
በተከታታይ በቲውተር ገጹ መረጃ የሚያሰራጨው የአሸባሪው ትህነግ አባል ጌታቸው ረዳ ትግራይን እንደማይመራ ክርክር ተነስቷል።
የራያ ልጅ የሆነውና ፍጹም የአማራ ደም ያለው ባንዳው ጌታቸው ቀደም ሲል በዩኒቨርስቲ መምህርነቱ ወቅት በረኸኞቹን ትህነጎች “ህግ የማያውቁ፣ ደደቦች፤ ምንም የማይገባቸው፤ መሃይም ደናቁርት” እያለ ክፍል ውስጥ ሲያንኳስስ እንደ ነበር የሚናገሩት ተማሪዎቹ የትህነግ አባል መሆኑ ይፋ ከሆነ ማግስት ጀምሮ ግን ለትህነግ አጎብዳጅና ተገዢ እየሆነ መምጣቱን እነዚሁ ተማሪዎችና በቅርብ የሚውቁት ይመሰክራሉ።
“እዳ በዝቶበት መክፈል ሲያቅተው የትህነግ አባል ሆኖ ማገልገል ጀመረ፤ ለፕሮጀክት የተሰጠውን ገንዘብ ሙልጭ አድርጎ በላው፤ ወሰበበት፣ ጠጣበት፤ ትህነጎችም በስልት አበሰበሱት” ሲሉ ጌታቸውን በቅርብ የሚውቁት ይናገራሉ። በቀጣይም “ዕዳ ስረዛ ተደርጎለት ትህነግን በነውሩ እንዲቀላቀል ተደረገ” ሲሉ እነዚሁ ወገኖ ያስረዳሉ።
ከለውጡ በኋላ ዋና ተዋናይ በመሆን ፊት የተቀመጠው ራያው ጌታቸው ረዳ ከህግ ማስከበሩ ዱላ ተርፎ በበረኻ ከአውሬ ጉድጓድ ብቅ እያለ በሚሰጠው ማብራሪያና በሚያሰራጨው መረጃ በትህነግ ደጋፊዎች ዘንዳ ታዋቂና ስሙ በሚዲያ የሚጠራ “አዲስ ታጋይ” ሊሆን ችሏል።
በጦርነቱ በርካታ የትህነግ ነባርና የመካከለኛ ዕድሜ አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ ግንባር ቀደም የሆነው ጌታቸው ትህነግ ከጉድጓድ ወደ መቀሌ ከገባ በኋላ “ትግራይን መምራትም ሆነ መወከል አይችልም፣ አማራ ነው” የሚሉ የትግራይ ሰዎች በዝተዋል።
በአማራነቱና በቀድሞው የትህነግ የበረኻ ትግል ተጋዳላይ ያልነበረ በመሆኑ ከትህነግ አመራሮች ውስጥ የተለየ እንደሆነ የሚነገርለት ጌታቸው፤ የአሸባሪው ትህነግ የነፍስ አባት ስብሃት ነጋ እጅግ ይዘልፈውና ይንቀው እንደነበር፣ እንዲያውም በአንዳንድ ላይ ጌታቸው ሃሳብ ሲሰጥ ስብሃት ማንነቱን እየጠቀሰ “ዝም በል አንተ …” ይለው እንደነበር ከራሱ ከትህነግ የወጡ መናገራቸው አይዘነጋም።
በዚህ በቆየው የማንነት ቀውስ ይሁን በሌላ በግልጽ ባይነገረም ጌታቸውን አስመልክቶ የተለያዩ አመለካከት መያዙን የኢትዮ12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ዘግቧል። እሱ እንዳለው ጌታቸው ክልሉ ቃለ አቀባይነት የዘለለ ኃላፊነት ከተሰጠው ቅቡል አይሆንም። ሰሞኑንን ድርድር አስመልክቶ የተለያየ አቋም መያዙን እንደሰሙ ለትህነግ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው።
በሰሜን አሜሪካ የሚኖረውና ለትህነግ የውጭ ክንፍ አመራሮች ቅርብ ሰው ባልደረባ ሰማሁ እንዳለው የጌታቸው ገኖ መውጣት አሁን አሁን ቅሬታ እንዲሰነዘርበት እያደረገ ነው። እሱ እንደሚለው አዲስ ቃል አቀባይ ሁሉ ሊሾም ይችላል። “ጌታቸው በየደቂቃው ትዊት የሚያደርገው የውስጥ የበላይነት ለመያዝና በውጭ ያለውን የትህነግ የጀርባ አጥንት ለመያዝ ነው” የሚሉ በተመሰቃቀለውና በተበታተነው ትህነግ ውስጥ በቅርቡ “ሽኩቻ እንሰማለን” ባይ ናቸው። ሽኩቻ ብቻ ሳይሆን ምን አላባትም “የጦር አበጋዝነት ክፍፍል ትግራይ እንደሚገጥማት እሙን ነው” የሚሉም እየተነሱ ነው።
ሌላው የወንበዴው ትህነግ መሪ ሆኖ ለመውጣት እየታተረ ያለው ጻድቃን ገብረትንሳይ ከማይታወቅ ቦታ ሆኖ መግለጫ መስጠቱ፤ በህይወት አሉ የሚባሉት መተንፈስ መጀመራቸውና ሁሉም ተሰባስበው አንድ ላይ አመራር አለመጀመራቸው ይታወቃል። ከዚህ አኳያ ትህነግ እንደ ቡድን ወጥ አመራር ይዞ በአንድ መሪ ብቅ ለማለት አለመቻሉ ከበፊት ጀምሮ በትህነግ ውስጥ ያለውን የጎጥ ክፍፍል እያባሰው እንደሄደ ይነገራል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ “አማራው ጌታቸው” የትግራይ አዲስ ትውልድ መሪ ሆኖ ብቅ ለማለት መፈለግ ከማንነቱ ጀምሮ በጽንፈኛ ትህነጎች ዘንድ ተወዳጅነትን አላተረፈለትም። ትህነግ እንዳበቃላትና በነጌታቸው ዓይነት “አዲስ ትህነጎች” መመራት አለባት የሚሉቱ ከጽንፈኞቹ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የአድዋ የበላይነትን ለማስጠበቅ የሚጥሩት ጥቂት ርዝራዦች ከሁለቱም ጋር በሌላ ጽንፍ ተያይዘዋል።
በትግራይ አውራጃ እየተለየ የሚፈጸመው ግድያ የከፋ መሆኑ፣ ወደ ኤርትራ የሚሰደዱ መኖራቸው፣ ጉዳዩን የዓለም ዓቀፉ ህብረተሰብ እንዲከታተለው መጠየቁ እያደር ነገሮች ሲጠሩ “ማን የማንን አካባቢ አጠቃ” የሚለው የልዩነቱ መሰረታዊ ማጠንጠኛ እንደሚሆን አስተያየት የሚሰጡ፣ ትላንት ዶ/ር አብርሃምና የራዩማ ፓርቲ አመራር እንዳሉት በራያ ከሰላሳ ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው የጉዳዩን አሳሳቢነት ያሳያል።
ነገሩን ከዳር ሆነው ለሚያዩ አማራው ጌታቸው በትግራይ መሪ ሊሆን እንደማይችል ያምናሉ። ሆኖም ጌታቸው ከአብን የተወሰኑ አመራሮች ጋር ግንኙነት እንዳለው እናውቃለን የሚሉ ግን ግምታቸው ሌላ ነው። (ከኢትዮ12 የተቀናበረ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ከት ብለሽ እየሳቅሽ ጥሩ ጥርስ እንዳለው
ገመናሽን ሁሉ ጠላት ወዳጅ አየው
ወያኔ የአውሬዎች ጥርቅም ነው። አሁን በመቀሌና በትግራይ ነጻ አወጣንህ በሚሉት ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል የሚዘግብ የለም እንጂ ድርጊታቸው ጤነኛን ሰው ልብስ አስወልቆ እብድ ያደርጋል። ሰው እንደ በግ አጋድመው አርደዋል። ባልሽን አምጭ፤ ልጅሽን አምጭ እየተባሉ ሲገደሉና ሲጎሳቆሉ ማየት የቀን ተቀን የወያኔ ተግባር ነው። ዘረፋው፤ በጉልበት ሴቶችን መድፈር በፊትም ነበር አሁንም ብሶበታል። ለማን ይግባኝ ይባላል። መንግስት የለ? ግን እብደቱ በወያኔ ላይ ብቻ አይደለም። በውጭ ያሉ የትግራይ ልጆችም አብደዋል። ለምን እውነትን ፍለጋ ሰዎች መርጠው አይልኩምና የሚሆነውን በስፍራው ተገኝተው ማየት እንደማይፈልጉ ጭራሽ አይገባኝም። ሩቅ ሆኖ እርዳታ እንካችሁ ማለትም ሆነ በለው በማለት ሰውን ለእሳት መግፋት ወንጀለኛ መሆን ነው።
ያለፈው ላይበቃ አሁንም የትግራይን ልጆች በግድና በውድ ለጦርነት እየማገድ መሬታችን እናስመልሳለን፤ ትግራይን ሃገር እናረጋለን፤ ጠላቶቻችን እንበቀላለን በማለት ሰውን የእሳት ራት አድርጎ ሌላውን ማስለቀስና ማሰቃየት ልብ ላለው አጥንት ዘልቆ ያማል። መቼ ነው እንባቸው ያለማቋረጥ የሚወርደውን የትግራይ እናቶችና እህቶች አይዞአችሁ በማለት እንባቸውን ወያኔ የሚያብሰው? መቼ ነው አማራና ኤርትራት ጠላቶቻችን ናቸው እናወድማቸዋለን ማለቱ የሚገታው። አሳዛኙ ነገር ግን ወሬው ሁሉ እኛ ወደ ጦርነት የሚገፋን እንጂ ወደ ሰላም የሚያመጣን ፍሬ ቃል የለውም። ለምሳሌ አንድ ቦታ ስመለከት የአማራ ሚሊሻ ታሪክ ሰራ ይላል። ታሪክ የቀን እድሜ የለውም። የረጅም ጊዜ ስብስብ እንጂ። ወያኔንና በጉልበት ተገዶ ውጊያ ውስጥ የተማገደ የትግራይ ወጣትን ገድሎና ራስም ሞቶ ታሪክ አይሰራም። ወንድምና እህታችን ገድለን የምንፎክር እብዶች ሃበሻው ብቻ ነው። እጅና እግሩ ታስሮ ተንበርክኮ ምህረትን የሚለምን ወንድሙን ገድሎ ጀግና ነኝ የሚል በቁሙ የሞተ፤ በጠበንጃ አፈሙዝ ብቻ የሚያስብ ጅራት አልባ እንስሳ የሚራወጥባት ምድር እንዴት ተብሎ ነው ታሪክ የሚሰራው? ታሪክ እኮ ለቀሪው ትውልድ ነው የሚሰራው። በፈረሰና በተናደ መሬት ላይ በእርስ በርስ መገዳደል የሚሰራ ታሪክ የለም። ሙትን መቁጠርና የብቀላ ድላ ቀኑ በጨለበት ላይ ማሳረፍ እንጂ።
ለጽሞና እና ለእርሻ ብዬ ትግራይን ጥዬ ወጣሁ ያለን የዶ/ር አብይ መንግስት ደግሞ ጭራሽ እውነቱን አልነገረንም። ወያኔ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ህዝብም ከህዋላ ወጋኝ ቢለን የሚነግሩን ነገር ለእውነት የተጠጋ በሆነ ነበር። ያው የግጭትና የጦርነት የመጀመሪያ ሰለባ እውነት በመሆኗ አሁን የሰሜን እዝ ለቆ ከወጣ በህዋላ በየቀኑ የሰሜን እዝን ክፋት ይዘግቡ የነበሩት ሚዲያዎች ሁሉ ጸጥ ብለዋል። ይህ የሚያመላክተው ምን ያህል የአለም ወሬ አራጋቢዎች ሚዛን የለሽ እንደሆኑ ነው። በትግራይ መከራው አሁንም ቀጥሏል። ግን አንድም ነገር መጻፍ አይፈልጉም። አይ ነጻ ፕሬስ ድንቄም ነጻነት።
አሁን የወያኔ ትራፊ አመራሮች አንተ ከአድዋ ነህ፤ አንተ የአማራ ደም አለብህ፤ አንተ እኛን አትመራም ማለታቸው በፊትም የነበረና አሁንም የሚኖር ነው። ዶ/ር አረጋዊ በርሄንና ሌሎችን ከአመራር ገፍቶ ያባረረው፤ ቀሪዎችንም ደግሞ በተለያየ ሴራ አፈር የመለሰባቸው የወያኔ ክፋት አሁንም እንደሚያባላቸው መጠራጠር አያሻም። አፉ ብቻ የቀረው ጌታቸው ረዳ የጭንቅላት በሽታ ያለበት ግፈኛ ሰው ነው። መጨረሻውም በሰፈረበት ቁና ተትረፍርፎ ይከፈለዋል። የግፍ ማቆሚያ አለው። ፍርድ ሲዘገይ ግን ህዝብ ተስፋ ይቆርጣል። አይዞን! የቆየ ታሪክ የሚነግረን የጨቋኞች እድሜ ቢንዘላዘልም መቆረጡ አይቀርም። ሽብርተኛው ወያኔ ግባዕተ መሬቱ እየተቃረበ ነው። ያን የሚያፋጥነው ግን የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። ሌላው ሃይል ሁሉ ተቀጥላና አላስፈላጊ ነው። የትግራህ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በሰላም እንዲኖር ወያኔ መወገድ አለበት። በቃኝ።
ጌታቸው ረዳ በምንም ይሁን ምንም ሕዝብን ለመምራት የሞራል ብቃት የየሌለው በስካር፣በዝሙት፣በተለያዩ አደንዛዥ ዕፆች የተለከፈ ሰው ለአገርም ለሕዝብም መልካም ኣርሃያ ኣይደለም ሕወኣት መልካም ነገር ኣይወጣባትም አንድ ኣርከበ ዕቁባይ ነበረ እሱም በዝምታ ይሰራል የነገውን አናውቅም። ጌታቸው መገምገም ያለበት ቀጣይ ሰው ነው።