• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት በአሶሳ ለጥፋት ሊጠቀምበት የነበረ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይና ገጀራ በቁጥጥር ሥር ዋለ

November 10, 2020 02:21 am by Editor Leave a Comment

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ለህወሓት የጥፋት ተልዕኮ ማስፈጸሚያነት ሊውል የነበረ ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ የያዙ 59 የባንክ ሂሳብ ደብተሮች፣ ጥሬ ገንዘብ እና ገጀራዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

በክልሉ ከህወሓት ተልዕኮ ወስደው ጥፋት ለመፈጸም በማሴር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች ቁጥር ከ70 በላይ መድረሱ ተገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ የህወሐት ጥፋት ቡድን ክልሉን ብሎም ሃገርን ለማተራመስ የሚያደርገውን ሴራ እየከሸፈ ነው።

“ባለፉት ሶስት ቀናት የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የክልሉ ልዩ ሃይል፣ ጸረ-ሽምቅ፣ ሚሊሻ እና በጎ ፈቃደኞች በተለይም አሶሳ ከተማን ትኩረት በማድረግ በቅንጅት እየሠሩ ይገኛሉ” ብለዋል።

ግለሰቦች ስማቸውን እየቀያየሩ የቁጠባ ደብተሩን በማዘጋጀት ገንዘቡን ለጥፋት ለማዋል ሲንቀሳቀሱ እንደተደረሰባቸው ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።

በሴራው ከተጠረጠረ አንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት 1 ሚሊዮን 300 ሺህ ብር በጥሬ መገኘቱን ለኢዜአ አብራርተዋል።

እንዲሁም በከተማው የአንድ ሆቴል ባለቤት በሆነ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ከ60 በላይ ገጀራ እና ቢላዋ መገኘቱን ኮሚሽነር አብዱልአዚም አመልክተዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule