• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደ ማርያም

February 5, 2017 11:32 pm by Editor 9 Comments

አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደ እንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር፤ በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር! እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው የጥቁር ድንጋይ ኮረት ላይ፣ ድቅድቂቱ ደግሞ የእኔን ራስ ጨፍልቆ! ምኒልክ ሀኪም ቤት ከስንት ቀኖች በኋላ የካቶሊክ መነኮሳት አስታማሚዎች ከነመለዮአቸው አልጋዬ አጠገብ ቆመው በትልቅ የበሽተኞች ድንኳን ውስጥ በአንዱ መደዳ ውስጥ ተኝቼ ነቃሁ፤ መድኃኔ ዓለም ማንን ልኮ የእኔን ጭንቅላት ከድንጋዩና ከድቅድቂቱ መክቶ እንዳዳነኝ አላውቅም፡፡

ሁለተኛ ከሶደሬ መውጫ ላይ በመቶ ሰባ ኪሜ የሚሽከረከር መኪና ተገልብጦ ከመኪናው በጣራው በርሬ ወጥቼ የጥቁር ድንጋይ ሰፈር በሆነበት አሸዋ ተነጥፎልኝ ሳልፈነከት በጭንቅላቴ አረፍሁና በጸጉሬ አሸዋ አፍሼ ተነሣሁ።

ሦስተኛ በፓሪስ በአንድ ዓለም-አቀፍ ስብስባ ላይ የተጠናወተኝ ሕመም እስከሎንዶን ተከትሎኝ፣ ወደአዲስ አበባ ለመመለስ አንድ ወዳጄ አውሮጵላን ጣቢያ ወሰደኝ፤ እኔ ከሆቴል ከወጣሁ በኋላ ምንም የማስታውሰው ነገር የለኝም፤ ጻዕረ ሞት እያለሳለሰ ይዞኝ በመሄድ ላይ ነበረ፤ በሦሰተኛው ቀን በሆስፒታል ውስጥ ነቃሁ፤ አሥራ ሦስት ቀን በሀኪም ቤት ስታከም ቀይቼ ወጣሁ፡፡

አራተኛ በቃሊቲ የወያኔ እስረኛ ሆኜ ጻዕረ ሞት ጎበኘኝ፤ ደበበ እሸቱ ደረሰበትና በወያኔ መልካም ፈቃድ በላንድሮቨር ወደፖሊስ ሆስፒታል ዶ/ር ሰይፉ ተረከበኝ፤ ለሦስት ቀናት ያህል ራሴን አላውቅም ነበር፡፡

አምስተኛ ተወልጄ ያደግሁበት አዲስ አበባ በድንገት ላንተ አይሆንም የተባለ ይመስል ኦክሲጄን እያነሰብኝ ትንፋሽ ያጥረኝ ጀመረ፤ አዋሳ ሄጄ አንድ ወር ያህል በሰላም ቆየሁ፤ ከዚያ በኋላ አገሩ ሁሉ በፉከራ፣ በጭስና በእሳት ታፈነና በአገሬ መሄጃ አጣሁና ወደህንድ መጣሁ፤ ለአሥር ቀናት ያህል ሰላም አገኘሁ፤ ከዚያ ጻዕረ ሞት ተቆጥቶ መጣ! እጄንና እግሬን ይዞኝ ታገልን! የእውነት ትግል ነበር፤ የሆቴሉን ስልክ አንሥቼ እያቃሳትሁ ወደሀኪም ቤት የሚወስደኝን መኪና (አምቡላንስ) እንዲያስመጡልኝ ጮህኩኝ! ኦክሲጅንና ሌላም ነገር እያማጉኝ በዚያ ሰውና መኪና፣ ድቅድቂት እየተጋፋ እየተዳፋ በሚሄድበት መንገድ ለረጅም ጊዜ እየተንገጫገጭሁ ተጓዝሁ፤ ነፍስ ውጪ-ነፍስ-ግቢ ክፍል አስገቡኝ፤ ጻዕረ-ሞት ተናድዶ እየዛተ ጥሎኝ ሄደ፡፡

እሱም አይቀር! እኔም ማምለጫ የለኝ!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ጥር/ 2009

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    February 8, 2017 06:04 am at 6:04 am

    Mesfin!!! Sira leseriw ishok latariw!!!

    Reply
    • Alem says

      February 9, 2017 05:42 pm at 5:42 pm

      Gashe Mesfin? Professor Mesfin?

      Reply
  2. Lusif says

    February 8, 2017 06:20 pm at 6:20 pm

    Oh, poor professor. Your encounter and story tells me one important aspect of life. I am a 40 yrs old person. I drive a transportation vehicle for a living. I had several life threatening accidents and several body injuries. When Doctors, relatives and friends thought the next accident was my last, it proved to be another accident, another day. Every time I was in an accident and in a hospital, besides the doctors effort and help, I was struggling to survive in my own way. I was successful all the time, still alive, strong and sound.
    We all are survivalist. Few individuals have that instinct. You are one of. Congratulations and many more years.

    Reply
  3. Eunetu Yeneger says

    February 9, 2017 03:31 pm at 3:31 pm

    ፕ/ር መስፍን የሚሰሙኝ ከሆነ አንድ በመማር ብቻ ሊገኝ የማይችል የገባኝን የሕይወት ሚስጢር ላካፍልዎት፡

    1)ዓመታትን ከኩነኔ/ከፍዳ ዓመት ወደ ዓመተ ምህረት የቀየረው የጌቶች ጌታ ‘ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህስ የት አለ’ በማለት በመስቀል ላይ የተሸነፈ ጣእረ ሞት እንዴት እየተከታተለ እንዲጫወትብዎ ፈቀዱለት?
    2)ምናልባት በ1፡18_25 ያለውን ቃል እንዳይረዱት ጆግራፊውና የዚህ ዓለሙ ፍልስፍና ከልክልዎት ይሆንን?
    3)ሌባው /ጣረ ሞት/ ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም!እርስዎ መድሃኒዓለም ያሉት የእግ/ር ልጅ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ግን፡ እኔ ሕይወት እንዲሆንላችው እንዲበዛላቸውም መጣሁ!/ዮሃንስ 10፡10/
    4)ስለዚህ፡ ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም /1ኛ ዮሃንስ 5፡12/ ስለሚል ጸሐይ ሳትጠልቅ በሃጢአት ምክንያት ለወደቀ የሰው ዘር ሲል በመስቀል ላይ የሁላችንንም የሀጢአት ዋጋ የከፈለውን /ዮሃ 3፡14 እስከ 18/ ጌታ ኢየሱስን /በ1ኛ ዮሃ 1፡8 እስከ 10/እና በዮሃ 1፡11 እስከ 13 ባለው ቃል መሰረት በመቀበል መንፈስዎን፣ ነፍስዎንና ሥጋዎን ያለነቀፋ እንዲጠበቁ ቢያደርጉ ትርፍ እንጂ ክስረት ፈጽሞ አያገኝዎትምና አሁኑኑ ጨክነው እንዲወስኑ ከሰማይ በተላከልን ፍቅር እንደ ባህላችን ዝቅ ብየ በፍጹም ትህትና ሁሉን ቻይ በሆነው በአባቶቻችን አምላክ ስም በአክብሮት ሳይመስ እለምንዎታለሁ???እስቲ፡ ‘ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም’ የሚሏት የተለመደች ምክርዎን ዛሬ፡ ከሞት ባሻገር በትንሳኤ የዘላለም ጽድቅ/ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም የጠፋውን ፍለጋ በማርያም በኩል ሥጋ ለብሶ የመጣውን አዳኝ ቆም ብለው በመቀበልዎ የሚያያገኙት ጥቅም እንዳይቀርብዎት ከማድረግ ባሻገር በመወሰንዎ የሚያጡት ምንም ነገር የለምና የአእምሮ/የፊደል ብልህ ብቻ ሳይሆኑ እባክዎት የመንፈስም ብልህ ይሁኑ??? በጣም ስለምወድዎትና ስለማከብርዎት ነው በሰው የማይደፈር የሚመስለውን የደፈርኩት! ደግሞስ ያበደን ነቢ በአህያ የሰው ቋንቋ ተናግሮ የመለሰ አምላከ እስራኤል በእዚህ ቀላል በሚመስል ነገር እየተገረዎት ቢሆንስ ማን ያውቃል???ስለዚህ በጊዜ መዘጋጀቱን እባክዎት አይርሱ? መጽሐፍ ቅዱሱን ለምርምር ብቻ ሳይሆን ለሕዎት ጭምር ቢያነቡት ደግሞ መልካም ነው::
    መልካም የሕይወት ውሳኔ ይሁንልዎት
    ጣረሞትን በመስቀል ሞት የገለው
    የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም
    አጋንንቶች ሁሉ ማንነቱን አውቀው
    የሚንቀጠቀጡለት መሆኑን አንርሳ???

    በእውነት መድሃኒዓለም በዚህ
    በመጨረሻ ዘመን ማስተዋልን ይስጥዎትና
    አምልጠው በአካባቢዎ ያሉትን እንዲያስመልጡ ጸሎቴ ነው!

    ቸሩ በቸርነቱ ለሁላችንይድረስልን

    አክባሪዎ
    እውነቱ ይነገር

    Reply
    • Yihuna says

      February 10, 2017 09:34 pm at 9:34 pm

      abet andand sew yalew yenegeroch aredad aytal new. sile yesiga mot ena yezelalem mot liyunet enquan saygebah sebaki lemohon tenesah mejemeria ye professor tsihuf yigbah. sile emnetachew hunetam ewiket yinurih. Do you have a clear understanding about ጻዕረ ሞት first? he is talking about a potential life and death incident which could happen to any human being in our daily life. tikis mederder kumneger new bante bet.

      Reply
  4. Eunetu Yeneger says

    February 9, 2017 05:47 pm at 5:47 pm

    እርማት፡

    2)በ1ኛ ቆሮ 1፡18 እሰከ 25
    መስመር 11 ላይ ሳይመስ = ሳይመሽ እለምንዎታለሁ???
    መስመር 16 ላይ እየተነገረዎት = እየተናገረዎት ቢሆንስ…..

    አመሰግናለሁ

    Reply
  5. Yihuna says

    February 10, 2017 09:44 pm at 9:44 pm

    It probably is our prayer professor, ewinet tenagari hager wedad abatochachinin tebikinil yeminilew. Emama Ethiopian ena Tariquan wedad tiwilid eyekeretsu endinoru Rejim edme ketene gar yistot professor.

    Reply
  6. Eunetu Yeneger says

    February 11, 2017 11:08 am at 11:08 am

    የተከበሩ ይሁና!(Yihuna)
    ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንዴት ሰነበቱ?እኔ ስለ ሃገሬ ከምሰማቸው ጥሩ ያልሆኑ ወሬዎች በስተቀር በመጠኑ ደህና ነኝ!

    አዎ በእኔ ቤት!እስከገባኝ ድረስ የአምላክ ቃል/ኢየሱስ ክርስቶስ/ እንዲጠቀስ የማይፈልግ የወንጌል/ሮሜ 1፡ 1 እስከ 5/ ጠላት የሆነው ሰይጣንና ፈረሶቹ ናቸውና ሚናን መለየት የሚያስፈልግ መሰለኝ፤ ቃሉን ማጥናት ደግሞ ጥቅሙ አንደበትን የባለጌ ቃላት ከመናገር ይገራልና በጎው በጎውን እያሰብን በማድረግ ብንኖረው አይሻልም??? ፕ/ርን በተመለከተ የማከብራቸውና የምወዳቸው ለራሳቸው ሳይሆን ለሃገርና ለወገን የኖሩና የሚኖሩ ብርቅየ የሰባዊ መብት ጠበቃ በመሆናቸው ሌላ ጠበቃ ፈጽሞ እንዳማይፈልጉ ላረጋግጥልዎ እወዳለሁ!!! /በሞቴና አፈረ ስሆን ትራስ ላይ ያለውን መጽሃፍ ቅዱስ አሁኑኑ አንስተው ፊልጵስዩስ 4፡8 እና 9 ያንብቡ/ ቸሩ በቸርነቱ ይጠብቀን!ከገባዎት ብቻ አሜን ይበሉ!!!

    አሁንም

    እውነቱ ይነገር ነኝ

    Reply
  7. Mulugeta Andargie says

    February 15, 2017 01:26 am at 1:26 am

    Guys!!! Professor Mesfin W/Mariam doesn’t want to die with respect and dignity. It is a great pride to him and to his family. His time was not good to our people. And couldn’t,wouldn’t come back!!! Die with respect!!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule