የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about በንጹሀን ዜጎች ላይ የሚፈጽመው ጭፍጨፋ ይቁም!!
Opinions
የኔ ሃሳብ
“የምትሰሙ ከሆነ ነጻ አወጣዋለሁ ለምትሉት ሕዝብ ይጠቅማል!”
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ የዛሬ ሁለት ዓመት መስከረም 14፤2007ዓም ለህወሃት ሊቀመንበር በግል እና ለህወሃት መሪዎች በጋራ እንዲሁም ለትግራይ ተወላጆች በወቅቱ ወደ ዕርቅ ሊያመጣ የሚችል ደብዳቤ ልከው ነበር፡፡ ይህንን መልዕክት ደግመን ልናትም ስናስብ ምላሽ አግኝተው እንደሆነ ለጠየቅናቸው "ለደብዳቤዬ ከህወሃት በኩል ምላሽ አላገኘሁም" በማለት ለጎልጉል ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ደብዳቤው ግልባጭ የተደረገላቸው መንግሥታት፤ ድርጅቶችና እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሚዲያ መረጃውን መዝግበው ይዘውታል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ "የዘር ማጥፋት አደጋው የተጠነሰሰው በራሳችሁ ነው፤ የምትሰሙ ከሆነ ነጻ አወጣዋለሁ ለምትሉት ሕዝብ ይጠቅማል!" በማለት የድርጅታቸውን (አኢጋን) አቋም በድጋሚ አሰምተዋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት ኦባንግ ከአብርሃ በላይ … [Read more...] about “የምትሰሙ ከሆነ ነጻ አወጣዋለሁ ለምትሉት ሕዝብ ይጠቅማል!”
ቢወሳሰብም መፍትሔው ቀላል ነው
የአገር ጉዳይ ለጥቂቶች የሚተው አይደለም፤ አያገባህም ሊል ወይም ሊባል የሚገባው ዜጋ የለም። እያንዳንዱ በቻለው መጠን አሳቡን ማካፈልና ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር መትጋት አለበት። መንግሥት የሕዝቡ አካልና አገልጋይ እንደመሆኑ ዜጎች ተሳትፎአቸው እንዳይገታ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ግዴታው ነው። አሁን የሚታየው አዝማሚያ እጅግ አሳሳቢ ነው። ሕዝብና መንግሥት፣ ሕዝብና ሕዝብ፣ መሪዎች ተፈራርተዋል። መተማመን አቅቷቸዋል። አይመለከተኝም ማለት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። የተለያየ ዓላማ ያነገቡ ቡድኖች ከየአቅጣጫው መንቀሳቀሳቸው ነገሮችን አወሳስቦአቸዋል። እነዚሁ ቀጥተኛ ዓላማቸውን ማስረዳት ሆነ እርስ በርስ መስማማት አልቻሉም። አንዳንዶችም ሁሉን ጠርገን አስወግደን አዲስ አሠራር እንመሠርታለን የሚሉ ናቸው። በስድሳ ስድስት እና በሰማንያ ሦስት ማግሥት ያየነውን ስንፍና መድገም ብቻ ሳይሆን … [Read more...] about ቢወሳሰብም መፍትሔው ቀላል ነው
ለመላው የዐማራ ልጅ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ጉዳዩ፦ የመጭውን ዘመን መለወጫ (መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም.) በፈንጠዝያ ሳይሆን፤ ዕለቱን በመሪር ሐዘንና በቁጭት አስቦ ስለመዋል። ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ፣ በዐማራው ወገናችን ላይ ከፋሽስት ጣሊያን በከፋ መልኩ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ሲፈጽም እነሆ 41ኛ ዓመቱን አገባድዶ በ42ኛው ላይ ይገኛል። በተለይም ካለፈው ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የጅምላ የጥፋት ዘመቻ አውጇል። የአገዛዙ የኅልውና መሠረት የሆነው ነፍሰ በላው የአጋዚ ሠራዊት ዕድሜና ፆታ ሳይለይ፥ ሕፃናትን፣ ወጣቶችን፣ አዛውንትን፣ ጎልማሶችን፣ ወንዶችና ሴቶችን ቤት ለቤት እያደነ እጅግ መርዘኛ በሆነ ጥይት እየደበደበ የዘር ፍጅት እያደረሰ ነው። የትግሬ-ወያኔ በከፈተው በዚህ ዐማራን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዘመቻ፣ በሺህዎች የሚቆጠሩ እህት ወንድሞቻችን … [Read more...] about ለመላው የዐማራ ልጅ የተሰጠ ማሳሰቢያ
ይድረስ ለብአዴን አባላት
ወያኔዎች “ሕዝቡን አረጋጉ፤ ሰላም ፍጠሩ” ወዘተ. እያሉ ቁም ስቅላችሁን እያበሏችሁ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ እናንተም እኛም አሳምረን እንደምናውቀው ግን የሕዝባችን ሰላም ያደፈረሰው ራሱ ወሮበላው የወያኔ ቡድን ነው፡፡ በሕዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት አውጆ ንጹሐንን የሚፈጀው፣ እንቡጥ ሕጻናትን የሚጨርሰው፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ የአማራ ወጣቶችን በየእስር ቤቱ አጉሮ ዘግናኝ ቶርቼር የሚፈጽመው፣ በርካታ ንጹሐን አማሮችን ከረሸነ በኋላ የወልቃይት ጠገዴን ጉዳይ ሁለቱ ክልሎች ተወያይተው ይፈቱታል እያለ በደማችን ላይ የሚቀልደው፣ የሰላም ጉባኤ እያለ እየሰበሰበ በብሶት የሚናገሩትን ወገኖቻችንን እየነጠለ የሚያስረው ወዘተ ወዘተ ራሱ ነብሰ ገዳዩ ወያኔ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ ሕዝባችን ሰላም ወዳድ ነው፡፡ የሰላም ጠንቅ፣ የሽብርና የሁከት አባት ወያኔ ነው፡፡ ስለሆነም ሰላም … [Read more...] about ይድረስ ለብአዴን አባላት
ETHIOPIA AT THE CROSSROADS – Win-Win or Zero-Sum?
Ethiopia is in crisis.The country is experiencing widespread civil disobedience manifesting itself in demonstrations, strikes, boycotts and in some cases armed resistances. Under the current federal arrangement, Oromia and Amhara regional states are the two largest parts of the federation, constituting 30 and 18 million population, respectively.That is close to half of the country's population.Based on news reports from inside and outside sources, in almost all parts of these two largest … [Read more...] about ETHIOPIA AT THE CROSSROADS – Win-Win or Zero-Sum?
ኳሷ ያለችው በታጋዩ ሕዝብ እጅ ነው።
የትግሬዎች ነፃአውጪ ግንባር በዘገምታ የመቃብር ጉዞውን ጀምሯል። ሕዝቡ በያለበት ትግሉን አጧጡፏል። የውጭ መንግሥታትም ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸውን ወገን ለመለየት ጎራ ይዘው እያዳመጡነው። በግብግቡ ብዙ ወገናችን እያለቀ ነው። ይህ ሆነ ያ፤ አሁን ባለንበት የፖለቲካ ሀቅ፤ ኳሷ ያለችው በታጋዩ ሕዝብ እጅ ነው። የትግሬዎች ነፃአውጪ ግንባር፤ በመላ ሀገሪቱ መግዛት አቅቶት፤ ሀገራችን ያለ መሪ ልትሆን አንድ ሐሙስ ቀርቷታል። በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል፤ ሕዝቡ ካሁን በኋላ በዚህ ዘረኛ ግንባር ሥር አልኖርም ብሎ አምጿል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ኳሷ ያለችው በታጋዩ ሕዝብ እጅ ነው።
AHRE urges Ethiopia to end use of lethal and excessive force against civilians
The Association of Human Rights in Ethiopia (AHRE) expresses deep concern over the Ethiopian Government’s continued use of force against protesters in both Amhara and Oromia region. AHRE calls on the Ethiopian authorities to immediately stop the use of excessive, unnecessary and lethal force by security forces against protesters in these regions and elsewhere in Ethiopia. AHRE also calls for the immediate and unconditional release of journalists, human rights defenders, political opposition … [Read more...] about AHRE urges Ethiopia to end use of lethal and excessive force against civilians
The struggle toward freedom reached its tipping point?!
When I heard that EPRDF’s Executive Committee held an extraordinary meeting that aimed at addressing the current stalemate, I had mixed feelings. In one hand, I thought for a brief moment, the party may carryout a genuine introspection, assess the situation objectively;most importantly, read the writing on the wall, and respond accordingly. On the other hand, knowing TPLF for more than two decades, I expected some dramas too. Well, they didn’t disappoint! Rather than admitting mistakes, taking … [Read more...] about The struggle toward freedom reached its tipping point?!
የቂሊንጦ ወኅኒ ቤት ቃጠሎ ጉዳይ…
በምርጫ 1997 ማግስት የአደባባይ አመፆች ተበራክተው ነበር፡፡ በጥቅምት 24፣ 1998 አዲስ አበባ በሕዝባዊ አመፅ ስትናወጥ፣ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥም ሊሰጠው ይገባው የነበረውን ያክል ትኩረት ሳያገኝ ያለፈ ትራጄዲ ተከስቶ ነበር፡፡ በወቅቱ እልፍ በኦ.ነ.ግ. ሥም ተወንጅለው የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች የቃሊቲ ግቢ ውስጥ ታጉረው ነበር፡፡ ታዲያ ግቢው ውስጥ በተፈጠረው ግርግር ‹ሊያመልጡ ሞክረዋል› በሚል 163 የሚደርሱ ታራሚዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸውን አጥተው ነበር፤ መንግሥት የሟቾቹ ቁጥር ዐሥር እንኳን እንደሚሞላ አላመነም ነበር፡፡ ‹ሻዕቢያ› በቂሊንጦ እና ቃሊቲ ወኅኒ ቤቶች እጅግ ዝነኛ ሥም ነው፡፡ ‹ሻዕቢያ› በሚባል ቅፅል ሥም የሚጠራው የዋርድያዎች ኃላፊ፣ በቂሊንጦ የሚገኙ ተመላላሽ እስረኞች በፍርሐት ይርዱለታል፡፡ ‹ሻዕቢያ› ከ1998ቱ የቃሊቲ እስረኞች እልቂት ጋር … [Read more...] about የቂሊንጦ ወኅኒ ቤት ቃጠሎ ጉዳይ…










