በዲያስፖራ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLF/OLA - ኦነግ ሸኔ) ተወካይ የሆኑት ጃል ጅረኛ ጉደታ በቅርቡ በደሃብ ቲቪ (Dahab TV) ቀርበው የሰጡት መግለጫ፣ ፋኖን እና ትህነግን ጨምሮ ሰባት ታጣቂ ቡድኖች መሥርተነዋል በሚሉት “ጥምረት” ውስጥ ያለውን ጥልቅ የፖለቲካ ኪሳራና መሰንጠቅ አደባባይ አውጥቶታል። ጃል ጅረኛ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት የሚዋጉት ስለ ኢትዮጵያ ሳይሆን “ሀገራችን” ስለሚሏት ኦሮሚያ ብቻ መሆኑን በግልጽ የተናገሩ ሲሆን፣ “ፋኖ ከአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እንዲገድል፣ ንብረት እንዲያቃጥልና እንዲዘርፍ ሁኔታዎች እየተመቻቹለት ነው” ሲሉ በቀጥታ ከሰዋል። አያይዘውም “ብዙ የአማራ ልሂቃንና አብዛኛው አማራ ዛሬ ላይ የመንግስት ደጋፊ ነው” በማለት የጥምረቱ አካል እንደሆነ የሚነገርለትን የአማራ ኃይል ጭምር የሚያገልና የሚወነጅል ንግግር … [Read more...] about “ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ገብቶ ሕዝብ እየገደለ ነው” የኦነግ ሸኔ (OLF/OLA) ተወካይ ጃል ጅረኛ

