02:59 am at 2:59 am

    ጓጉጠህ አናግረን!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule