እግዚአብሔር ዓይንን ፈጠረና እዩበት አለ፤
እግዚአብሔር ጆሮን ፈጠረና ስሙበት አለ፤
እግዚአብሔር አእምሮን ፈጠረና አስቡበት አለ፤
እግዚአብሔር አንደበትን ፈጠረና ተናገሩበት አለ፤
ወያኔ አይሆንም አለ!
በዓይንህ አትይ፤
በጆሮህ አትስማ፤
በአእምሮህ አታስብ፤
በአንደበትህ አትናገር፤
አበሻ ተዋረደ!
ዓለም እየሰማ ድንቁርና ታወጀበት!
ማን ያሸንፋል?
እግዚአብሔር አለ፤
ወይስ ወያኔ አለ?
(ምንጭ: Prof. Mesfin Wolde-Mariam Blog)
ጌታቸው፡ወልደሥላሴ says
የወያኔ፡ንጉሥ፡ዲያቢሎስ፡አለ።
እሱንም፡ያሸነፈ፡የእመቤታን፡ልጅ፡ክርስቶስ፡ብቻ፡ነው።
አማላጃችንን፡ከከዳን፡ፊቷን፡ወደ፡እኛ፡አታዞርልንም።