እጅግ መረን በለቀቀ ሁኔታ የኢትዮጵያን የመንግሥት ሥልጣን ተቆጣጥሮ የነበረው የተገንጣይ ወንበዴዎች ቡድን እና በዚሁ የተገንጣይ ቡድን ስም አገር ሲገዛ የኖረው ትህነግ/ህወሓት በአሁኑ ወቅት በሚኒስትሮች ም/ቤት ያለው ኅልውና ሊከሰም ጥቂት ነው የቀረው። የጠ/ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ፣ የመከላከያ (ኤታ ማዦር ሹም)፣ የማስታወቂያ (በኋላ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተባለው) ወዘተ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በብቸኝነትና በማንአለብኝነት ለበርካታ ዓመታት ሲቆጣጠር የነበረውን የተገንጣይ ቡድን በሚኒስትሮች ም/ቤት ትወክለው ነበረችው ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር ከሥልጣኗ ተወግዳለች። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የላከውን መረጃ የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አማርኛ ልሳን በፌስቡክ አረጋግጧል። የህወሓት የፖሊትቢሮ አባልና የደብረጽዮን ምክትል የሆነችው ፈትለወርቅ (ሳሞራ የኑስ ባወጣላት የበረሃ ስሟ … [Read more...] about በኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ም/ቤት የህወሓት ኅልውና እየከሰመ ነው