
ቦርዱ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሶስት ፓርቲዎችን ላይ በቦርዱ የትግራይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቀረቡ መረጃዎች እና ሌሎች ጥቆማዎች መሰረት ተጨማሪ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት ስለእንቅስቃሴያቸው ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቷል። ትእዛዝ የተሰጣቸው ፓርቲዎችም የሚከተሉት ናቸው።
ሀ. “ዓሲምባ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /ዓዴፓ/”- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ እያሉ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በተካሄደ ህገወጥ ምርጫ ስለመሳተፋቸው
ለ. “ብሔራዊ ባይቶ አባይ ትግራይ /ባይቶና/” – በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ እያሉ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በተካሄደ ህገወጥ ምርጫ ስለመሳተፋቸው እንዲሁም የፓርቲው አመራሮች በአመጻ ተግባር በመሳተፋቸው ለቦርዱ መረጃ በመድረሱ
ሐ. “ሳልሳይ ወያነ ትግራይ /ሣወት/”- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምዝገባ ሂደት ላይ እያሉ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በተካሄደ ህገወጥ ምርጫ ስለመሳተፋቸው እንዲሁም የፓርቲው አመራሮች በአመጻ ተግባር በመሳተፋቸው በቦርዱ መረጃ በመድረሱ
እነዚህ ህወሃት ላካሄደው የጨረቃ ምርጫ ጠፍጥፎ የሠራቸው በመሆኑ ዐውራው ሲሞት እነሱም ይቀጥላሉ የሚል ግምት ባይኖርም እንደታዘዙት ማብራሪያ ካልሰጡ ቦርዱ ያፈርሳቸዋል። (ምንጭ የምርጫ ቦርድ ፌስቡክ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply