• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከተማርኩት ቁጥር 1

March 12, 2016 05:41 am by Editor 2 Comments

ያሜሪካ ቆይታዬ በጣም አጭር ነው። ሁለት አመት እንኳን አይሞላም። ላገሩ አሁንም ላገሩ ባዳ ለወንዙ እንግዳ ነኝ። ገና ብዙ ያልገባኝ ነገር አለ።

ግን በዚህች አጭር ጊዜም ቢሆን ብዙ ጠቃሚ ነገር ተምሬያለሁ ብል “አይ ገና ምኑ ተይዞ” እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ለምን ቢባል ልማር ላለ ሳር ቅጠሉ እውቀት መሆኑን ታውቁታላችሁ ብዬ ነው። ይልቅስ ለመሆኑ ምን ተማርክ ብትሉኝ ወጌን እጀምራለሁ።

አዎ! ብዙ ነገር። ከእንግዲህ ምናልባት ሰሚ ካገኘሁ ከተማርኩት እያልኩ በተከታታይ አንዳንድ ነገር ለማካፈል አቅጃለሁ። ታዲያ እኔ ትምህርት አገኘሁበት ያልኩት ነገር ከታወቀ የቆየ ወይም የፊደል ቆጣሪ ግንዛቤ ሆኖ ካገኛችሁት የሞተውን አባባ ይለዋል ወይም የልጅ ነገር ሳትሉ ሃሳብ ስጡበት። እኔ አላማዬ መማር ስለሆነ ከስህተቴ እማራለሁ።

ከተማርኩት ቁጥር 1

ወደፍሬ ነገሩ ከመግባቴ በፊት ተማርኩባቸው የምላቸው ጉዳዮችን የማነሳው ሀገሬ ኢትዮጵያን በሆዴ ይዤ መሆኑን ልብ በሉልኝ። ባጭሩ መሰረታዊ ጉዳያችን ታላቋ ኢትዮጵያ (ለኔ ዛሬም ኢትዮጵያ ታላቅ ናት) ከታላቋ አሜሪካ ህይወት ምን ልትማር ትችላለች የሚል ነው።

ስለ ጦርነት

አሜሪካኖች እርስበርእሳቸው ተዋግተዋል። ለአምስት አመት። ከ600 ሽህ ህዝብ በላይ አልቋል። ልባአድርጉ! የተዋጉት እርስበርስ ነው። ከዚህ የታሪክ ክስተት መነሻና መድረሻ ለሀገራችን ጉዳይ የሚጠቅም ቁም ነገር ማግኘት ይቻላል። በመጀመሪያ ኢትዮጵያውያን እርስበእርሳችን ስንዳማ መኖራችን የሚያስመሰግን ባይሆንም ካለም ለይቶ የሚያስረግመን ገጠመኝ አይደለም። በዘመኑ የተሻለ ስልጣኔ የነበራቸው አሜሪካኖች ዴሞክራሲያዊ የሚባል ስርአት ከገነቡ በኋላ እንኳን በዚያን ጊዜ ባስከፊነቱ ወደር አልባ የነበረ እልቂት ያስከተለ ጦርነት አካሂደዋል። ከዚህ አንፃር ሲታሰብ የኢትዮጵያውያን ልምድ ባይወደስም ጉድ ሊባል አይገባም።

ከዚህ ሁሉ የበለጠው ትምህርት ግን ጦርነትን የታሪክ ትምህርት እንጂ የዘወትር የጀግንነት ስራ አድርጎ ያለመቀጠል ነው። አሜሪካኖች ጦርነቱን ታላቅ ሀገርና ጠንካራ የፍትህ ስርአት ገንብተውበታል። ዳግመኛም አላካሄዱትም። ጦርነታቸውን ሌላ ጦርነት የማያስነሳ ስርአት መሰረቱበትና ታሪክ ብቻ ሆኖ እንዲቀር አደረጉት። እኛም ማድረግ ያቃተንና ማድረግ ያለብንም ይህንን ነው። መኮነን ያለብን ያሳለፍነውን ጦርነት ሳይሆን የሚመጣውን አዲስ ጦርነት ነው። አሜሪካኖች አንድ ጊዜ ደም ተፋሰው የጦርነትን በር ዘጉ። እኛ የታሪክ ጦርነቶችን እያብሰለሰልን ላዲስ ጦርነት ጠመንጃ እንወለውላለን። ልዩነታችን እዚህ ላይ ነው። በጦርነት ስልጣን የያዘው አካል ጦርነት በታሪክ ያደረሰብንን ጉዳት በማጤን ዳግም ደም አፋሳሽ ግጭት እንዳይነሳ ለሰላምና ለህዝብ ደህንነት በግንባር ቀደምትነትና በሆደሰፊነት ጠንክሮ ከመስራት ይልቅ ወንድ የሆነ ይምጣ አይነት ፉከራን ያሰማናል። እንዲያውም ራሱ ቀድሞ በራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ህዝብ በከፈለው ግብር ጥይት እየገዛ ህዝብ ላይ ይተኩሳል። ሌላው በበኩሉ ለነፃነትና ሰላም መፍትሄው ጠመንጃ ነው በሚል አቀባብሎ ደም ሸቶኛል ይላል።

ዳያስፖራውም ቢሆን ቢያንስ ጦርነት አከል ንግግር አላጣም። እና ሁላችንም ተደምረን ስንሰማ ዜማችን አንድ ነው። ይሄውም፤ ትናንት ስንዋጋ ነበር፤ ዛሬም እንዋጋለን፤ ነገም እንዲሁ፥ የሚል ነው። ክፉ አባዜ!

አሜሪካኖች ከጦርነት ዘላቂ ሰላም፣ ነፃነትና ፍትህን ሲመሰርቱ እኛ ከጦርነት ተነስተን ወደ ጦርነት እንጓዛለን። አሜሪካኖች ከጦርነት ልማትን ተምረው ሰላማዊ ስርአት ሲመሰርቱ እኛ ግን ከጦርነት ለነገ የሚሆነንን አዲስ ጥፋት እንቀስማለን።

እኔ ግን የተማርኩትና ያገሬ ሰውም እንዲማር የምመኘው ከጦርነት ጥፋትን ሳይሆን ደህንነትን፣ ከግጭት ቂምን ሳይሆን ፍቅርን፣ ከስህተት ስህተትን ሳይሆን እርምትን እንማር ዘንድ ነው። እናም እኔ ካሜሪካኖች ታሪክ የተማርኩት የመጀመሪያው ቁምነገር ይህንን ነው። ሌላውን ሌላ ጊዜ ማንሳቴ አይቀርም። ሰላም ሁኑልኝ፡፡

ህሩይ ደምሴ

ከዋሽንግተን ዲሲ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. eunetu says

    March 18, 2016 04:03 pm at 4:03 pm

    ወንድሜ ህሩይ

    በወገኔና በአገሬ ላይ ከገጠመኝና አልወለድ ካለ የጽንስ ምጥ የገላገልከኝ መሰለኝ!ለካ እንዲህ እንዳንተ ያሉ ቅን ሃሳብ ያላቸው ወንድሞች በየቦታው አሉ በማለት ከእንቅልፌ ነቃሁ! በርታ ወንድሜ! አብረን እንጬህ በጎ የሆነውንም በተግባር እናሳይ!በለው፣ አሳደው፣ ድፋው፣ አሳየው፣ ፉከራው፣ ጥላቻውና መነቋቆሩ ወዘተ የትም አላደረሰንምና በፍቅር ለሁለንተናዊ የዘመናት ችግራችን በጋራ ምክክር አብረን ለበጎ ሥራ እንነሳ???

    ይህችን አባባልህን ወደድኳት:

    እኔ ግን የተማርኩትና ያገሬ ሰውም እንዲማር የምመኘው ከጦርነት ጥፋትን ሳይሆን ደህንነትን፣ ከግጭት ቂምን ሳይሆን ፍቅርን፣ ከስህተት ስህተትን ሳይሆን እርምትን እንማር ዘንድ ነው። እናም እኔ ካሜሪካኖች ታሪክ የተማርኩት የመጀመሪያው ቁምነገር ይህንን ነው። ሌላውን ሌላ ጊዜ ማንሳቴ አይቀርም። ሰላም ሁኑልኝ፡፡

    መልካም ፈቃድህ ከሆነ በኢሜል ተገናኝተን በመመካከር ለምስኪኑ ወገናችን ሰላም በእግዚአብሔር ስም በጎ ሥራ አብረን እንሥራ: eunethiwot@gmail.com

    የፍቅር አምላክ በመለኮታዊ ፍቅሩ በጽሑፍህ ላይ ከገለጥከው በበለጠ መልኩ:
    ለራሱ ክብር!
    ለምስኪኑ ወገንህ ጥቅምና ሰላም!
    ለክፉው ደግሞ መዋረድ!
    በሃይልና በስልጣን ይግለጥህ!!!

    ይህ ከሆነ ሕልምህ እኔም አብሬህ ነኝ!!!

    በእውነት ወንድምህ

    እውነቱ ነኝ

    Reply
  2. Yikir says

    March 29, 2016 09:31 pm at 9:31 pm

    Mikirih melkam new hizibum yaminal. Hulum sew Mihur Mehayimu yemisasatew neger:- Ethiopian yemimeraw akal Satan /LUSIFER MEHONUN / YIZENEGALU. Wendime eski hasabihin le Lusiferu asredaw.KETEKEBELEH WEDE AGANINTINET ZIK BILOWAL MALET NEW 10 % KETEGEBERE JINI HONWAL MALET NEW. 50 %ketekebeleh yih jini tamo yihonal.ANTE YALKEWIN 90% KETEKEBELE YIH JINI MOTOWAL MALET NEW. Lije berta jiniw bimot le Ethiopiachim melkam new.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule