• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዘመነ መሳፍንትና የፖለቲካ መሪዎቻችን የወረሱት ቅርስ

December 7, 2014 02:31 am by Editor Leave a Comment

በዘመነ መሳፍንት ወቅት፤ ለስሙ በዙፋኑ ላይ የዘር ግንድ ያለውን ሰው አስቀምጠው፤ ራሳቸውን እንደራሴ በመሾም፤ ጉልበተኞች ያደረጉት ሁሉ ግልጽ ነው። የውጭ ሀገር መንግሥታት ደግሞ በወኪሎቻቸው አማካኝነት ፀረ-ኢትዮጵያ ሚና ተጫወቱ። በደንብ በዝርዝር የሚያስረዳ መዝገብ ግን አላገኘሁም። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሜ የተገነዘብኩትን ይዣለሁ። የእስክንድርያውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በመጠቀም፤ ግብፅና ቱርክ በአንድ በኩል፣ በፖርቹጋሎች የተጀመረውን ግንኙነት በመጠቀም፤ የካቶሊክ ቤተክርስትያን በሌላ በኩል፣ በእንግሊዝና በፈረንሳይ በኩል ደግሞ የፕሮቴስታንትና የአድቬንቲስት ተቋሞች በማዕከላዊው የሀገራችን ክፍል ያላደረጉት ተንኮል የለም። የሁሉም ጥርቅም ጥረት፤ ክርስትናን ወይንም እስልምናን ተከትለው፤ የፈጣሪያቸውን ሥራ ለማስተማር ሳይሆን፤ ጠንካራ ኢትዮጵያ እንዳትኖር ለማድረግ ነበር። አባይን እንዳትገድብ፣ ለቅኝ ግዛት ተቀናቃኝ እንዳትሆን፣ የጥቁር መንግሥት ሆና ለባሪያ ንግዳቸው እምቢተኝነት መመኪይ እንዳትሆን ነበር። ማዕከላዊ ጥንካሬው እየበረታ የሄደው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በክልሉ ያሉትን ዜጎች እያስተዳደረና ኢትዮጵያዊነትን እያጎለበት በሄደ ጊዜ፤ ለረጅም ዘመን በኢትዮጵያዊ መንግሥታት ሥር የነበሩ ክልሎችን አምጡ ማለቱና፤ የአውሮፓዊያንን የቅኝ ግዛት በአካባቢው ለማስፋፋት መሯሯጥ የሚገታ መሆኑ ሁሉንም አስጋ። እናም ይህ የውጪ ያላባራ ተንኮል፤ ሀገራችን ባሉት ባላባቶች ውስጥ፤ ያላቋረጠ የመጠፋፋት መናኮርን አፋፋመ። አንድና ሁለት ጠመንጃዎች ካስርና ሃያ ጥይቶች ጋር በመጸሐፍ ቅዱስ በመጠቅለልና በማቀበል ቆስቋሾቹ እያራገቡት፤ ግለቱ እየጨመረ፤ አንድ ጳጳስ በመላክ ውስጡን እያመሱ፤ ትርምሱ እያደገ፤ በሀገራችን ውስጥ የጎጥ ገዥዎች አየሉ። በዚያ ጊዜ የተተከለው መርዝ አሁንም እያመረቀዘ፤ ጥዝጠዛውና ግማቱ እኛን አፍኖናል። እንዴት? ይህን ነው የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ። አንድ ቢሆኑ ኖሮ!

ከፍጻሜ መንግሥት አንስቶ አፄ ቴዎድሮስ እስከተነሱበት ድረስ፤ ዘመነ መሳፍንት እየተባለ የሚጠራው የታሪካችን ወቅት፤ ምን ያህል የሀገራችን ዕድገት ወደ ኋላ እንዲጎተት እንዳደረገው በሰፊው የተመዘገበ ነው። ይህ ዘመን፤ ለረጅም ጊዜ፤ እየተዋጉም ሆነ አባት ለልጁ እያወረሰ፤ ተከታታይነት የነበረውን የማዕከላዊ መንግሥት ሕልውና ከጥያቄ ውስጥ አስገባው። እኔስ ከማን አንሳለሁ በማለት፤ ወገኖቹንና ነፍጥ በማሰባሰብ፤ ያካባቢው ገዥ እኔ ነኝነት ነገሠ። በዳር ዳር በሚባሉ አካባቢዎች የሚገኙት ዜጎች ከማዕከላዊው መንግሥት የነበራቸው ግንኙነት ላላ። ትግራይ፣ ወሎ፣ ወልቃይት፣ ላስታ፣ የጁ፣ ስሜን፣ ሸዋ፣ ጎጃም፣ ቋራ፣ ከፋ፣ ሐረር፣ ኦጋዴን፣ ሞያሌ፣ የሚባሉት ክፍሎች፤ የየራሳቸው ጉልበተኞች እንደራሴዎች ሆኑባቸው። ሲደክሙ ለጉልበተኛው እየገበሩ፣ ሲጎለብቱ ራሳቸው እያስገበሩ፤ መንግሥታዊ ተግባር የሚባለውን ረስተው፤ ነፍጥ መሰብሰብንና ለሚቀጥለው ውጊያ መዘጋጀትን፤ የሕልውናቸው አውታር አደረጉት። ትብብር ማለት፤ እኔን ነገ እስከጠቀመኝና እሱን ወግቼ እስካቸነፍኩት ድረስ በሚለው ስልት ተለወጠ። እንግዲህ ይህ የውስጡ ሀገራዊ አስተዳደሩ ነበር። መቼም ይህ ለሁላችን ግልጽ ነው። ታሪክ መመርመር ሳይሆን ያለንበትን መመርመሩ በቂ ማስረጃ ነው። የውጪ ጣልቃ ገቦች ለዚህ ሂደት ምን ያህል ተጠያቂነት አላቸው? አሁን ላለንበትስ? እንግዲህ እዚህ ላይ ነው የዘመነ መሳፍንት ቅርሳችን እና የፖለቲካ መሪዎቻችን ተወራራሽነት በግልጽ የሚታየው። አንድ ቢሆኑ ኖሮ!

አፄ ቴዎድሮስ ለዘመነ መሳፍንት ፍጻሜ ከሠጡት ይሄው ከአንድ መቶ ሃምሳ ዓመት በላይ ሆኖታል። ዘመኑን እንጂ አብሮን ያለውን አመለካከቱን ማለቴ አይደለም። በአእምሯችን ያንን የታሪካችንን ወቅት ብናስወግደውና ተከታታይነቱን የጠበቀ የኢትዮጵያ መንግሥት ቢኖር ኖሮ የሚለውን አስተባቅተን፤ አሁን ሀገራችን ልትደርስበት የምትችልበትን ብናጤን፤ አሁን ካለንበት ምን ያህል ይለይ ነበር? መቼም የታሪክ ሂደት በሰዎች እቅድና ፍላጎት እንደማይመራ ዕውቅ ነው። ታልሞና ተቀምሮ የሚነደፍና የሚገፋ እንዳልሆነ ስቼ አይደለም። ነገር ግን ትልሙን በመዘርጋት ዕይታ ለመፍጠር ስል ነው። የተደናቀፈው ሁሉ ቢስተካከል፤ የት ልንደርስ እንችል እንደነበር መገመቱ ቀላል ነው። በአኳያው ደግሞ፤ ከዚያ ትምህርት ወስደን፤ የያኔውን ወቅት ስህተት አለመሥራቱ፤ የኛ ታሪካዊ ግዴታ ነው። እንደያኔዎቹ አሁንም ያንኑ ሆኖ መገኘት፤ ጅልነት ነው። ጅልነቱም በቀላሉ ሲመነዘር ነው። ከዚያ ለከፋ ስድብ ራስን ማሰለፉ አልጥም ስላለኝ ነው። እንደያኔዎቹ የየራሳችን ቦታ ባንይዝም፤ በትካቸው ድርጅቶች አሉን። እናም የየድርጅቶቻችን ንጉሥች አሉን። ዙፋኑንም ለማንም ላለማውረስ፤ ለሚነሳው ተቀናቃኝ የስድብ ውርጅብን በመቆለል ትንንሽ ሌሎች ድርጅቶች እየተፈጠሩ፤ ተደላድለው በመቀመጥ ዓመታትን ያስቆጠሩ ስንት ንጉሦች አሉን? እንግዲህ ቦታውና በዙፋኑ የተቀመጠው ንጉሥ፤ በድርጅት ተተክቷል። እንደራሴዎች የሆኑት ያሁኖቹ የድርጅቶቻችን መሪዎች ናቸው። ሀገር ማለት፣ ወገን ማለት፣ ታሪክ ማለት፣ ድርጅት ሆኗል። በቃ አለቀ በቃ! የኔ ድርጅት ያቸንፍ! አለያ ገደል ግቡ ተብለናል። ተሳስቼ ይሆን? አንድ ቢሆኑ ኖሮ!

የያኔዎቹ ባላጋራቸውን እያብጠለጠሉ ለውጭ መንግሥታት አቤቱታ በማቅረብ ይለምኑ ነበር። አሁን ደግሞ ሌላውን ታግይ ድርጅት መኮነን፣ ሰላማዊ ሰልፍ በውጭ ሀገሮች ማድረግና መታገያ እንዲሆነን የበጎረቤት ሀገር መጠጋቱን ሙያችን ብለነዋል። ድንቄም! አለች ጎረቤቴ! አንድ ቢሆኑ ኖሮ!

(አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ)
እሁድ ታህሣሥ ፳ ፱ ቀን ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት (12/7/2014)

ተጨማሪ ጽሁፎችን በአቶ አንዱ ዓለም ተፈራ ብሎግ ላይ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule