• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ነገሪ ሌንጮ፣ አቦይ ስብሃት በሙስና መታሰራቸውን ይንገሩን!

July 26, 2017 07:41 am by Editor 1 Comment

የነጋዴዎች አድማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ገዥው ፓርቲ ከየአቅጣጫው በመወጠሩ – የችግሩን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር አለበት። የተለመደ የፉገራ ካርዳቸውን መዘዝ አድርገው ለዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ሰጡዋቸው።

ኦቦ ነገሪ ሌንጮ 34 የመንግስት ባለስልጣናት እና ነጋዴዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ትናንት ምሽት አብስረዋል። እነማን እንደታሰሩ ግን አልገለጹም። ታሳሪዎቹን ሊያውቁዋቸው ስለማይችሉ ሊገልጹ እንደማይችሉ ግልጽ ነው። እንደወትሮው ተጽፎ የተሰጣቸውን ከማንበብ ውጭ አማራጭ የላቸውም። የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን መታሰር እንደማንኛውም ተራ ሰው በዜና የሰሙት ነገሪ ሌንጮ ምን አፍ ኖሯቸው ስለ ባለስልጣናት መታሰር ይነግሩናል? ስራዎቼን ሁሉ በግምት ነው የምሰራው – መረጃ እንኳን አይሰጡኝም የሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትርስ ምን አቅም ኖሯቸው ጉዳዩን ያስፈጽሙታል?

የሙስና ጉዳይ በየአመቱ ነው የሚነሳው። ችግር ሲመጣ እየጠበቁ ለአቅጣጫ ማስቀየርያ ይለቁብናል። አንዳንዴ በሙስና ታሳሪ ገጸ-ባህርያትን ይፈጥሩና አስቂኝ ድራማ ያሳዩናል። ሌላ ግዜ ደግሞ የንግድ ባላንጣዎቻቸውን ለመበቀል ይጠቀሙበታል። አንዳንዴም ለመታመን ሲሉ ተራ የመንግስት ሰራተኞችን እና ነጋዴዎችን ይዘው ያጉሯቸውና ግርግሩ ሲረሳሳ ደግሞ ይለቋቸዋል።

በእርግጥ የሙስና ተጠርጣሪዎችን ማሰር ቢያስቡ – መጀመርያ አቦይ ስብሀትን ወይንም አዜብ መስፍንን በማሰር ያሳዩን ነበር። ጸረ-ሙስናው ዘመቻ እውን ቢሆን ኖሮ የህወሃት የጦር አለቆች በሙሉ መኖርያቸው ቂሊንጦ በሆነ። የአቶ ስብሀት ነጋ ልጅ ተከስተ ስብሀት ነጋ እና እህት ቅዱሳን ነጋ ህልቕ መሳፍርት ንብረት ቢታገድ ነበር ጸረ-ሙስና ዘመቻ ተጀመረ ምንለው።

የሙሰኞች ንብረት ታገደ የምንለው የጄነራል ሳሞራ የኑስ፣ የሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፣ የሌ/ጄ ገዛኢ አበራ፣ የሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ፣ የሌ/ጄ ሳእረ መኮንን ቦሌ ላይ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ቤቶች ሲታገዱ ነው።

ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ፣ ሌ/ጄ ብርሃነ ነጋሽ፣ ሌ/ጄ ሳእረ መኮንን፣ ሌ/ጄ አበባው ታደሰ፣ ሜ/ጄ አብርሃ ው/ገብርኤል፣ ሜ/ጄ ዮሃንስ ገ/መስቀል፣ ሜ/ጄ ስዮም ሃጎስ፣ ሜ/ጄ ሃየሎም አርአያ፣ ሜ/ጄ ገ/እግዚአብሄር መብራቱ፣ ብ/ጄ ታደሰ ጋውና፣ ብ/ጄ ተክላይ አሽብር፣ ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳነ፣ ብ/ጄ ፓትሪስ፣ ብ/ጄ መስፍን አማረ፣ ብ/ጄ ምግበ ሃይለ፣ ብ/ጄ ሃለፎም ቸንቶ፣ ኮ/ል ታደስ ንጉሴ፣ ኮ/ል ጸሃየ መንጁስ በህዝብ ገንዘብ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ያሰሩዋቸው በሚሊዮኖች የሚገመቱ ቤቶች በወር ደሞዛቸው እንዳልሆነ ፖሊስና አቃቤ ህግ ሳያውቁት ቀርተው ነው?

እነ ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ፣ አባዲ ዘሙ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሽመልስ ኪዳኔ፣ አርከበ እቁባይ፣ አባይ ጸሃዬ፣ ገብረ መድህን ገብረ ዮሃንስ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአኤል፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ ታደሰ ሃይሌ፣ ሰምሃል መለስ ዜናዊ ከባህር ማዶ ያከማቹት በቢሊዮን የሚቆጠር የህዝብ ገንዘብ እስቲ ይታገድ እና ነገሪ ሌንጮን እንመን።

ይህን መራራ ሃቅ የሚክድ የለም። ራሳቸውም የሚሉት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲፈሩ ሲቸሩ “ሙስና አለ – ማስረጃ የለም” ብለውናል። አቦይ ስብሃት ደግሞ በሰንደቅ ጋዜጣ አዳልጧቸው “መቶ ሚልዮን የሰረቁና ያስዘረፉ፤ 10ሺህ ብር የሰረቀውን ሲያገላብጡት ሲያስፈራሩት ይታያሉ” ብለው ነበር። የየሃገራቱን የሙስና መጠን ደረጃ በየአመቱ የሚዘግበው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለዉ ተቋም ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሙስና ከሚፈፀምባቸዉ ሃገራት አንዷ መሆኗን አመልክቷል። እንደ ተቋሙ ዘገባ ከሆነ ከኢትዮጵያ በህወሃት ዘመን ተዘርፎ የወጣው ገንዘብ 17 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል። ጥናት ከተደረገባቸው 174 ሃገሮች መካከል ኢትዮጵያ 113ኛ ቦታን ይዛለች። ይህ ቁጥር መንግስታዊ ሙስናው ሃገሪቱን ምን ያህል እንደ መዥገር እመጠጠ መሆኑን ያሳየናል። ታቦ ኢምቤኪ የመሩት ሌላ ጥናት ደግሞ በአምስት ዓመታት ዉስጥ ብቻ ከኢትዮጵያ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ 10 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ወደ ዉጭ እንዲወጣ ተደርጓል።

በአንድ ወቅት በጸረ-ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናቱን ንብረት የመመዝገብ ደንብ ወጣና ስራውን ጀመረ። ብዙ የተወራለት ይህ ኮሚሽን ወደ ጀነራል ሳሞራ የኑስ ቤት ነበር ቀድሞ ያመራው። አይተ ሳሞራም የጸረ-ሙስናውን ቡድን አስቀምጦ “ስራችሁን አደንቃለሁ። ጥሩ ጅምር ነው። ግን ከላይ ጀምሩ” ብሎ ወደ አዜብ መስፍን መራቸው። ንብረት መዝጋቢዎቹ ወደ አዜብ ቤት ሳይደርሱ ግማሽ መንገድ ላይ እንደጠፉ ይነገራል። አዲዮስ ፌደራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን!

የሲቪክ ማኅበራት በነፃነት መንቀሣቀስ በማይችሉበት፣ የፕሬስ ነጸነት በታፈነበትና የህግ የበላይነት በሌለበት ሃገር ሙስናን እናጠፋለን ማለት በህዝብ ሳይሆን በራስ ላይ መቀለድ ነው የሚሆነው። አላማው ከችግሩ አቅጣጫ ለማስቀየር ከሆነ ደግሞ ሌላ ካርታ መጠቀሙ የሚበጅ ይመስላል። ደጋግማችሁ በተባላ ካርታ አትጫወቱ።

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    July 30, 2017 06:03 pm at 6:03 pm

    “ከሚኒስተሮች ይልቅ ግንዘብ ላይ ከፈተኛ ሥልጣን ያላቸው ዳይሬከተሮቶች ናቸው” ጠ/ዓ/ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ
    ” የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎች ተደርገው የሚወሰዱት ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዴኤታዎች የፖለቲካ ተሿሚዎች ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በዚህ ጉዳይ የሉበትም ባይባልም እንኳን፣ ዋነኛ ሥራቸው ፖለቲካዊ አቅጣጫ መስጠት ነው፡፡….(የፖለቲካ አቅጣጫ ማለት? ጠዋት ጠዋት ሥራ ሲገቡ የፖለቲካ ንቃት አብዮታዊ ዴሞክራሲ፤ አክራሪነት፡ጠባብነት፡ጽንፈኝነት በዴሞክራሲያዊ ብሔረትኝነት እየተቆላመጠ ኮርስ በእየሕንጻው ላይ ይሰጣል ማለት ነው!?)

    ___” ከፍተኛውን የመወሰን ድርሻ ያለው በዳይሬክተር ደረጃ ያለው ኃይል ነው፡፡ አጠቃላይ የገንዘብ እንቅስቃሴውንና በቢሮክራሲው ላይ የመወሰን ሥልጣን በእነዚህ ጫንቃ ላይ የወደቀ ነው፡፡” ታዲያ እነኝህ እየሰሩ ሌላው ጫንቃቸው ላይ ተቀምጦ የፖለቲካ ሹመኛ የሚሆነው በነጻ እያገለገለ ነው? ወይንስ ሌላው በሰራው እነሱ በታጋይ ሥም ተቀምጠው የራሳቸው ቡድን ካልተጠቀመና ከንግዱ ስላልተመሳጠረ እነኝህን በሙስና አስወግዶ የራሳቸውን የፖለቲካ አቀንቃኝ መረብ ለመዘርጋት የመንገድ ጠረጋ ነው ማለት ነው።አደለም እንዴ ዋሸን እንዴ?
    >» የህወአት/ኢህአዴግ ሙስና መር ኢኮኖሚ…ማኒፌስቶአዊ የልዩ ጥቅማጥቅም(እከክልኝ ልከክልህ…ብላና አባላ…ለአንተ ልጆች እስታዲየም ለነጻ አውጭህ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ…በመፈቃቀድና በመፈቃቀር መድፈር…ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት… አብዮታዊ ዲሞክራሲ…ብሶት የወለደው ስኳር ሲቅም ሌላው በምሬት ይሰደዳል፡ የባህር ገብቶ አዞ ይበላዋል፡ ከፎቅ ተፈጥፍጦ ይሞታል።…እንዲያው በዚህ የሙስና ድሪያ ላይ እንደ ደህንነቱና መከላከያው እንደኢኮኖሚው ዕድገት የብሔር ተዋፅዎው እንዴት ነው!?
    የስኳሩ አባት አባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ሳሌም ከበደ… እንደጂነዲን ሳዶ ሚስት ይሆንና ባለቤቷን ለህወአት ኢኮኖሚና ሥልጣን ግንባታ፡ ለአማራ ልጆች ውድቀት፡ ለሠራውና ለሠረሰረው ውለታ ሲባል በክብር ለትምህርት ውጭ ሀገር ልኮ እንዲከዳ መረዳት፡ ኢሳት ላይ እሳት እንዲጭር ማድረግ የተለመደ አሠራር ነው።
    __ በልዩ ጥቅማጥቅምና አድርባይነት ሲበሉና ሲያባሉ የነበሩ ባለውለታዎች የእንባ አሳዳሪነት ማዕረግ ተሰጥቶ እራቅ ብለው እንዲቆሙ ሲደረግ፡ ለህወአት ኢኮኖሚ ሞኖፖል ሲዋደቁ የነበሩ፡ ጥቁር ልብስና መነጽር ተከራይተው/ተውሰው ለታላቁ መሪ አልቃሽ የመለመሉ፡ ካኒቲራና ፎቶ ያባዙ ዛሬ አገልግሎታቸውን ጨርሰው ዶ/ር የለም፡ መሐንዲስ፡ አገልግል አስቋጥሮ አቧራ ላይ አንደባለለው!…እነኝህ ምልምል ተሞሳሟሾች ከባለቤቶቹ (ሚኒስተሮችና ሚኒስተረ ዴታዎች ) በፊት ወድቀው “ኢኮኖሚው፡ ዕድገቱ፡ ትምህርቱ፡ጤናው፡ ግድቡ፡ ሀዲዱ፡መብራቱ፡ ፈጠራው ህወሓት/ኢህአዴግ ከአፍሪካ አንደኛ፡ ከዓለም ሁለተኛ፡ እያሉ ትምህርታዊ ትንታኔና ቱልቱላ/ጥሩ’ንባ ሲነፉ/ሲረጩ አልነበረም!?
    __ ለመሆኑ ይቺ ገንዘብ ለዚህ ሁሉ አድርባይ ሲካፈል ምን አላት? ይህ ገንዘብ በሶስት ጡረተኛ ጄነራሎች ሥም ብቻ ያለ የገንዘብ መጠን አደለምን!? በአንድ ክልል ፵፭ ትላልቅ ነጋዴዎች ግብር ካልከፈሉ ፳ ተጠርናፊ ቢኖራቸው ፱፲፻ ተሞሳሟሽ ጠርንፈው ታላቁ መሪ ላይ ንፍጥና ልሃጫቸውን በማዝረከረክ የተካኑ በክልል የተፈለፈሉ ጥቅማጥቅመኞች ሕዝቤ የሚሉትን አጅዝበው/የበይ ተመልካች ሆኖ እነሱም ባንዳ(ሹምባሽ) በመሆናቸው ሥርዓት እንዳይለወጥ፡ ሀገር እንዲናወጥ፡ ወገናቸውን ያስበሉ ስንቶች ቃሚና ተጠቃሚ ናቸው?።
    ** “የአዲስ አበባን የንግድ ኢኮኖሚ የሚወስኑት ፹፭ ነጋዴዎች ናቸው” ተጠቅላዩ ሚ/ር መለስ ዜናዊ
    **”፻ ሚሊዮን ብር የወሰዱና የበሉ አውቃለሁ ግን አልነግራችሁም ” ” የራሳቸው የግል እሥር ቤት ያላቸው ነጋዴዎች አሉ” ኅይለማረያም ደስለኝ
    እዚህ እንዴት ሥማቸው የለም? ጭር ሲል ሊወጡ ነው? ይህ በብድርና በልመና የቆመ አብዮታዊ ገዢ/አውራ ፓርቲና መንግስት(!?)
    ” የሕንጻውን መሠረት ሳያወቁ ቅርንጫፍ ባንክ የሚከፍቱ” አለ ከያኒው.. አብዮት ልጇን ትበላለች ካላችሁ ግቡ እንያችሁ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm
  • “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት August 1, 2023 09:25 am
  • ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው July 31, 2023 09:27 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule