• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የእነ ለማ ጉዳይ ወደ ሕግ ሊያመራ ይችላል ተባለ

August 13, 2020 08:05 am by Editor Leave a Comment

ሰሞኑን ከኃላፊነታቸው መታገዳቸው የተሰማው የኦሮሚያ ከፍተኛ አመራሮች አቶ ለማ መገርሣ፥ ወ/ሮ ጠይባና ሜልኬሣ ሚደጋ ከፌዴሬሽን ምክርቤት አባልነታቸውም ተነስተዋል ተብሎ በሥፋት ሲናፈስ ነበር። ሆኖም ዜናው ሐሰት ነው ተብሎ ማስተባበያም ተሰጥቶበታል።

ጎልጉል ከወደ አዲስ አበባ ያሰባሰበው መረጃ እንደሚጠቁመው በቀጣይ ግለሰቦቹ ጉዳያቸው ወደ ሕግ የሚሄድበት መንገድ እየተመቻቸ ያለ ይመስላል። በተለይ ወ/ሮ ጠይባ ሻሸመኔ ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ በከተማዋ ለተፈጸሙ ዘግናኝ ግፎች ተጠያቂ የሚሆኑበት ሁኔታ አለ የሚለው ገዝፎ እየወጣ ነው። እንደሚታወቀው ወ/ሮ ጠይባ ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ በሻሸመኔ ከተማ እጅግ ዘግናኝ የሆነው ግድያ ያውም ገድሎ ዘቅዝቆ የመስቀልና የማቃጠል አሰቃቂ ወንጀል ተፈጽሟል።

የብልጽግና ኦሮሚያ ቅርንጫፍ አመራሮችም ጉዳዩን በግልጽ ባይናገሩትም የጠይባን በሕግ የመጠየቅ ሁኔታ በተደጋጋሚ ሲያስተጋቡ እንደነበር ሰሞኑን በሰጡት ቃለመጠይቆች ተሰምተዋል።

ሚልኬሣ ሚደጋም (ዶ/ር) እንዲሁ ከፓርቲው አሠራር ውጪ መልዕክቶችን በማሰማትና ጸንፈኛ አካሄድ በመከተል የፈጸሙት ከሕግ አንጻር የሚታይበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ጥቆማዎች አሉ።

አቶ ለማ ወያኔን በማስወገድ ትግል የፈጸሟቸው ተግባራትና የሰጡት አመራር እንደ ውለታ ተቆጥሮ በሕግ የመጠየቃቸው ጉዳይ ወደጎን ሊደረግ ይችላል የሚሉ ግምቶች አሉ። ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሞ ውስጥ መከፋፈል ላለመፍጠርና ውጥረቶችን ለማርገብ አቶ ለማ በገዛ ፈቃዳቸው ከመከላከያ ሚ/ር ሥልጣናቸው እንዲነሱ እንደሚደረግ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የሪፖርተሩ ዮሐንስ አንበርብር “የመከላከያ ሚኒስትሩ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነታቸው መነሳታቸው ታወቀ” በሚል ርዕስ የዘገበው ከዚህ በታች ይነበባል።

የኦሮሚያ ክልልን በመወከል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የነበሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ከአባልነታቸው መነሳታቸው ተጠቆመ። ሰሞኑን ደግሞ ከኦሮሚያ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው መታገዳቸው ተሰምቷል።

ከአቶ ለማ በተጨማሪ ሌሎች ሁለት አመራሮችም ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነታቸው መነሳታቸውን ሪፖርተር ያገኘው መረጃ አመልክቷል። 

ክልሉን በመወከል የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎቹ ሁለት አባላት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነት እንዲነሱ የተወሰነው ጨፌ ኦሮሚያ ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደው ስብሰባ ላይ እንደሆነም የሪፖርተር መረጃ ያመለክታል። 

አቶ ለማን ጨምሮ ሦስቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት በተለያዩ ምክንያቶች ተጓድለዋል በሚል ምክንያት ጨፌው ሌሎች አባላትን በመምረጥ እንዲተኩ ማደረጉን መረጃዎቹ አመልክተዋል።

ጨፌው በአቶ ለማ እና በሌሎቹ ሁለት አባላት ምትክ አዲስ አባላትን መርጦ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያስታወቀ ሲሆን፣ አቶ ለማን ተክተው የተመረጡትም በአሁኑ ወቅት የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ኃላፊ እና በጨፌ ኦሮሚያ የክልሉ መንግሥት ተጠሪ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ፍቃዱ ተሰማ ናቸው።

በሌሎቹ ሁለት አባላት ምትክ ደግሞ የክልሉ ፓርቲ አደረጃጀት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻና አቶ አብዱል ሐኪም መመረጣቸው ታውቋል። የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ለማ ሰሞኑን በተካሄደ የፓርቲ ስብሰባ ከኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው መታገዳቸውም ይፋ ሆኗል።

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ በአዲስ አበባ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብስባ ነሐሴ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. አጠናቆ ባወጣው መግለጫ፣ አቶ ለማን ጨምሮ ሦስቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ላልተወሰነ ጊዜ መታገዳቸውን አስታውቋል።

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ለሁለት ቀናት የተካሄደውን ስብሰባና ውሳኔዎቹን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ ስብሰባው በፓርቲው ክልላዊ መዋቅር ላይ የተስተዋሉ ድክመቶች ላይ በስፋት ተወያይቶ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን የተመለከቱ ውሳኔዎችን እንዳሳለፈ ገልጸዋል።

በፓርቲው የክልል መዋቅር ከፍተኛ አመራሮች ላይ ባደረገው ግምገማም በማዕከላዊ አባልነት ሲያገለግሉ የነበሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ፣ ወ/ሮ ጠይባና ሚልኬሳ (ዶ/ር) ላልተወሰነ ጊዜ ከማዕከላዊ አባልነታቸው እንዲታገዱ መወሰኑን አስታውቀዋል።

አቶ ለማ መገርሳ ከማዕከላዊ አባልነታቸው እንዲታገዱ ምክንያት ከሆኑት ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ በፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባዎች ላይ በተደጋጋሚ አለመገኘታቸው መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም የመከላከያ ሚኒስትር ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በተጣሉባቸው መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ላይም በተደጋጋሚ አለመገኘታቸውን አቶ ፍቃዱ በምክንያትነት አንስተዋል።

አቶ ለማ የአገር መከላከያ ሚኒስትርን በመወከል የፌዴራሉ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ በምክር ቤቱ ስብሰባዎች ሲሳተፉ አይስተዋሉም። አቶ ለማ ላይ ሌላው የቀረበው የዲሲፕሊን ጥሰት አባል በሆኑበት የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት ስብሰባ ላይም በተደጋጋሚ አለመሳተፋቸውና ለሁለት ቀናት በተካሄደው የፓርቲው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተደጋጋሚ ጥሪ ተደርጎላቸው አለመገኘታቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም አቶ ለማ ከማዕከላዊ አባልነታቸው ታግደው እንዲቆዩ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ባካሄደው ስብሰባ በሙሉ ድምፅ መወሰኑን አስረድተዋል።

ወ/ሮ ጠይባም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት በነበሩ ግጭቶች ጋር በተገናኘ ስማቸው ሲነሳ መቆየቱ ጠቁመው፣ ከፍተኛ አመራሩና አባሉም አመኔታ በማጣቱ ጥያቄ ያነሳ ስለነበር ጉዳያቸው እስከሚጣራ ድረስ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ሚልኬሳ (ዶ/ር) ከፓርቲው ሥነ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ በውስጥ ማድረግ የሚገባን ትግል ወደ ውጭ በማውጣትና መገኘት በሚገባቸው ስብሰባዎች ላይ ሊገኙ ባለመቻላቸው እንዲሁም የፓርቲውን ሚስጥር በተለያዩ መድረኮች በማውጣታቸው ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑን ገልጸዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: lemma megerssa, milkessa, tayiba

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule