
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)
ዛሬ ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች በስፋት አየተዘገበ ስላለው የኮሮና መድሀኒት ተገኘ የተባለው ዴክሳሜታሶን መድሀኒት አዲስ የተገኘ ሳይሆን ከዚህ በፊት እኛም ሀገር ላይ በስፋት ስንጠቀምበት የነበረ መድሀኒት ነዉ።
ዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) የሚባለው ስቴሮይድስ (Steroids) ከሚባለው ቤተሰብ የሚመደብ የመድኃኒት ዓይነት እ.ኤ.አ ከ1960 ጀምሮ ለተለያዩ በሽታዎች ጥቅም ላይ ሲዉል የቆየ ነው።
ዛሬ ቢቢሲ ላይ የተዘገበዉ መድሀኒት የመተንፈስ ችግር እና በጽኑ የኮሮና ቫይረስ ሕመም ላይ ያሉ ሰዎችን እንጂ መጠነኛ (Mild Symptoms) ምልክት ላላቸው እንደማይጠቅም በጥናቱ ላይ አስፍረዋል።
በተጨማሪ ስቴሮይድስ (Steroids) ‘ በከፍተኛ ጥንቃቄ’ የሚሰጡ መድኃኒቶች ሲሆኑ በርካታ ‘የጎንዮሽ ጉዳት’ እንዳላቸው መረዳት ይገባናል።
ባሁኑ ሰዓት በእጃችን ያለዉ ብቸኛው መድሀኒት መጠንቀቅና መጠንቀቅ ብቻ ነው!
እንዳትዘናጉ!
‘ ዴክሳሜታሶን ‘ የተባለው መድሃኒት በኮሮና ቫይረስ በፅኑ የታሙሙትን ሰዎች ህይወት ለመታደግ የሚረዳ ነው እንጂ መድሃኒቱ ከኮቪድ-19 ሙሉ በሙሉ የሚፈውስ አይደለም።
መድሃኒቱ በተለይም በመተንፈሻ መሳሪያዎች (ቬንትሌተር) እና ኦክሲጅን ድጋፍ የሚተነፍሱ ታማሚዎችን የመሞት እድል ይቀንሳል የተባለ ነው።
በተጨማሪ መድሃኒቱ በከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች እገዛና ምክር እንዲሁም ‘በጥብቅ ድጋፍ’ የሚወሰድ መሆኑ ነው የጤና ባለሞያዎች የሚስጠነቅቁት።
በአሁን ሰዓት በዓለም ላይ ለኮሮና ቫይረስ ፍቱን የሆነ ፈዋሽ መድሃኒት የለም፤ አልተገኘም። የምርምር ስራዎችን ግን እንደቀጠሉ ናቸው።
አሁን ላይ ብቸኛው ይህን ፈታኝ ወቅት የምንሻገርበት መፍትሄ እና ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽን የምንተርፍበት መንገድ የጤና ባለሞያዎችን ምክር ማድመጥ ብቻ ነው።
Leave a Reply