
የዛሬ 30 ዓመት ገደማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሒሣብ መዝገበ አያያዝ ትምሐርት አስተምር ነበር። ዛሬም በሱው ነው እንጀራዬን በስደት ዓለም ከስቃይ ጋር እንደወጥ እያጣቀስኩ የምበላው። ታዲያ ያኔ፣ የመምሕራን ካፌቴሪያ ለምሳ በየጠረጴዛው ዙሪያ በቡድን በቡድን እየተሰበሰብን አንዳንድ ክፍል ውስጥ ያጋጠሙን ገጠመኞች እያነሳን እንስቅ ነበር። አንድ ዕውቅ የኢኮኖሚክስ መምሕር ነበሩ። እግዚአብሔር ይመስገንና፣ ዛሬም በሕይወት አሉ። ስማቸውን ግን አልጠቅስም። ታዲያ አንድ ቀን ከጎናችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ሁነው ምሳ እየበሉ ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በዕለቱ ያጋጠማቸውን አስቂኝ ክስተት ሲገልጹ፣ ጆሮዬን ጣል አድርጌ እንደዋዛ እሰማቸው ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዳንድ ጠጠር ያሉ የኢኮኖሚክስ ጽንሰ-ሀሳቦችን አንስተው ሲያስተምሩ፣ አንድ ወጣት ተማሪ ነገሩ ከብዶት ነው መሰል፣ ሳያስበው እንቅልፍ ይዞት ለሽ ይላል። ያንን ያዩት ዕውቁ የኢኮኖሚክስ ባለሙያ፣ ድምጻቸውን በድንገት በጣም ክፍ በማድረግ፣ ጮክ ብለው ማስተማር ይጀምራሉ። እንቅልፉን ይለጥጥ የነበረው ተማሪ በርግጎ ተነስቶ ይቆማል። መምሕር ትኵር ብለው አይተውት፤ “ይቅርታ! ቀሰቀስኩኽ እንዴ? ምን ላድርግ ብለኽ ነው። እንጀራ ነው የሚያስጮኸኝ።” አልኩት ብለው ሲናገሩ ጠረጴዛቸው ዙሪያ የተኮለኮሉት በሳቅ አውካኩ። እኔ ባልስቅም፣ ነገሩን ልብ ብዪ ከጎናቸው ከነበረው ጠረጴዛ እሰማቸው ስለነበር እስካሁን አስታውሰዋለሁ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply