
በኢትዮጵያና በውጪ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያ የሃሰት መረጃ በማሰራጨትና የበርካታ ሰዎችን ትኩረት በመሳብ በርካታ ገቢ የሚያስገኝ ተከታታይ መሰብሰብ ያልተለመደ ተግባር አይደለም።
በተለይ ግን ብዙ ተከታይ አለን በሚሉ ዘንድ ይህ በተደጋጋሚ ሲከሰት መስተዋሉ የሞራልም የስብዕናንም መዝቀጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው።
ህወሓት በአገራችን ሕዝብ ላይ ካደረሰው የግብረገብነት ዝቅጠት ወደ ተሻለ መንገድ ለመሄድ ጥረት እየተደረገ ባለበት ወቅት በሃሰት መረጃ የሰዎችን ቀልብ በመሳብ እና ክሊክ በማግኘት ይህም ደግሞ የሚያስገኘውን ተራ ጥቅም ብቻ በማየት ለዚህ ዓይነት ርካሽ ሥራ መሠማራት ውርደት ነው።
በኢትዮጵያ የሚወጡትን የሐሰት መረጃዎች እያነፈነፈ የሚያጋልጠው Ethiopia Check “ዘሐበሻ” እና “Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ” የተባሉ “በሚዲያ” ስም የሚጠሩ ማክሰኞ ያተሙትን መረጃ የሐሰት መሆኑን አረጋግጦባቸዋል።

Ethiopia Check፤ ዘ-ሐበሻ ስላወጣው የሐሰት መረጃ ይህንን ብሏል፤
አቶ ልደቱ አያሌው ዛሬ ከእስር እንደተፈቱ ይህ ከ1 ሚልዮን በላይ ተከታይ ያለው ዘ-ሀበሻን ጨምሮ በበርካታ ገፆች ተሰራጭቷል።
እውነታው ግን ዛሬ (ማክሰኞ) “በመምሸቱ ምክንያት” የዋስትና ማቅረብ ሂደቱን መጨረስ እንዳልተቻለ እና በነገው እለት ግን ሊፈፀም እንደሚችል የኢዴፓ ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደሰ በስልክ ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቀዋል።
“የፍርድ ቤት ማዘዣውን አግኝተናል፣ አቶ ልደቱ ወዳሉበት ማረፊያ ስንደርስ ግን መሸ። ነገ ይፈፀማል ብለን እንጠብቃለን” ብለው ነግረውናል።
“(በዘሐበሻ) የተሰራጨው ፎቶ ዛሬ አቶ ልደቱ ከማረፊያ ቤት ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ የሚያሳይ ነው፣ እውነታው ይህ ነው እንጂ አቶ ልደቱ ዛሬ አልተፈቱም” ብለው አስረድተዋል።
አቶ ልደቱ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲወጡ ዛሬ የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስኖ ነበር።
‘Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ’ ስላተመው የሐሰት መረጃ ደግሞ Ethiopia Check ይህንን ብሏል፤
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ባለው ኩዋዙሉ ናታል ግዛት፣ በፖሜሮይ እና ደንዲ መሀል ባለችው ኢብሆቪኒ መንደር ዛሬ የተነሳ ፎቶን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተከሰተ ተደር ጎ ‘Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ’ በተባለ ገፅ ማምሻውን ቀርቧል።
በፎቶሾፕ የሚቀናበሩ እንዲሁም ሌላ ሀገር ተከስተው ሀገር ውስጥ እንደተደረጉ የሚቀርቡ ፎቶዎችን የጉግልን ወይም TinyEye የተባለውን ድረ-ገፅ በመጠቀም ሼር ከማረግዎ በፊት ያጣሩ።
ይህንን መረጃ የሚያነቡ ሁሉ @EthiopiaCheck የቴሌግራም አካውንት (https://t.me/ethiopiacheck) በመቀላቀል ራሳቸውን ከሐሰት መረጃ እንዲከላከሉ የዝግጅት ክፍላችን ይመክራል።
ጎልጉል የድረጽ ጋዜጣ
ድንቄም የሃሰት መረጃ ! ቄሮ የተባለው አውሬ የሰውን ልጅ በመጥረቢያና በገጀራ አካልን ከቆራረጠ በኋላ በሞተር ሳይክል የተቆራረጠ አካልን በመኪና መንገድ ላይ ሲጎትት አልነበረም እንዴ ? ይሄ ምን ያስደንቃል ! በሻሸመኔ ፥ በዝዋይ ፥ በአሳሳና በመሳሰሉት በሰኔ 23/2012 እጅግ የከፋ ወንጀል ተፈጽሞ የለም እንዴ ? መንገድ ተቆፈረና ትልቅ ነገር አድርጋችሁ ስታቀርቡት በጣም ይገርማል ።