ዐማራው ከ1972 እስከ 2008 ዓም ባሉት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ወያኔ በጠላትነት ተፈርጆ ከፍተኛ የሆነ የዘር ጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበት መሆኑን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባለፉት አራት ዓመታት ተከታታይ መግለጫዎችን ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በአጠቃላይ በወያኔ የዘር አገዛዝ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ ተደርጓል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ከዐማራው የጸዱ አካባቢዎችን ለመፍጠርና ዐማራውን አሰቃይቶ፣ አደህይቶና ከሰው በታች አድርጎ ተዋራጅ ለማድረግ ሀብት ንበረታቸውን በመንጠቅ ተባረዋል። አያሌዎች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል። በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እንዲሰደዱ ተደርጓል። (ፎቶዎቹንና ዘገባውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply