1. ህንፃ ተክለብርሃን ይባላል። የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 (መርካቶ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበረ በኃላ በእድገት የክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ ነው።
2. ገ/ትንሳኤ ዓርአያ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዋና ሥራ አስፈፃሚ የነበረ በእድገት የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረ በቅርብ ጊዜ ከአመራር የተቀነሰ ነው።
ህብረተሰቡም ካሁን ቀደም ህዝብን እናገለግላለን በማለት ከተማችንን የእኩይ ተግባራቸው ማስፈጸሚያ ስፍራ ለማድረግ ከሚጥሩ ጸረሰላም አካላት በመራቅ የተለዩ እንቅስቃሴዎችን በተለይ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት ፣ በሆቴሎች ፣በመዝናኛ ስፍራዎች እና በትራንስፖርት ስፍራዎች አጠራጥሪ ነገር ካጋጠመ በአካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ እና የጸጥታ አካል ማሳወቅ ይገባል።
በተጨማሪ በተለያዩ አደረጃጀት የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት አባላት፣የታክሲ ተራ አስከባሪ እና የጫኚ እና አውራጅ ማህበራት ፣የፓርኪንግ ሰራተኞች የጸጥታ አካል ጋር አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የከተማችችን ሰላም በመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። (NISS)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply