ሐይሌ ሪዞርት በዝዋይ እና በሻሸመኔ ከተሞች ለወደመበት ኢንቨስትመንት መንግስት ድጋፍ ካደረገ ወደ ስራው እንደሚመለስ አስታውቋል። የድርጅቱ ባለቤት አትሌት ሃይሌገብረስላሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንዳለው የድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞትን ተከትሎ በዝዋይ እና ሻሸመኔ ከተሞች በስራ ላይ የነበሩት ሆቴሎች ሙሉ ለሙሉ ወድመዋል። አትሌት ሃይሌ ከዚህ በፊት በነዚህ ከተሞች የነበረውን ኢንቨስትመንት ማቋረጡን ያስታወቀ ቢሆንም አሁን ግን መንግስት ለወደመበት ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ካደረገለት ወደ ስራ እንደሚመለስ ገልጿል። የዝዋዩን ሪዞርት ወደ ስራ ለመመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የጥገና ጊዜ የሚፈጅ ሲሆን የሻሸመኔው ሀይሌ ሪዞርት ቅርንጫፍ ግን የግድ እንደ አዲስ መገንባት ስለሚጠይቅ ወደ ስራ ለመመለስ በትንሹ ሶስት አመታትን እንሚፈጅ አትሌት ሀይሌ … [Read more...] about በሁለት ሪዞርቶች ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት