ሕዝባዊ አመጹ ያመጣውን ቀውስ ተከትሎ በህወሃት ከፍተኛ አመራር ውስጥ ከፍተኛ መበጣበጥ እና የርስ-በርስ ፍጥጫ መከሰቱን ከታመነ የውስጥ አዋቂ ምንጭ መረጃ ደርሶናል።
“አመራሩ ክፉኛ ከመከፋፈሉ የተነሳም የርስበርሱ ችግራቸው ላይ ተወጥረዋል” ይላል መረጃው። ቀንደኞቹ የህወሃት አባላት ስርዓቱ እንዳበቃለት ስለተገነዘቡ ንብረት እና ልጆቻቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው።
ሕዝቡ ሁሉ እንደተፋቸው በግልጽ እየነገራቸው ስለተገነዘቡ፤ የህወሃት የደህንነት አባላት ሕዝቡን ትተው የራሳቸውን ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሰልሉ ተነግሯቸዋል። “ተጠርጣሪ” የኦህዴድ እና ብአዴን አባላት በነዚህ ሰላዮች ስለተከበቡ በፍርሃት መወጠራቸውን ከራሳቸው አንደበት እየተሰማ ነው።
የርስበርስ ውጥረቱ የተከሰተው ወቅታዊ ችግሩን እንዴት እንፍታ በሚለው ሃሳብ ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በሙሉ በመጥራት የአንድነት መንግስት እንመስርት በሚለው ሃሳብ ላይ ስምምነት ተወያይተው ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ በዚህ የተከፋው ቡድን ባነሳው ተቃውሞ እንደሆነ መረጃው ጠቁሟል። ይህ ቡድን ችግሩን በውይይት ሳይሆን በመሳሪያ ሃይል ለመፍታት ለብቻው መክሯል። ውይይታቸው ሁሉ ዛቻ እና ስድብ አዘል ንግግሮችም እንደነበሩበት ምንጫችን ጠቅሷል።
በውሳኔው መሰረት ተቃዋሚዎች በቤተመንግሥት ይጋበዛሉ ተብሏል። ለማዘናጋትም ተብሎ ይሁን ወይንም በፍርሃት የመጣው ይህ ሃሳብ ግዜው አልፎበታል።
በሌላ በኩል ደግሞ ወታደራዊ ካምዮኖች የአጋዚ ወታደሮችን እና ከባድ መሳርያ ጭነው ከህወሃት ነጻ ወደ ወጡት ስፍራዎች እየጎረፉ ነው። ማብቅያ የሌላቸው እነዚህ የጭነት መኪናዎች እየተጓዙ ያሉት የውጭ ጠላትን ለመመከት ሳይሆን የገዛ ሕዝብን ለመደምሰስ ታቅዶ እና ታስቦ ነው። አለ የተባለው ሁሉ የህወሃት ሰራዊት ወደ አማራው ሕዝብ ተልኮ መንገድ ላይ ታግቷል። በአሁኑ ሰአት ሌላው አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ እንኳን ቢኖር ከአጋዚ ነጻ ይመስላል።
ሕዝባዊ አመጽ በተቀጣጠለባቸው ስፍራዎች (በተለይ በጎንደር እና ጎጃም) ያሉ የሰራዊት አባላት በሕዝቡ ላይ እንዲተኩሱ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። ችግር ግን አለ። ይህ ትዕዛዝ ከአካባቢው የሰራዊቱ አባላት ተቀባይነት አላገኘም። ልዩ ፖሊስ በመባል የሚታወቁት የአካባቢው ፖሊሶች እና ወታደሮች ከህዝብ ጎን መቆምን መርጠዋል። በአካባቢው ያሉ የሰራዊቱ አባላት በህዝብ ላይ አንተኩስም ብለዋል። ይልቁንም ልዩ-ፖሊሶች ህዝብን ከአጋዚ ገዳዮች በመከላከል ላይ እንዳሉ ነው የሚሰማው።
በተለይ በጎንደር እና ጎጃም ሕዝቡ አስቀድሞ መንገዶችን በሙሉ ዘግቶ የአጋዚ ገዳዮች ወደ ስፍራው እንዳይገቡ አድርጓቸዋል። ይህ ባለመሳካቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የውስጥ በረራውን አቁሞ የአጋዚ ሠራዊትን ወደ ባህርዳር እንዲያመላልስ ታዝዟል። በበርካታ ስፍራዎችም ሕዝቡ ራሱን ለመከላከል በመፋለም ላይ ይገኛል።
ሃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ፤ በምክትሉ ነው የሚመራው። ለእያንዳንዱ የሚፈስ ደም፣ ለእያንዳንዱ የጦር ወንጀል፣ ለእያንዳንዱ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል … የመጀመሪያ ጠያቂው እሱ መሆኑን ዘንግቶት ግን አይደለም።
ላለፉት 25 ዓመታት በጥቂቶች የተረገጠ ህዝብ ብሶቱ ከመብዛቱ የተነሳ ገንፍሎ ወጥቷል። (አብዛኛዎቹ) የጎንደር እና ጎጃም ክፍለ ሃገራት ከዘረኛው የህወሃት አገዛዝ ነጻ ወጥተዋል። በአንዳንድ ስፍራዎች ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ቢሆንም ሁኔታው ለህወሃት እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነበት ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ውጥረት እንደሰፈነ ነው። በሃገሪቱ የሚያስፈራ ድባብ ሰፍኗል። የኢኮኖሚው እንቅስቃሴ በእጅጉ እየተዳከመ ነው። የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና ኢንተርኔት መቋረጥ ህዝቡን እጅግ አስመርሮታል። አንድ ሊፈነዳ ያለ ነገር እንዳለ ይሰማል። ሕዝባዊ አመጽ በቀጠሮ አይመጣም። ብሶቱ መጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርስ ይፈነዳል።
የአዲስ አበባ ሕዝብ ለሰዓታት ከቤቱ ወጥቶ በሩ ላይ ብቻ ቢቆም፣ አሁን የሚደነፉበት ዘራፊዎች ሁሉ ሃገር ለቀው ይጠፋሉ።
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
rasdejen says
ጀግናዉ ዎሎ፤ጀግናዉ ሸዋ ሆይ፥፡
የህወሃት ገዳይ ዎታደር አና ኣጋዜ ባንተ በኩል ኣድርጎ በጎጃምና በጎንድር ዎገኖችህን ሊጨፈጭፍ አየጎረፈ ነዉ። በምታዉቀዉ ጋራ፣ሸንተረር፣ሸለቆና መሿለኪያ አያጠመድክ መንገድ ላይ አንድታስቀረዉ በሰፊዉ ዎገንህ ስም ይህን ጥሪ ኣቀርብልሃለሁ። ተነስ የጀግንነትና ሰዉ ኣድን ታሪክ ኣሁን ስራ!!!! ተ….ነ…………ስ………….!!!!!!!!!!!!!!
ጀግናዉ ጋየንት አና ጀግናዉ የፋርጣም ህዝብ ሾልኮ የሚሄደዉን ወገን ኣራጅ ሃይል እንድታስቀረዉ ጥብቅ ወገናዊ ጥሪ በወገን ስም ከአክብሮት ጋር ኣቀርባለሁ!!!!!!!!!!!!!
እንዴ፤አትነሳም… እንዴ? https://www.youtube.com/watch?v=KmLwEgwBey8
ለወገን ደራሽ ወገን ነዉ
ይህ ጥሪ ከፍተኛ እድልም ነዉ፤ ኣጥብቀዉ እየተመኙ ያላገኙት በዙወች ነን
እድልም ነዉና ኣይለፍችዉ፤ ኣይለፍሽ፤ኣይለፍህ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
Lusif says
Obviously. Tyrany just doesn’t’t go away without futile and desperate last attempt. That is what we are seeing right now. The ruling party is on life support—– the military and security tube. Most staff members of the military are to busy with moving, hiding and transferring there looted wealth and properties. A lot of them do not seem fully engaged in defending the status quo, rather they seem looking a way out.
Those who are financially well off are arguing for a peaceful transition and transfer of power so that the can enjoy the wealth they have already accumulated without raising any alarm.
What I am trying to show is the ruling party is currently disorganized and in disarray. The situation is very fertile. The conditions are favorable for total change. What everybody needs to do is to come together, keep the momentum and increase the pressure stronger and stronger.
I live in the country. I have lots of friends and business acquaintances. Every individual I know have become desperate. Each seems seeking information and help to know where all these end up, what the future would look like. And most of all most are worried how society would react towards them. Everybody is running to save the self and immediate family members.
In general the ruling party is in its weakest links and shape. Time is precious. Let everybody utilize it wisely.