• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ታጋይ ጎቤ መልኬ በአዴት ጦርነት ተሰዋ፤ “የህወሃት ወራሪ ሃይል ጉዳት ደርሶበታል”

February 28, 2017 11:46 pm by Editor 6 Comments

  • “ጎቤ ሲሰዋ አዳዲስ ጎቤዎች ትግሉን ተቀላቅለዋል’’

“አርበኛ ጎቤ መልኬ ተሰዋ” ሲሉ በአካባቢው የሚገኙ የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ገለጹ። ህወሃት የሚመራው ሰራዊት ክፉኛ ጉዳት ደርሶበታል። ዜናው ኢህአዴግ በሚያስተዳድራቸውም ሆነ በሚደጉማቸው መገናኛዎች ይፋ አልሆነም። ለነጻነት ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚባሉ አካላትም ይህ ዜና እስከታተመበት ድረስ በግልጽ ያሉት ነገር የለም። አርበኛ ጎቤ እራሱን እንዳጠፋም የሚገልጹ አሉ።

በሰሜን ምዕራብ ቆላማዉ ክፍል የደፈጣ ተዋጊዎችን የሚመራዉ ታዋቂዉ አርበኛ ታጋይ ጎቤ መልኬ በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ዕዝ ስር ባለዉ “አንገረብ” እየተባለ በሚጠራዉ የስለላ ቡድንና በ“ጸረ-ሽብር ግብረ ኃይል ቡድን” የጋራ ዘመቻ በጠገዴ ወረዳ ልዮ ስሙ “አዴት” በተባለ በርሃማ ቦታ ትላንት ማምሻዉን በተካሄደ ዉጊያ ነው “ጎቤ ተሰዋ” የተባለው።

የጎልጉል የአካባቢዉ የመረጃ ሰዎች እንደገለጹት የካቲት 20 ቀን2009 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ሰዓታት ነበር ውጊያው የተካሄደው። ዉጊያ የተከፈተው ድንገት ሲሆን በከፍተኛ ኃይልና በከባድ መሳሪያ የተደራጀዉ የህወሓት የጦር ሰራዊት ድንገተኛ የማጥቃት ዘመቻ ጀመረ። በከባድ መሳሪያ ሽፋንና ሰፊ ቁጥር ባለው “ወራሪ” የታገዘው ድንገተኛ ማጥቃት በነጻነት ኃይሎች ላይ ጉዳት ቢደርስም ዱር ቤቴ ያሉት ታጋዮች ለመከላከል ባደረጉት ትንቅንቅ የህወሓት ጦር ላይ ቀላል የማይባል ጉዳትና ውድመት አድርሰዋል።

ከህዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ በአርማጭሖና በጠገዴ አካባዉ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ፖሊስ እንዲወጣ ተደርጎ አካባቢው በህወሓት ልዩ ጦርና ዳንሻ ላይ በሰፈረዉ 44ኛ የመከላከያ ጦር ሰራዊት ዕዝ ስር እንዲወድቅ ተደርጓል። ቀደም ሲል የአማራ ክልል ፖሊስ ከለላ የሚሰጣቸው የነጻነት ሃይሎች የአማራ ክልል ልዩ ሃይል አካባቢውን እንዲለቅ ከተወሰነ በኋላ፣ ለዚህ መሰል ድንገተኛ ጥቃት ሊዳረጉ መቻላቸውን ታዛቢዎች ይናገራሉ። ትላንት ማምሻዉን ጠገዴ ወረዳ “አዴት-ጄጄ” በተባለ ቦታ የተካሄደ ዉጊያም የዚሁ ውጤት እንደሆነ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በውጊያው የታወቁ ከሃያ በላይ የህወሓት ጦር ሰራዊት አባላትና አዋጊ መኮንን ተገድለዋል፤ ታጋይ ጎቤን ጨምሮ ዘጠኝ የነጻነት ሃይሎች ተሰዉተዋል፡፡

“ታዋቂዉ አርበኛ ታጋይ ጎቤ መልኬ በተለያዩ የሰሜን ምዕራብ ቆላማ ቦታዎች እየተዘዋወረ በህወሃት/ኢህአዴግ ኃይሎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ያደረሰ ጥቃት ሲፈጽም የነበረ ልበ ሙሉ ታጋይ ነበር” የሚሉት የክፍሎች “ታጋዩ ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተፈጠረዉ ህዝባዊ አመጽ ቤቴ፣ ንብረቴ፣ ሃብቴ ሳይል ህይወቱን ለመስጠት ምሎ የተነሳ ታጋይ ነበር’’ ብለዋል። “የጎቤን የትግል ፈለግ በመከተል እኛም የበቀል ክንዳችን እናፋፍማለን” ሲሉ የታጋይ ጎቤ መልኬ የትግል አጋሮች ቃላቸውን ማደሳቸውንም ጠቁመዋል።

“ልዩ” ከሚባለው አርበኛ መሰዋት በኋላ በርካታ ጎቤዎች መፈጠራቸውና ሰፊ ቁጥር ያላቸው ወደ ጫካ እንደሚገቡም አረጋግጠዋል። ለጥንቃቄ ሲሉ የቦታ ስሞችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። የአካባቢው የጎልጉል ምንጭ ያነጋገራቸው “ታጋይ ይሰዋል። ትግል ግን ይቀጥላል። አሁን የተጀመረው ትግል የሚቆም አይደለም። አንድ ጎቤ ሲሰዋ፣ በርካታ ጎቤዎች ወዲያው ተወልደዋል። በቅርቡ የበቀል ርምጃ ይወሰዳል። ህዝብ ተናዷል። ብሶቱና ቁጣው እየነደደ ነው። አፈናውና ስቃዩ በቃላት የሚገለጽ አይደለም። የአማራ ክልል አስተዳዳሪዎች በውክልና ህዝባቸውን የሚሸጡበት ዘመን እስኪያበቃ መስዋእትነት ይከፈላል። ጎቤ በክብር የማይቀረውን የህይወት ጉዞ ተቀብሏል። ሕዝባቸውን ለሸጡ፣ እየሸጡ ያሉና በባንዳነት የገለሙ ያካባቢው ተወላጆች ከነጌቶቻቸው ይፈረድባቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻ ባገኘነው ዜና “ወራሪው ህወሃት ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት የደረሰ ቢሆንም ጦርነቱን የአካባቢው ሚሊሻዎች እንዳካሄዱትና ቀላል እንደነበር በማስመሰል የፕሮፓጋንዳ ስራ ለመስራት አንዳንድ ሆድ አደሮችን ለምስክርነት አነጋግርዋል” ብለዋል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከአካባቢዉ በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ታጋይ ጎቤ መልኬ በታች አርማጭሆ ወረዳ የተከበረ አራሽ-ነጋዴ፣ አራት የጭነት አይሱዚ መኪኖች፣ ከአራት መቶ በላይ የቁም ከብቶች፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረትና ሰፊ የሰሊጥ እርሻ መሬት ባለቤት፣ ከነጻነት በቀር ምንም ያላጣ ታዋቂ ባለሃብትና የሀገር ሽማግሌ ነበር፡፡

የአማራና የትግራይ ክልል የድንበር ይገባኛል ዉዝግብ በተካረረ ስሜት በሚራገብበት ሰዓት ችግሮች በዕርቅና በሽምግልና እንዲፈቱ ጥረት ሲያደርጉ ከነበሩ የአካባቢዉ ተወላጆች ዉስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሰዉ ጎቤ መልኬ፣ በትግራይ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አደራጅነት በየጊዜዉ በአማራ ክልል ነዋሪዎች ላይ የሚደርሰዉን ጥቃት አጥብቆ ያወግዝ ነበር፡፡ በተለይም ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸዉ የአካባቢዉን ችግር ለአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ባህር ዳር ድረስ በመሄድ አቤቱታ ካሰሙ ያገር ሽማግሌዎች አንዱ ጎቤ መልኬ ነበር፡፡

ይህን ጉዳይ ዛሬ ላይ በቁጭት የሚያስታዉሰዉ የታጋይ ጎቤ መልኬ የቅርብ ሰዉ “ሰዉየዉ ተገፍቶ ነበር ጫካ የገባዉ፤ የእርሱ ደም እንዲህ በዋዛ ባክኖ አይቀርም፡፡ የጎቤ መስዋዕት መሆን ከትግላችን አያሸሸንም” ሲል በመረረ ስሜት አስተያየቱን በስልክ ሰጥቶናል፡፡

የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን ለማፈን የህወሓት ጦር ጎንደር ከተማ ላይ ያደረገዉ ዘመቻ ያልታሰቡ መዘዞችን እንዳመጣበት ይታወሳል፡፡ ሐምሌ 04/2008ዓ.ም ምሽት 3፡30 ጀምሮ በየኮሚቴ አባላቱ ቤት በመዘዋወር የተካሄደዉን የአፈና ዘመቻ በመቃወም በማግስቱ ሀምሌ 05/22008ዓ.ም አደባባዩን በአመጽ የሞሉት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን በመደገፍ ከዳንሻ፣ ጠገዴ፣ ሶረቃ፣ ሳንጃ፣ ሙሴ ባምብ … የተዉጣጣዉን የህዝባዊ ጦር ሰራዊት በመምራት ጎንደር ከተማ ድረስ ዘልቆ በመግባት በታላቅ ጀብዱ ከህወሓት ጦር ጋር በመዋጋት የህወሓት ጦር ልዮ ኦፕሬሽን ሃላፊ የነበረዉን የዘመቻዉን ሃላፊ ኮማንደር ሀለፎም በርሄ ጨምሮ ሃያ ሰባት “የጸረ ሽብር ግብረ ኃይል ቡድን” አባላትንና አስራ ዘጠኝ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በጎንደር ከተማ ቀበሌ አስራ ስምንት አደባባይ ላይ (ኮለኔል ደመቀ ዘዉዱ መኖሪያ አካባቢ) ትግሉን ካፋፋሙት ቁንጮ የነጻነት ታጋዮች አንዱ የሆነዉ ጎቤ መልኬ በአካባቢዉ ነዋሪዎች የበዛ ክብር የነበረዉ ሰዉ መሆኑን የጎልጉል የመረጃ ምንጮች ዘገባ ያመለክታል፡፡

በስልሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ይገኝ የነበረዉ ታጋይ ጎቤ መልኬ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ከኮሚቴ አባላቱ እስር በኋላ ተዳፍኖ እንዳይቀር የአካባቢዉን ሰዎች በማስታጠቅ ሲፋለም የነበረ ቆራጥ የነጻነት ታጋይ ነበር፡፡ የታጋዩ የቀብር ስነ ሥርዓት በታች አርማጭሆ ወረዳ “አመራ ቁስቋም” ገዳም ዉስጥ እንደሚካሄድ ከአካባቢ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡

የታጋዩን መስዋዕት መሆን ተከትሎ ቁጣ የተቀሰቀሰባቸዉ አካባቢዎች መበራከታቸዉን የሚጠቁሙት የጎልጉል የአካባቢዉ ምንጮች ከጎንደር ወደ አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ዳንሻ የሚወስዱ መንገዶች በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ በየ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀቶች የመከላከያ ኬላ የተጣለ ሲሆን ዛሬ የካቲት 21/2009 ዓ.ም ከጎንደር ወደ ሁመራ የሚሄዱ መኪናዎች ከሳንጃ በኋላ በደህንነት ስጋት ጉዟቸዉ የተገታ መሆኑን ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡

የታጋዩ ጓዶች በጫካ ብቻ ሳይሆን በህዝብ ጥላ ስርም የታቀፉ በመሆኑ በቀጣይ የበቀል ክንዳቸዉን በህወሓት ሰዎች ላይ እንደሚያነሱ ይጠበቃል፡፡ እንደ አካባቢዉ የመረጃ ምንጮቻችን ጥቃቱ በህወሓት ሰዎች ብቻ የሚቆም ሳይሆን የህወሓት ማህበራዊ መሰረቶች ናቸዉ በሚባሉ የእርሻ ቦታዎች፣ ፋብሪካወዎችና ተቋማቶችንም ይጨምራል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረረጃዎችን ከሰሞኑ የሚያደርስ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል መሳሪያ ፍታ፣ መሳሪያ ከየት እንዳመጣህ ተናገር፣ ማን አስታጠቀህ በሚሉ ጉዳዮች ሕዝብ እየታሰረ፣ እየተገረፈና እየተሰቃየ መሆኑንን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያረጋግጣሉ። መሳሪያቸውን ላለማስረከብ የሚሰወሩም እየተበራከቱ መሆኑ እየተሰማ ነው። አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ይህን ያኮረፈና የመረረው ህዝብ አደራጅቶና የትግል ስትራቴጂ ነድፎ የሚያታግል ቁም ነገረኛ ኃይል ቢኖር ትግሉ እስካሁን ብዙ ርቀት ሊሄድ ይችል ነበር።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Uncategorized Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Ezira says

    March 1, 2017 02:37 pm at 2:37 pm

    በቅድሚያ ለጎልግሎች !
    የተለመደውን አድናቆቴን ስግልጽላችሁ PROFESSIONAL የጋዜጠኝነት ሙያችሁን በተደጋጋሚ በተግባር ስለምታሳዩን ነው። በእውነቱ ለሙያችሁ ያላችሁ ትጋትና ዌብ ሳይታችሁ ላይ ይዛችሁ የምትወጡት ትኩስ ዜናዎቻችሁ ትኩረቴን ሁሌ ይስበዋል። በዚህ ላይ ጥልቅ ትንታኔያችሁ ደግሞ ምራቅ ያስዉጣል። እናም አምላክ ከክፉ ነገር ይሠውራችሁ እላለሁ። ሙያ በልብ እንዲሉ እንደ ( ZeHabesha) ሳትንጣጡ፣ ሙያችሁን ፀጥ ብላችሁ በተግባራችሁ የምታሳዩ በመሆናችሁ የዘወትር አድናቂያችሁ ነኝ። ይሄንን መሠል ብቃታችሁን ደግሞ ይበልጥ አጠናክራችሁ ትቀጥሉበት ዘንድ መልካም ምኞቴን ስገልፅላችሁ በኩራት ነው። ስምን መልዓክ ያወጣዋል ይባላልና እንደስማችሁ ሁሉ ትኩስ ትኩስ (HOT)ዜናዎችን ጎልጉላችሁ እንካችሁ ስትሉን የዜና ምንጮቻችሁንም ጠንካራ መሆን ያምላክታልና ነው። በርቱ ጎልጉሎች !!

    ሲቀጥል፥ የወራሪው የትግሬ ወያኔ ማረከሻ የሆነዉና የነበረው የታጋይ ጎቤ መልኬ ሞት፣ የሚጠበቅና የጀግና ሞት ነው። ጠላትን ገደሎ መሞት በጀግኖች ሜዳ መገኘትን ይጠይቃል። የጀግናን ሞት እንዲህ በቀላሉ በስለትም ሆነ በምኞት አይገኙትም። የጅግናን ሞት የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው። ያውም ልባቸው በጀግንነት እሣት የነደዱ ሰዎችን ይመርጣል። ለነገሩማ የጀግኖችን ልብ ሙሉነት የሚያሳይ ወይም የሚገለጽም አንድ አባባል አለ- እንዲህ ነው…… “ጀግናን ኧረ ተግ በል ማለት ሲቻል፥ ፈሪን ግን ማጀገን አይቻልም። ምክንያቱም ፈሪ ቀድሞውንም ዉኃ ውስጥ ገብቶም ያልበዋልና ነው። ስለዚህ የታጋይ ጎቤን ነብስ በገነት ያሳርፍልን። የጀግና ሞቱ ኩራቱ ተብሏልና። ሠልፍ የጀግና ኃይል ግን የእግዚአብሄር ነው። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

    Reply
  2. Tewedros says

    March 2, 2017 11:17 am at 11:17 am

    It is with immense sadness that I received the assassination of a great hero. Indeed, it is incumbent on a hero to die as one.

    The brave sons of the land will not relent until every inch of the Tigre-annexed region is freed and our country liberated from such a contemptible enemy.

    Reply
  3. Tadesse says

    March 2, 2017 10:10 pm at 10:10 pm

    We need a united front,there are many Tigrians who are opposed to this rule of selfish people,the most loosers in this bad political game are the people of Tigray.

    Reply
  4. Mulugeta Andargie says

    March 4, 2017 02:15 am at 2:15 am

    Guys!!!Gobie is 70 years old; isn’t it??? Was he a retired person or a fighter??? Man!!!! 70 years old!!!!

    Reply
  5. balcha says

    March 4, 2017 05:58 am at 5:58 am

    Lets not make mistake, the tplf war with the Amhara Arbegnoch is the war with the Amhara people. The war is between Tigray vs Amhara. If they are able to dismantle the Arbegnoch force which is not possible of course, then they will even brag much more as Tigray is the land of the brave and the Amharas are cowardice. How long will it take again to form another Amhara force that struggle the tplf. Tplf pretend to fed one Amhara in one hand until it kills the other Amhara on the other hand. Finally it will come back and kill the one it was feeding.

    Reply
  6. Koda lebshu Amhara says

    March 15, 2017 07:09 pm at 7:09 pm

    You know who killed Gobe? The killers are Takle yashaw, demise belete, Hara ethiopia [haileyesus Admau], Girma kassa, and Bete Amhara paltalkers, Ristte tesfaye
    This are the killers blame them

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am
  • የኤሊያስ መሠረትን ፌክ መረጃ ማን ያጋልጥ? February 19, 2025 06:00 pm
  • አዘርባጃን፡ የሻዕቢያን ሸምቀቆ ማጥበቂያ?! February 19, 2025 12:29 am
  • የአሜሪካ ድምፅ/ቪኦኤ ይዘጋ ተባለ  February 12, 2025 03:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule