• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሕወሃት ብጥብጥ እና ሽሽት- ከውስጥ አዋቂ ምንጭ

August 30, 2016 02:42 am by Editor 2 Comments

ሕዝባዊ አመጹ ያመጣውን ቀውስ ተከትሎ በህወሃት ከፍተኛ አመራር ውስጥ ከፍተኛ መበጣበጥ እና የርስ-በርስ ፍጥጫ መከሰቱን ከታመነ የውስጥ አዋቂ ምንጭ መረጃ  ደርሶናል። ­­­

“አመራሩ ክፉኛ ከመከፋፈሉ የተነሳም የርስበርሱ ችግራቸው ላይ ተወጥረዋል” ይላል መረጃው። ቀንደኞቹ የህወሃት አባላት ስርዓቱ እንዳበቃለት ስለተገነዘቡ ንብረት እና ልጆቻቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው።

ሕዝቡ ሁሉ እንደተፋቸው በግልጽ እየነገራቸው ስለተገነዘቡ፤ የህወሃት የደህንነት አባላት ሕዝቡን ትተው የራሳቸውን ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሰልሉ ተነግሯቸዋል። “ተጠርጣሪ” የኦህዴድ እና ብአዴን አባላት በነዚህ ሰላዮች ስለተከበቡ በፍርሃት መወጠራቸውን ከራሳቸው አንደበት እየተሰማ ነው።

የርስበርስ ውጥረቱ የተከሰተው ወቅታዊ ችግሩን እንዴት እንፍታ በሚለው ሃሳብ ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በሙሉ በመጥራት የአንድነት መንግስት እንመስርት በሚለው ሃሳብ ላይ ስምምነት ተወያይተው ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ በዚህ የተከፋው ቡድን  ባነሳው ተቃውሞ እንደሆነ መረጃው ጠቁሟል። ይህ ቡድን ችግሩን  በውይይት ሳይሆን በመሳሪያ ሃይል ለመፍታት ለብቻው መክሯል። ውይይታቸው ሁሉ ዛቻ እና ስድብ አዘል ንግግሮችም እንደነበሩበት ምንጫችን ጠቅሷል።

በውሳኔው መሰረት ተቃዋሚዎች በቤተመንግሥት ይጋበዛሉ ተብሏል። ለማዘናጋትም ተብሎ ይሁን ወይንም በፍርሃት የመጣው ይህ  ሃሳብ ግዜው አልፎበታል።

በሌላ በኩል ደግሞ ወታደራዊ ካምዮኖች የአጋዚ ወታደሮችን እና ከባድ መሳርያ ጭነው ከህወሃት ነጻ ወደ ወጡት ስፍራዎች እየጎረፉ ነው። ማብቅያ የሌላቸው እነዚህ የጭነት መኪናዎች እየተጓዙ ያሉት የውጭ ጠላትን ለመመከት ሳይሆን የገዛ ሕዝብን ለመደምሰስ ታቅዶ እና ታስቦ ነው። አለ የተባለው ሁሉ የህወሃት ሰራዊት ወደ አማራው ሕዝብ ተልኮ መንገድ ላይ ታግቷል። በአሁኑ ሰአት ሌላው አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ እንኳን ቢኖር ከአጋዚ ነጻ ይመስላል።

ሕዝባዊ አመጽ በተቀጣጠለባቸው ስፍራዎች (በተለይ በጎንደር እና ጎጃም) ያሉ የሰራዊት አባላት በሕዝቡ ላይ እንዲተኩሱ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። ችግር ግን አለ። ይህ ትዕዛዝ ከአካባቢው የሰራዊቱ አባላት ተቀባይነት አላገኘም። ልዩ ፖሊስ በመባል የሚታወቁት የአካባቢው ፖሊሶች እና  ወታደሮች ከህዝብ ጎን መቆምን መርጠዋል። በአካባቢው ያሉ የሰራዊቱ አባላት በህዝብ ላይ አንተኩስም ብለዋል። ይልቁንም ልዩ-ፖሊሶች ህዝብን ከአጋዚ ገዳዮች በመከላከል ላይ እንዳሉ ነው የሚሰማው።

በተለይ በጎንደር እና ጎጃም ሕዝቡ አስቀድሞ መንገዶችን በሙሉ ዘግቶ የአጋዚ ገዳዮች ወደ ስፍራው እንዳይገቡ አድርጓቸዋል። ይህ ባለመሳካቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የውስጥ በረራውን አቁሞ የአጋዚ ሠራዊትን ወደ ባህርዳር እንዲያመላልስ ታዝዟል። በበርካታ ስፍራዎችም ሕዝቡ ራሱን ለመከላከል በመፋለም ላይ ይገኛል።

ሃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ላይ ቁጭ ብሎ፤ በምክትሉ ነው የሚመራው። ለእያንዳንዱ የሚፈስ ደም፣ ለእያንዳንዱ የጦር ወንጀል፣ ለእያንዳንዱ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል … የመጀመሪያ ጠያቂው እሱ መሆኑን ዘንግቶት ግን አይደለም።

ላለፉት 25 ዓመታት በጥቂቶች የተረገጠ ህዝብ ብሶቱ ከመብዛቱ የተነሳ ገንፍሎ ወጥቷል። (አብዛኛዎቹ) የጎንደር እና ጎጃም ክፍለ ሃገራት ከዘረኛው የህወሃት አገዛዝ ነጻ ወጥተዋል። በአንዳንድ ስፍራዎች ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ ቢሆንም ሁኔታው ለህወሃት እጅግ አስቸጋሪ እንደሆነበት ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች ውጥረት እንደሰፈነ ነው። በሃገሪቱ የሚያስፈራ ድባብ ሰፍኗል። የኢኮኖሚው እንቅስቃሴ በእጅጉ እየተዳከመ ነው። የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና ኢንተርኔት መቋረጥ ህዝቡን እጅግ አስመርሮታል። አንድ ሊፈነዳ ያለ ነገር እንዳለ ይሰማል። ሕዝባዊ አመጽ በቀጠሮ አይመጣም። ብሶቱ መጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርስ ይፈነዳል።

የአዲስ አበባ ሕዝብ ለሰዓታት ከቤቱ ወጥቶ በሩ ላይ ብቻ ቢቆም፣  አሁን የሚደነፉበት ዘራፊዎች  ሁሉ ሃገር ለቀው ይጠፋሉ።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. rasdejen says

    August 31, 2016 10:26 am at 10:26 am

    ጀግናዉ ዎሎ፤ጀግናዉ ሸዋ ሆይ፥፡

    የህወሃት ገዳይ ዎታደር አና ኣጋዜ ባንተ በኩል ኣድርጎ በጎጃምና በጎንድር ዎገኖችህን ሊጨፈጭፍ አየጎረፈ ነዉ። በምታዉቀዉ ጋራ፣ሸንተረር፣ሸለቆና መሿለኪያ አያጠመድክ መንገድ ላይ አንድታስቀረዉ በሰፊዉ ዎገንህ ስም ይህን ጥሪ ኣቀርብልሃለሁ። ተነስ የጀግንነትና ሰዉ ኣድን ታሪክ ኣሁን ስራ!!!! ተ….ነ…………ስ………….!!!!!!!!!!!!!!

    ጀግናዉ ጋየንት አና ጀግናዉ የፋርጣም ህዝብ ሾልኮ የሚሄደዉን ወገን ኣራጅ ሃይል እንድታስቀረዉ ጥብቅ ወገናዊ ጥሪ በወገን ስም ከአክብሮት ጋር ኣቀርባለሁ!!!!!!!!!!!!!

    እንዴ፤አትነሳም… እንዴ? https://www.youtube.com/watch?v=KmLwEgwBey8

    ለወገን ደራሽ ወገን ነዉ
    ይህ ጥሪ ከፍተኛ እድልም ነዉ፤ ኣጥብቀዉ እየተመኙ ያላገኙት በዙወች ነን
    እድልም ነዉና ኣይለፍችዉ፤ ኣይለፍሽ፤ኣይለፍህ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    Reply
  2. Lusif says

    August 31, 2016 05:22 pm at 5:22 pm

    Obviously. Tyrany just doesn’t’t go away without futile and desperate last attempt. That is what we are seeing right now. The ruling party is on life support—– the military and security tube. Most staff members of the military are to busy with moving, hiding and transferring there looted wealth and properties. A lot of them do not seem fully engaged in defending the status quo, rather they seem looking a way out.
    Those who are financially well off are arguing for a peaceful transition and transfer of power so that the can enjoy the wealth they have already accumulated without raising any alarm.
    What I am trying to show is the ruling party is currently disorganized and in disarray. The situation is very fertile. The conditions are favorable for total change. What everybody needs to do is to come together, keep the momentum and increase the pressure stronger and stronger.
    I live in the country. I have lots of friends and business acquaintances. Every individual I know have become desperate. Each seems seeking information and help to know where all these end up, what the future would look like. And most of all most are worried how society would react towards them. Everybody is running to save the self and immediate family members.
    In general the ruling party is in its weakest links and shape. Time is precious. Let everybody utilize it wisely.

    Reply

Leave a Reply to Lusif Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule