ኦሮሚያ ካለቀሰች በኋላ – ህዝብ ሃሳቡን ሊጠየቅ ነው

የኢህአዴግ ቴሌቪዥን የቅስቀሳ ዘመቻ ጀመረ

በአምቦ ህዝብ አዝኗል። የሟቾች ቁጥር ከ22 በላይ እንደሆነ ይገመታል። በድፍን ኦሮሚያ ከ36 ሰዎች በላይ ተገድለዋል የሚሉ መረጃዎች አሉ። ኢህአዴግ ባወጣው መግለጫ 11 ሰዎች መሞታቸውን አምኗል። ታዛቢዎች እንደሚሉት ኦሮሚያ እያነባች ነው። ህዝብ ለቅሶ ከተቀመጠ በኋላ ኢህአዴግ በቴሌቪዥን ቅስቀሳ ጀመረ።

አርብ ሚያዚያ 24፤2006 (2/05/2014) ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ባሰራጩት መረጃ በጉዳዩ ዙሪያ ህዝብ ሃሳቡን እንደሚጠየቅ አመላክተዋል። የዚሁ መነሻ እንደሆነ የተነገረለት የቅስቀሳ ዘመቻ ዛሬ በቴሌቪዥን ተላልፏል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኩማ የድንበር ጉዳይ እንደማይነሳ በመጥቀስ ተቃዋሚዎችን ወቅሰዋል።

ኦሮሚያን ልዩ ዞን ከአዲስ አበባ ጋር ያዋሀደው አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በክልሉ ከተካሄዱት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች የአምቦው በጉልህነቱ ይጠቀሳል። አምቦ ነዋሪው ግልብጥ ብሎ በመውጣት ተማሪዎችን ተቀላቅሏል። ኢህአዴግ ባወጣው መግለጫ “… በአምቦ ዩኒቨርስቲ የተቀሰቀሰው ሁከት ወደ ከተማ በመዝለቁ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት በአምቦና ቶኬኩታዮ ከተሞች የሰባት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ባንኩን ጨምሮ በበርካታ የመንግስትና የሀዝብንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል” በማለት ግድያውን ከንብረት ውድመት ጋር ለማያያዝ ሞክሯል። በመደ ወላቡ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን፣ በሌላም በኩል “በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በሰላም የእግርኳስ ጨዋታ በቴሌቪዥን በመከታተል ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተወረወረ ፈንጂ ወደ70 ያህል ተማሪዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል” ሲል በህይወት ላይ የደረሰውን ጉዳት አስታውቋል።police12

ኢህአዴግ የሟችና የቁስለኞችን ቁጥር ዝቅ ቢያደርግም የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ኦ.ፌ.ኮን በመጥቀስ እንደዘገበው በአምቦ ለተገደሉት 17 ሰዎች ኢህአዴግን ተጠያቂ አደርጓል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫ ደግሞ አመጹን ከኋላ ሆነው የመሩትን የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል። ክልሉ በመግለጫው ህይወታቸው ስላለፈ ዜጎች ያለው ነገር ስለመኖሩ የኢህአዴግ ቴሌቪዥን ያለው ነገር የለም። ግድያው ስለተፈጸመበት አግባብ የማጣራት ስራ እንደሚከናወን እንኳን አልጠቆመም።

የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙትና የጎልጉል የኦሮሚያ ምንጮች እንዳሉት በሰሞኑ ተቃውሞ ከ36 ሰዎች በላይ ተገድለዋል። የሲኤንኤን አይ ሪፖረተር በአምቦ ብቻ 30 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን አመልክቷል። ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ በሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ታስረዋል። የቁስለኞች ቁጥርም ቀላል አይደለም። በዚሁ ሳቢያ የህዝብ ስሜት በቁጭት የተሞላ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። የክልሉ ምክር ቤት ግን ህዝብ ከጎኑ መቆሙን በመጥቀስ ምስጋናውን አቅርቧል።

በአምቦ ከደረሰው ሰብአዊ ጉዳት በመቀጠል በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ማንነቱ የማይታወቅ ሰው ወረወረው በተባለ ቦንብ አንድ ሰው መሞቱና 70 መቁሰላቸው አስደንጋጭ ዜና ሆኗል። ቦንቡን ማን ጣለው፣ ከየት መጣ? ማን፣ ለምን ዓላማ ተማሪዎች ላይ ቦንብ መወርወር ፈለገ? ተማሪዎችን መጨረስ ከፈለገ ከተጠቀሰው በላይ ጉዳት እንዳያደርስ ማን ከለከለው? የሚሉትና ተመሳሳይ ጥያቄዎች እየተሰነዘሩ ነው። ምን አልባትም የተቀነባበረ ድራማ ሊሆን አንደሚችልና ጉዳዩን ከብሄር ጋር የማገናኘት ዓላማ ያለው እንደሚሆን እየተሰማ ነው

ኢህአዴግ በቴሌቪዥን ባሰራጨው የቅስቀሳ ፕሮግራም “ኦሮሚያ መሬት ተቆርሶ ለአዲስ አበባ እንደማይሰጥ፣ ክልሉ ካልፈቀደ የሚሆን ነገር እንደሌለ፣ ክልሉ ቢፈቅድ እንኳን እንደ ቀድሞው ልዩ ዞኑ ውስጥ ያሉት ወረዳዎች በኦሮሚያ ስር እንደሚተዳደሩ፣ የመሬት ቆረሳው ተራ የጠላት ወሬና ፕሮፓጋንዳ” እንደሆነ አቶ ኩማ ደመቅሳን ጨምሮ የተለያዩ ሃላፊዎች ሲናገሩ አሰምቷል።

በዚሁ የፕሮፓጋንዳ ስርጭት “የክልሎች ማንዴት በህገመንግሰት የታሰረ ዋስትና አለው” በማለት የኦህዴድ ሰዎች ሲናገሩ ታይተዋል። ስርጭቱ አዲስ አበባና የልዩ ዞኑ ከተሞች በተቀናጀ ልማት ተሳስረው “ሲያብቡ” የሚያሳይ ዲዛይን በተደጋጋሚ በማቅረብ “ለዚህ ልማት እንረባረብ” የሚል ጥሪ አሰምቷል።

ቪኦኤና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ እንደዘገቡት የኦሮሚያ ፌዴራል ኮንግረንስ ድርጊቱን ክፉኛ መቃወሙንና ለደረሰው የህይወት ኪሳራ ኢህአዴግ ተጠያቂ አድርጓል። በልማት ስም ከድሃ አርሶ አደሮች ላይ የሚወሰደው መሬት “የመሬት ቅርምት” ስለሆነ ባስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል። ክልሎች ህገ መንግስታዊ መብትም ሳይሸራረፍ እንዲከበር አሳስበዋል።

dire dawa universityበተያያዘ ዜና ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በሚወጡ ሰልፈኞች ላይ ፍጹም የሃይል ርምጃ እንዲወስዱ የታዘዙ የጸጥታ ሃይሎች ርምጃቸውን እንዲያለዝቡ መታዘዙ ታውቃል። በተወሰደው የሃይል ርምጃ ህዝብ ክፉኛ በመቆጣቱ የሚወሰዱ ርምጃዎች እንዲላዘቡ መታዘዙን ተከትሎ በዛሬው እለት አንዳንድ ከተሞች ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልጸው በሰላም መበተናቸውቸው ሰምቷል። ቪኦኤ እንዳሰማው የድምጽ መረጃ “የነፍጠኞች ሃውልት ይፍረስ” የሚለው ጥያቄ አሁንም እየተስተጋባ ነው።

የኦፌኮው አቶ ገብሩ ገ/ማርያም እንዳሉት አማራውንና ኦሮሞውን ለማጫረስ እየተከናወነ ያለ ሴራ አለ። ለረዥም ዓመታት አብሮ የኖረን ህዝብ ለማናከስ የሚደረገውን ሴራ ድርጅታቸው እንደማይቀበለውም አመላክተዋል። ከዚሁ ነፍጠኛን ከማውገዝ ጋር በተያያዘ “የአዲስ አበባን መስፋፋትና ነፍጠኛነትን ምን አገናኛቸው?” በማለት የሚጠይቁ፣ “ያረጀውን የነፍጥ ታሪክ ከማውራት አሁን ነፍጥ አንስቶ ጥቃት እየፈጸመ ስላለው ህወሃት የሚባለው የአንጋች ቡድን መነጋገር አይሻልም ወይ” ሲሉ ይደመጣሉ። (ፎቶዎቹ ከፌስቡክ የተወሰዱ ናቸው – የየትኛውም ኢትዮጵያዊት እናት ለቅሶ የሁሉም መሆኑን እንዲያሳይ የተጠቀምንበት ነው)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Comments

 1. melat yohannes says:

  Evrithing is true we ganna help by evrithing

 2. ማንም ስለ አማራ ያወራ የለም። ስለ ባለገዉና ሊያጣላ ስለሚሞክረዉ መንግስት እንጂ

 3. Leave TPLF alone!!!REMEMBER THAT TPLF WON THE WAR AGAINST ALL ODDS BUT NEVER TRIED TO CONTROL POWER ALONE. BUT YOU HAVE NOT APPREACIATED THIS!!!! IT IS SHAME!!! NO WHERE BUT IN ETHIOPIA NO ONW BUT TPLF GIVES EQUAL RIGHT TO THOSE IT HAS DEFEATED IN WAR!!!!!!!!!!!!!!I AM SORRY FOR THE LOSE OF LIFE OF INNOCENTS BUT I CANNOT HELP IT. WE NEED TO BE REASONABLE!!!!!!!!!!!!

  • We left you alone to kill and torture, expropriate and abuse the whole nation. Enough is enough there is no leave alone. You have this twenty years propaganda that TPLF used to convince the Tigrian people that they won the war. It is a false myth that the TPLF created. What type of war they won? They came to Addis with no war. It the internal turmoil of the Derg and the Ethiopian people were fed up with the Derg and they want them to fail and the army left with out firing a bullet. we know this it is the silent revolution against the Derg that led the TPLF to detour their unsuccessful liberation struggle to the false war winning you are bragging here. Yes it is only in Ethiopia that TPLF exist with absolute control of everything and had never given equal right to anyone. There is no equal right it is clear dictatorship and that is why we have all this mess.

 4. no one is worth dying. the one who knows his right and duty stands for his right. no nationalism at all. “no second nation.” struggling for ur identity, ur culture, and for a land given by nature is undeniably my right.

 5. just wait, time will come to through away the weyane junta. I am afraid where will go the tigraian people. not in Amhara land or oromia land

 6. የሰልፉ አላማ በመሬት ይዞት ወይንም የአፓርታይዝ አስተዳደር ጉዳይ ከሆነ ተገቢነት ቢኖረውም፡ ከዚህ በበለጠ የሚያሳስበው፡ በኦሮሞ ሕዝቦች ላይ የደረሰው ሰባዊ ረገጣ በሌሎችም ኢትዮጵያውያንና/ት የደረሰና እየደረሰ አለ በመሆኑ የቀድሞው ነፍጠኛ ለሀገር አንድነት፡ ያሁኑ ነፍጠኛ የዘር የጎጥ የሃገር አጥፊ በመሆኑ፡ ተረድተን የሁላችንን ነጻነትና መብት ሃገራዊ ጥቅም ተጋሪነት ማረጋገጥ የምንችለው፡ ያለ ወገንተኝነት የሁላችን ችግር ለመፍታት በሕብረትና በመከባበር ይህንን ጎጠኛ ስራአት መገርሰስ ገባናል፡ እንዲሁም ሊሂቃኑን በትልቅ ደረጃ የትምህርት ገበታ የተሰማራችሁ ውድ ወገኖች የግል ጥቅምን ላማስጠበቅ ኦሮሞ በማለት ጠባብነት በሕዝብ ላይ አትዝሩ፡ ኢትዮጵያ በታሪክ መዛግብት የምትታወቀው የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ያላት በቋንቋና በልምድ የበለጸገች ድንቅ አፍሪካዊ ሃገር ናት ይህ ክብርና ማንነት ለመሻር አይቻልም፡፡ በተወሰደው ጭካኔ የተመላበት ፋሽሽታዊ እርምጃ፡ለደረሰው ምንኛውም የሕይወትና የንብረት ውድመት የዚህሰርዓት ጋሻ ጃግሬዎች ምስለኔዎች ተጠያቂዎች ናቸው፡ ለደረሰው የሕይወት ጉዳት ለመላው የአንቦ ሕዝብ ለወላጆች ያለኝን ልባዊ ሃዘን ስገልጽ ጽናትና መረጋጋት ፈጣሪያችን እንዲያድላቸው እመኛለሁ። ሥርዓቱ እስኪወድቅ ትግሉ ከመላው ኢትዮጵያዊ ጋር በማበር ይቀጥል፡

  • ተረድተን የሁላችንን ነጻነትና መብት ሃገራዊ ጥቅም ተጋሪነት ማረጋገጥ የምንችለው፡ ያለ ወገንተኝነት የሁላችን ችግር ለመፍታት በሕብረትና በመከባበር ይህንን ጎጠኛ ስራአት መገርሰስ ገባናል፡ እንዲሁም ሊሂቃኑን በትልቅ ደረጃ የትምህርት ገበታ የተሰማራችሁ ውድ ወገኖች የግል ጥቅምን ላማስጠበቅ ኦሮሞ በማለት ጠባብነት በሕዝብ ላይ አትዝሩ

   This type of contradiction is the problem. On one side Adnet’s golden idea says “በሕብረትና በመከባበር ይህንን ጎጠኛ ስራአት መገርሰስ ገባናል’ that is good we all want to see this unity with respect. His poisonous or something from his inside says ” “በትልቅ ደረጃ የትምህርት ገበታ የተሰማራችሁ ውድ ወገኖች የግል ጥቅምን ላማስጠበቅ ኦሮሞ በማለት ጠባብነት በሕዝብ ላይ አትዝሩ”. Standing for the interest of Oromo has nothing to do with narrow mindedness. This is a big obstacle for unity and it does not bring us closer it only stretches our distance. Why is being an Oromo is ጠባብነት? Be carful l what you say. You see, when you open your mouth we can see your mind and brain.

 7. Ordofaa Hordofaa says:

  What are these children and grandchildren of Naftegnas doing at our demonstrations? We do not want them to come to our peaceful rallies with their blood stained flags. I see someone who looks like our lion-heart freedom fighter Jawar standing next to the blood stained flag of the Naftegnas. He should never be seen in the vicinity of these descendants of mass killers. Next time I see him I am going to express my outrage to him. We do not need Naftegnas’ help. We have already liberated Oromia 99%. I just received word from back home that every Oromo member in the defense forces have defected and liberated 100% of Illu, Wollegaa, Bale, Southern Sidamo, and Haraghe. 99% of Shewa is under their control with the exception of Finfine. All Tigre and Amhara(Except the Gojjames) members of the defense forces have fled and sought refuge in their homelands. Gojjame soldiers have taken side with us and we will help them in the liberation of their homeland from the Tigrayans and Amharas. I have told you Oromia will be an independent nation in 2014. Did I lie? Here it is.

 8. Ittu Aba Farda says:

  I see grim days ahead for our people. Extremists on both sides are given a windfall they have been waiting for. As we all know unemployment back home is staggeringly very high in general and among the youth in particular. This vast unemployed youth is ripe to be used as a cannon fodder for whoever comes along with seemingly rosy promises. They are urging this unemployed and frustrated youth to take his/her anger on innocent poor farmers and public infrastructures. These wicked extremists are feeding this hopelessly unemployed youth poison from what had happened almost 150 years ago. I was recently found myself very disappointed of a very educated elderly man from my own Oromo nationality wherein he dug up some incendiary material out of the travel memoir of an English man named William Cornwallis Harris. Scratching the surface of our shared history is not a bad thing but keeping oneself busy clawing in what was written long time ago just to find something that will definitely incense unsophisticated readers. Such action will not help heal the wound sustained in the past. Unless such malignant propagation stops I see impending mayhem and unseen massacre of innocent and poor farmers and dwellers. The setup is similar to what we had seen in the early 1990’s but this time it is being fanned in many media outlets that were not available then. Such hatred fanning is being shamelessly carried out by some well educated individuals who are trying to prove that they are also ‘True and Genuine’ Oromos.
  Again, I feel unsettled by what is being set up now. I hope I am wrong but unless we all refrain from fanning the wheels of ethnic hatred I see something afoot. Budding youth of my proud Oromo people are being aroused the wrong way leading to disastrous consequences both by the seated regime and narrow minded intellectuals who have made violence their romance of the day. We should make the welfare of our people part of our daily prayers. I believe in the power of prayers because I believe the Will of Our Creator Will Triumph upon Evil!!! May Peace and Harmony Prevail Among Our People!!!! Insha Allah!!!!!

Speak Your Mind

*