• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!

June 22, 2016 08:43 am by Editor 2 Comments

በተለያዩ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በወሳኝ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በህወሃት ውስጥ ያለው ፍርሃቻና አለመረጋጋት ለሁኔታው አስገዳጅነት ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡ ህወሃት ለዓመታት ያገለገሉትን ሎሌዎች የማያምናቸው ከሆነ እነርሱም “አለመታመናቸውን” ማሳየት ይገባቸዋል፡፡

በአሜሪካ፤ በአውሮጳ፤ በአውስትራሊያና በኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በቅርቡ ወሳኝ በሆኑ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ መታሰቡን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አስታውቀዋል፡፡ ለመረጃው ቅርብ እንደሆኑና የአገራቱም ዝርዝር እንዳላቸው የተናገሩት መረጃ አቀባይ የሹምሽሩ ምክንያት ይህ ነው ተብሎ በውል ባይታወቅም ህወሃት ከውስጥና ጫና ተጠቃሽ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡

በኢህአዴግ ተለጣፊና ድቃይ ድርጅቶች ታቅፈው የሥርዓቱ ሎሌ የሆኑት አምባሳደሮች በመጪዎቹ ሳምንታትና በሐምሌ ወር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባና ግምገማ ተብሎ ሽፋን የሚሠጠው ይኸው አምባሳደሮችን የመጥራት ውሳኔ በህወሃት ሰዎች የተቀነባበረና የትኞቹን አምባሳደሮች በማን ለመተካት እንደታሰበ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፡፡ በዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ህግጋት መሠረት የሚነሱት አምባሳደሮች መረጃ ለየአገራቱ ደርሷል፡፡

ለ25 ዓመታት እጅግ አሰቃቂ ወንጀሎችን በመፈጸም በነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን በፍግ እየገዛ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር ከፍተኛ ችግር ውስጥ በሚወድቅበት ጊዜ ታማኝ የትግራይ ተወላጆችን በተለይም ነባር ታጋዮች ላይ አመኔታውን በማድረግ “ክፉ ጊዜያትን” ሲያልፍ ቆይቷል፡፡ የአሁኑም ጉዳይ ከዚህ የተለየ እንዳልሆነ ነገራል፡፡

በተለይ በሰብዓዊ መብት ረገጣ እያደረሰ ያለው ግፍ ከበቂ በላይ በሆነ ማስረጃ በተደጋጋሚ እየወጣበት ባለበት ባሁኑ ጊዜ የወደፊቱ ሁኔታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው መመለስ ያለበት ጥያቄ ሆኗል፡፡ ለዚህም ይመስላል በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከአማራው ክልል ጋር ተያይዞ ያለውን አደገኛ ሁኔታ ለማምከን የኤርትራ ካርዱን የመዘዘው በማለት አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ ወራትን ያስቆጠረው የኦሮሞ ወጣቶች ተቃውሞ ከሁሉም በላይ አረመኔነቱንና ለሥልጣኑ ሲል የማይፈጽመው ወንጀል እንደሌለ በግልጽ ያሳየ መሆኑን ሰሞኑን የወጣው የሰብዓዊ መብት ተመልካቹ መ/ቤት (ሂውማን ራይትስ ዎች) ዘገባ ያሳያል፡፡

በተለይም በያዝነው ዓመት ጥር ወር አካባቢ የአውሮጳ ፓርላማ ኢህአዴግን “ልክ የሚያስገባ” ባለ 19 ነጥብ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ውሳኔው ኢህአዴግ “ልክ ሊገባ ይሆን” የሚል አመለካከት መጫሩን ጎልጉል ጠቅሶ በጻፈበት ወቅት “ረቂቁ ለውይይት እንዳይቀርብ የቻሉትን ያህል የጣሩት ቴድሮስ አድሃኖም “ዲፕሎማሲያቸው” አለመሥራቱን፤ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ውሳኔው “ውስጡ በብረት የተወጠረ የቦክስ ጓንቲ ነው” ማለታቸውን ጨምሮ ዘግቦ ነበር፡፡ ይህ በዝርዝር መረጃ ቀርቦበት ለውሳኔ የበቃው ሰነድ ቀኑን ጠብቆ ህወሃት ላይ ሰይፉን እንደሚመዝ የወንጀሉ ተዋናዮች ከማንም በላይ የሚረዱት እውነታ ሆኗል፡፡

በአሜሪካ፤ ወሳኝ በሆኑ የአውሮጳ ከተሞች (ህብረቱ ያለበትንም ጨምሮ) እንዲሁም በኢትዮጵያ አጎራባች አገራት ያሉ አምባሳደሮች በታማኝ የህወሃት ተጋዳላዮች ለመተካት መታሰቡ የዲፕሎማሲው ተጽዕኖ ያስከተለው ጫና ብቻ ሳይሆን በህወሃት ውስጥ ሌላም ፍርሃቻ ስለአለ ነው በማለት ጉዳዩን ከሌላ አንጻር የሚመለከቱ ይናገራሉ፡፡

አሊ ኦጃሊ
አሊ ኦጃሊ

ምዕራባውያን ኃይላት ትኩረታቸውን ሊቢያ ላይ አድርገው ጋዳፊን ከሥልጣን ለማውረድ እንቅስቃሴ በጀመሩበት ወቅት ዓመጹ እየተፋፋመ ሲሄድ በየአገሩ የነበሩ የጋዳፊ ታማኞች መክዳታቸው ይታወሳል፡፡ ጋዳፊ ህይወታቸው በOctober 2011 ከማለፉ ስምንት ወራት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ ታማኝ አድርገው ያስቀመጧቸው አምባሳደር አሊ ኦጃሊ ጋዳፊን መክዳታቸው ይታወቃል፡፡ ለጋዳፊ ታማኝ በመሆን አርባ ዓመት ያህል ያገለገሉት አምባሳደሩ በወቅቱ ከከዱ በኋላ የአማጺውን ኃይል ተቀላቅለው ነበር፡፡ ከዚህ አልፈው በአሜሪካ የአማጺው አፈቀላጤና ተወካይ በመሆን ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ የጋዳፊ መውደቅ እውን እየሆነ ሲሄድ አሜሪካ መልሳ በቦታቸው አስቀምጣቸው ነበር፡፡ ከዚህ አንጻር ህወሃትን ያስፈራው ይህንን መሰል የፖለቲካ ቁማር እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከሎሌነት ባላለፈ አገልግሎት የሚሰጡትን “የራሴ፤ ታማኞቼ” ከሚላቸው ጋር ፈጽሞ እኩል ሊያደርጋቸው የማይፈልገው ህወሃት የፖለቲካው ትኩሳት አቅጣጫውን የቀየረ ዕለት የአሊ ኦጃሊን መንገድ ሊከተሉ ይችላሉ ብሎ የጠረጠራቸውን በቶሎ ለመተካት መወሰኑ “ከጋዳፊ ተምረናል” የሚል እንድምታ እንዳለው ይነገራል፡፡ በየትኛውም የለውጥ እንቅስቃሴ ጊዜ በተለይ በጎረቤትና በኃያላን አገራት ያሉ አምባሳደሮች መክዳት አልፎም ንቅናቄውን መቀላቀል የአምባገነኖችን ዕድሜ በማሳጠር በኩል ቁልፍ ሚና ይኖረዋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ህወሃት ምዕራባውያን በተገኘው አጋጣሚ ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት በመገመት ይህንን መሰሉን ጥንቃቄ ማድረጉ ሥልጣኑን እንዴት እንደሚንከባከብ የሚያሳይ ነው፡፡ በተለይ የኦህዴድ መሸርሸርና በክልሉ ያለው ዓመጽ እስካሁን አለመብረድ ከአምባሳደር ጀምሮ እስከ በታች እርከን የቆንስላ ተግባራት ላ የተሰማሩ ኦሮሞ ዲፕሎማቶችንና ሠራተኞችን በዓይነቁራኛ እንዲታዩ እያደረጋቸው ነው፡፡ ከዚህ አንጻር “ለችግር ጊዜ አትታመኑም” ተብለው እንደሸቀጥ እንዲመለሱ የሚጠሩት አምባሳደሮች ቀን ፊቷን ሳታዞርባቸው ለምንስ በእርግጥ “የማይታመኑ መሆናቸውን” ለህወሃት አያሳዩትም በማለት የዜናው አቀባይ ለዲፕሎማቶቹ ጥሪ አዘል ምክር ለግሰዋል፡፡   (ፎቶ: ያለፈው አመት ሹመኞች)


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. gud says

    June 25, 2016 07:06 pm at 7:06 pm

    Shabian days are numbered !

    With that the days of parasite diasporas will come to an end ! Death to HGDF and it’s brainless servants !

    Reply
  2. Kebede says

    July 7, 2016 07:30 pm at 7:30 pm

    This is just another creative essay writing. Just propoganda.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule