• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ለብቻው ቤተ-መንግስቱን ያንቀጠቀጠ ብላቴና፣ ቴዲ አፍሮ

September 3, 2017 02:16 pm by Editor Leave a Comment

በነዚያ የነተቡ ብዕሮች “ተራራውን ያንቀጠቀጠ” እየተባሉ ሲወደሱ የነበሩ ሁሉ እነሆ በአንድ ብላቴና ሲንቀጠቀጡ ከማየት የበለጠ ምስክር ከየትም ሊመጣ አይችልም። የ”ኢትዮጵያ” ስም ሲጠራ ብርክ እንደያዘው የሚሽመደመዱ፤ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት እያልን በጣት የምንቆጥራቸው የጥላቻና የበቀል ጉግማንጉጎች ለመሆናቸውም ትውልድን ደፍሮ ይናገርላቸዋል። የዚህ ቡድን አባላት  ከመጠን ያለፉ ጭቃዎች መሆናቸውን እንኳ ለማወቅ ራሳቸውን በመስታወት የሚመለከቱ አይመስልም።

መቶ ሚሊዮን ሕዝብ እየመራ ያለው ይህ  ቡድን በየትኛውም መመዘኛ ቢለካ አርቆ ማሰብ እና አስተዋይነት ይጎድለዋል። አስተዋይነት ደግሞ የታላላቆች ውድ ስጦታ ስለሆነ ከርካሽ ሰዎች አይጠበቅም።

አበው ትተውልን ያለፉት አንድ ቅርስ፣ ያቺ የቀስተደመና ተምሳለት፣ ያቺ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ስትነሳ አጋንንት እንደለከፈው እርያ የሚክለፈለፉ የዘመናችን ጉዶች…. አንድ ነገር እንዳላቸው አንክድም። የቤተ-መንግስቱ ተራ ደርሷቸው የተቀመጡት ትንሾች ያላቸው አንድያ ነገር መሃይምነት ብቻ ነው። ግና ኮንሰርት በመከልከል ቴዲን የጎዱ እየመሰላቸው ይልቅ ተወዳጅነቱን በእጥፍ ጨመሩለት።

አንድ ኢትዮጵያዊ፣ ቴዲ አፍሮ ሲያርበተብታቸው አየን። በጩኸት ሳይሆን በዝምታ፣ በሰይፍ ሳይሆን በዘለሰኛ፣ በጥላቻ ሳይሆን በፍቅር ብቻ የሚሰባብራቸው፣ ሰባብሮም ድል የሚያደርግ ጀግና። እንግዲህ በዚህ አይነት እጅግ በወረደ ተራ ነገር ይህን ድምጻዊ በገንዘብ ሊጎዱት ይችሉ ይሆናል። የህይወት ስንቅ የሆነው ፍቅር ግን ወዲህ ነው። የማይለወጥ የሚሊዮኖችን ፍቅር። እነ ደብረጽዮን አቅሙ ኖሯቸው ይህንን ቢነፍጉት ኖሮ ቴዲ ሊጎዳ ይችል ነበር። አንድ በቀነሱበት ቁጥር፣ በመቶ እጥፍ እንደሚጨመርበት ግን መቼም ሊያስተውሉት አይችሉም።

አያሌ እንቅፋቶችን አልፎ ዛሬ ምሽት ላይ በሂልተን ሆቴል ሊደረግ የነበረው የ”ኢትዮጵያ” አልበም ምረቃ  ባይስተጓጎል ነበር የሚገርመን። ምክንያቱም አልበሙ “ኢትዮጵያ”፣ መልእክቱም ፍቅር እና አንድነት ነዋ! ይህ ደግሞ ኢትዮጵያን ሳይወድዷት ለሚገዙዋት ራስ ምታት ነው። ባንዲራዋን የሚጠሉ ሁሉ የሶስቱ ቀለማት መውለብለብ ያሳምማቸዋል።

ቴዲ አፍሮ፣ ፓርቲ ሳያቋቁም፣ በሶስትም ሆነ ባራት ሳይደራጅ፣ በአንዲት አልበም ብቻ ቤተ-መንግስቱን ያሸበረና የነቀነቀበት ምስጢር ይኸው ነው። የፈሪ ዱላቸውን የመምዘዛቸው ምስጢርም ኢትዮጵያዊነትን የመስበኩ ወንጀል ነው። አንድ ዜማ ወደ ፍርሃት ጥግ ሲገፋቸው የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ አሳጣቸው። ኮንሰርቱን ሲያግዱ፣ የምርቃቱን ዝግጅት ሲከለክሉ፣ የባንዱን አባል ከሃገር ሲያባርሩ…

እርግጥ ነው። ብላቴናው ላውንቸር ወይንም ሚሳየል ሳይሆን ኢትዮጵያን ከጀርባው ይዟል። ዛሬ በዙፋን ሆነው ይፈርዳሉ። የግዜ ጀግኖች አሁንም በንጹሃን ዜጎች በድፍረት ፍርደ-ገምድል ውሳኔ ይበይናሉ። በዚህ ሁኔታ ለዘልዓለም የሚዘልቁም ይመስላቸዋል። ይህንን ሲያድደርጉ  የሚተማመኑበት አንድ ነገር አለ። ፈጣሪን አይደለም። ሕዝብንም አይደለም። ጠመንጃቸውን ነው የታመኑበት። “የቆሙ የመሰለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” ይላልና ቃሉ የዛሬ ፈራጆች ነገ እንደማይወድቁ ምንም ዋስትና የለም። በእርግጠኝነት የምንናገረው አንድ ነገር አለ። ትውልድ አምጿል። ልብ በሉ! በመጭው አመት አንድ አዲስ ነገር እናያለን። ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ይጠብቅ።

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule