• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሁለት ሪዞርቶች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት

July 23, 2020 08:06 am by Editor 2 Comments

ሐይሌ ሪዞርት በዝዋይ እና በሻሸመኔ ከተሞች ለወደመበት ኢንቨስትመንት መንግስት ድጋፍ ካደረገ ወደ ስራው እንደሚመለስ አስታውቋል።

የድርጅቱ ባለቤት አትሌት ሃይሌገብረስላሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንዳለው የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞትን ተከትሎ በዝዋይ እና ሻሸመኔ ከተሞች በስራ ላይ የነበሩት ሆቴሎች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል።

አትሌት ሃይሌ ከዚህ በፊት በነዚህ ከተሞች የነበረውን ኢንቨስትመንት ማቋረጡን ያስታወቀ ቢሆንም አሁን ግን መንግስት ለወደመበት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ካደረገለት ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል።

የዝዋዩን ሪዞርት ወደ ስራ ለመመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የጥገና ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን የሻሸመኔው ሀይሌ ሪዞርት ቅርንጫፍ ግን የግድ እንደ አዲስ መገንባት ስለሚጠይቅ ወደ ስራ ለመመለስ በትንሹ ሶስት አመታትን እንሚፈጅ አትሌት ሀይሌ ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከዚህ በፊት በነበሩ ሁከቶች ምክንያት ለወደሙ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በባለሙያ በማስጠናት ካሳ መክፈሉ ይታወሳል።

የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ባሳለፍነው ሳምንት ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት በኋላ በተፈጠሩ ሁከቶች በክልሉ ለወደሙ ኢንቨስትመንቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ መናገሩ አይዘነጋም። (ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን ሐምሌ 16 ቀን 2012 ዓ.ም)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Right Column Tagged With: haile, jawar massacre, shashemene resort, ziway resort

Reader Interactions

Comments

  1. G b says

    July 24, 2020 09:52 am at 9:52 am

    Merete new beretu

    Reply
  2. Tesfa says

    July 31, 2020 01:36 pm at 1:36 pm

    በምንም ዓይነት ሂሳብ እንደገና መጠገን አያስፈልግም። ይህ በግብታዊነት የተፈጸመ ወንጀል ሳይሆን በተጠና እና በተደራጀ መልኩ ዘር ሳይለይ ክርስቲያን የሆኑ ሰዎችን በተለይም አማራዎች እና ሌሎች ተወልደው ባደጉበት ምድር መጤ እየተባሉ የተገደሉበት እውነታ ነው ያለው። አልፎ ተርፎም ድርጊቱ ከተፈጸመ በህዋላ የነፍጠኛ (ማለት ወታደር ማለት ነው) ማንም ንጽሁ ኦሮሞ ከአማራ ወይም ከሌሎች ሰዎች ላይ ንብረት ቢገዛ ወዪለት እየተባለ እንዳለ አሁንም በስልክና በተበታኝ ወረቀቶች የሚደርሱት ዛቻዎች ያሳያሉ። የኦሮሞ አክራሪዎችና የወያኔ ፓለቲከኞች ጥላቸው ኢትዮጵያ ከሚለው ስም ጋር ነው። ይባስ ብሎ ኦሮሞዎቹ በቆዳ ስፋት፤ በህዝብ ቁጥር ብልጫ ስላለን መገንጠልና ኦሮሚያን ለኦሮሞዎች ብቻ ማድረግ አለብን ብለው ነው የሚያምኑት። ይህም አስተሳሰብ ከሻቢያና ከወያኔ ጋር ሰበቴ መጠጣጣቸውን ያሳያል።
    ትዕይንት ሻሸመኔ – ዘራፊዎች ተሰልፈው ይህ የአማራ ቤት ነው የክርስቲያን ቤት ነው እያሉ ይንጋጋሉ። ቤቱን ሰብረው ገብተው እቃ እየዘረፉ ካዝና ዘርፈው ወደ 400 ሺህ ብር ይቀባበላሉ። በዚህ መካከል የቤቱን አባወራና እርጉዝ ሚስቱን ጨምረው ጎትተው በማውጣት ሚስቱን ልጆቹ ፊት በአሰቃቂ ሁኔታ ይገሏታል። ይህ ሁሉ ሲሆን የአካባቢው የጥበቃ ሃይል ጉዳዪን ያውቃል። ግን ተመሳጥረዋል። ታዲያ እነዚህ የሰው ከብቶች እንደገና ተመልሰው ድርጊቱን እንዳይፈጽሙ የሚያደርጋቸው ምንም ሃይል የለም። እኔ ሻለቃ ሃይሌ ገ/ስላሴን ቢያደርገኝ መሸጥ ነው። ስንት ሌላ ስፍራ ሞልቶ ሥራ ፈላጊና ባለሃብቶችን በሰላም የሚያስተናግድ!
    እነዚህ ቀፋፊ ሃይሎችና የወያኔ የቀድሞውን ስልጣን የመናፍቅ ጥማት ከግብጽ ጋር በማበር ገና ህዝባችን ያጫርሱታል። አንድ ማስረጃ ልስጥ። በቅርቡ በአዲስ አበባ አካባቢ የተያዙት የወያኔ ባለስልጣኖች በ 5 ሺህ የዋስ መብት መለቀቃቸው በራሱ ወያኔ ምን ያህል ከኦሮሞ አክራሪ ሃይሎች ጋር እንደተጣመረ ያመላክታል። ይታያችሁ የተከሰሱበት ጉዳይ እኮ ” የሃገር ሚስጢርን ለውጭ ሃይሎች አሳልፎ መስጠት” ነው የሚለው። አስገራሚ ድራማ ነው። ሌሎች እንደ ኢ/ይልቃል ጌትነት፤ እንደ እስክንድር፤ ህጻን ልጇን ትታ የDHL ፓስታ መቶልሻል ተብላ የታሰረችው፤ እንዲሁም እውቁ ፓለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌውና ሌሎችም የዋስ መብት አልተፈቀደላቸውም። የፈጠራ ክሱ እስኪዘጋጅ ድረስ በማረፊያ ቤት እንዲቆዪ ተደረጓል። ግፍ በምድሪቱ ማቆሚያ እንደለሌው የሃምሌ ዝንብ በህዝባችን ላይ ይወርዳል። የተበዳዮችን ጩኽት ሰምቶ አይዞአቹሁ ወንጀለኞችን ይዘናል። እስቲ ኑ እስር ቤት ይህ ነው አባትክን፤ እናትክን፤ ሚስትህን የገደለብህ እስቲ ለዪልን ማለት የማይቻልበት ወንጀል ሰሪና አሳሪ የተመሳጠሩበት ትስስር ነው ያለው። በውጭ ሆነው ዳዎን ዳዎን ኢትዮጵያ የሚሉት አክራሪ ኦሮሞዎችንና ደጋፊዎቻቸውን ለማሳፈር ሰልፍ ብቻውን አይበቃም። ያደረጉት በደል በፊልም በመቅረጽ ከሞት ተራፊዎችን ቃለ መጠየቅ በማድረግ ለዓለም ህዝብ መበተን አስፈላጊ ነው። እነዚህ ዳዎን ዳዎን ያሉት ደግሞ በዚያው ቁመው ባፋከሩበት ሃገር እንዲኖሩ ከሃገር እንዳይገቡ በመረጃው መሰረት መከልከል አለባቸው። እዚያው ባበድበት ሃገር ይቀበሩ!
    ስለሆነም አረጋግተናል፤ ተፈናቃዮችን ወደ ስፍራቸው መልሰናል ወዘተ የሚለው የመንግስት ጡሩንባ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም አይነት ነው። በጭራሽ ይህ ትውልድ ያበደ ትውልድ በመሆኑ ዳግመኛ መሸራገድ አይቀሬ ነው። የኦሮሞ ወጣቶች ለኦሮሞ ህዝብ አይገዳቸውም። ያማ ቢሆን ስንቱ ስራ ፈት በሆነበት ሃገር ላይ የስራ ፈጣሪዎችን ሃብትና ንብረት እንዲሁም የመንግስትን መ/ቤቶች ባላወደሙ ነበር። ፍትጊያው ቅናት ነው። ፍትጊያው ተላላኪነት የፈጠረው ነው። የኦሮሞን ህዝብ ጠቅሞ አያውቅም ወደፊትም አይጠቅምም። የራሱን ወገን ገድሎ የገደለው አማራ ነው ብሎ መልፈፍ ምን ያህል እብደት እንደሆነ ያመላክታል።
    ጠ/ሚሩ በምላጭ አፋቸውና በቃላት ጋጋታ ብቻ ሃገር ይገነባ ይመስል በዙሪያቸው አክራሪ የኦሮሞ ፓለቲከኞችን ጉያቸው አርገው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ቢሉ ምንም ፋይዳ የለውም። ትልቁ የኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ጥላቻ ኢትዮጵያ የሚለው ስምና ክርስትና ነው። ይታያችሁ በግድ ክርስቲያን ያረጉን ነፍጠኞች ናቸው የሚሉ ጭፍን ምሁራን ያፈራች ምድር ናት። ታዲያ ነፍስ ካወቅክ በህዋላ አልፈልግም አትልም እንዴ? ግን የማባያ ፓለቲካቸው እንዲህ ነው የፈጠራ ወሬ!
    ከሁሉ እኔን የሚያሳዝነኝ ግንባር ቀደም የሆኑት የኦሮሞ መሪዎች መራራ ጉዲና፤ አቶ ሌንጮ ለታና ዳውድ ኢብሳ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እነዚህ ቄሮ ነን ባዮች የሚያደርሱትን ግፍ አለማውገዛቸው ነው። ይባስ ብለው ጉዳዪን በማቀናጀትና በመምራት እልቂት ያደረሱ ሰዎች እንዲፈቱ ይወተውታሉ። እናውቃለን በአርባ ጉጉና በበደኖ ኦነግ ያደረሰውን በደል። ትውልድ አይረሳም። ግን ህዝባችን ከዚያ እልቂት አልተማረም። ዛሬም እኖራለሁ በሚል ተስፋ በግ ካራጅ ጋር ይውላል እንዲሉ ሆነ። በቅርቡ አቶ ሌንጮ ሲናገር “ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ሃገር ናት በሚለው ላይ ስምምነት የለም። ሃገራዊ ምክክር ያስፈልጋል” ብለዋል። ቀጥለውም “በተፈጠረውን ችግር በኦሮሚያ ላይ ብቻ ማተኮር ትክክል አይደለም” ብለዋል። ሌላው ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ በፓለቲካ ዓለም ተዘፍቆ የኖረው ዶ/ር መራራ ጉዲና “ጃዋር ካልተፈታ ችግር ይፈጠራል” ይለናል። አይ ጊዜ አይ ፓለቲካ የሰዎች ደም የውሻ ደም የሆነበት። እስቲ የአሁኑ ከአለፈው ይሻላል የምትሉ ንገሩኝ። የቱ ላይ ነው መሻሉ?
    ፓለቲካ ጊዜን ታካኪ ነው። የዛሬ አሽቃባጮችና አንገት ቀይዎች ነገ በወረፋቸው ይቀላሉ። ችግሩ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ነው። ለነገሩ ወያኔ የሃገር መሪ ከሆነ ወዲህ ሁሉም ነገር እጅ በእጅ ሆኗል። ሰው ሲመረው በረሃ ይገባል። የትጥቅና የህዝብ ቁጥር ብዛትም ማንም አያድንም። በወለጋና በሌሎችም የኦሮሚያ ግዛት እናቶች ሲገደሉ፤ ባለስልጣኖች በጠራራ ጸሃይ ሲረሸኑ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ነን ባዮች የኦሮሞን ህዝብ እያገለገሉ ይመስላቸው ይሆን። ሴት ተማሪዎችን አፍኖ የሚወስድ የኦሮሞ ነጻ አውጪ የእንስሳዎች ክምችት እንጂ የሰውነት ባህሪ የለውም። በቅርቡ በሲያትል የኦሮሞ ድውያን አንድን ነጭ ሲደበድቡት የሚያሳየውን ቪዲዮ ለአንድ የህግ ባለሙያ አሳየሁትና አንዲህ ብየ ጠየኩት። አሁን ይህ ወጣት ታጥቆ ቢሆንና ተኩሶ ቢገላቸው ህጉ ምን ይላል አልኩት። አይ በህግ የታጠቀው ከሆነና የሚመቱትን ብቻ ተኩሶ ቢገድል አንድም ቀን እስር ቤት አያድርም አለኝ። የእብድ ፓለቲካ እንዲህ ነው የጅምላ አስተሳሰብን ምርኩዝ ያረገ በራስ ማሰብን የነጠቀ የቁራሪቶች ጭኽት። ስለሆነም ቤታችሁ የተቃጠለ፤ ንብረታችሁ የወደመ፤ ወገናችሁ የታረደ እንደገና በዚሁ የደም ቦታ ያለኝን አስተካክዪና ጨምሬ በሰላም እኖራለሁ ብላችሁ ማሰባቹሁ እብደት ነው። ምድሪቱ ሰፊ ናት። ሌላ ቦታ ሃብታችሁን፤ እውቀታችሁን ይዛችሁ ሂዱና ኑሮ። የኦሮሚያ ክልል እሳት ተጀመረ እንጂ ገና አላለቀም። የኦሮሞ ግንባር መሪዎችን ነን የሚሉት የሚናገሩት ለዚህ ዋንኛ ማሳያ ነው። የክልል ፓለቲካ ሁሌ መተራረድ ነው። እንሰንብት ግድ እናያለን። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule