በእንግሊዝ ሃገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ገንዘብና ጉልበቱን አስተባብሮ በእግዚአብሔር ተራዳዒነት የገዛውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ለወያኔ ሹማምንት አሳልፈው በመስጠት ሥልጣንና ንዋይን የሚያጋብሱ የመሰላቸው የለንደኑ ዳያብሎስ አባ ግርማ ከበደና ተከታዮቻቸው፤ የቤተ ክርስቲያኑን አባላት መብት የሚነፍግ ተግባር ፈጽመው አባላቱ በቤተ ክርስቲያኗ ንብረት እኩል የመገልገል መብታቸው እንዲከበርላቸው ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው በ13/02/2013 በዋለው የእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት ተፈረደላቸው።
ይህንን አስመልክቶ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔና ያወጣውን ትዕዛዝ (interim relief order ) አባ ግርማና ተከታዮቻቸው ተግባራዊ አናደርግም በማለታቸው የፍርድ ቤትን ትዕዛዝ ባለማክበረ (በContempt of Court) ተከሰው በ12/03/2015 እንደገና ከፍተኛው ፍርድ ቤት በCommittal hearing ላይ ቀርበው እንደነበር ከአሁን በፊት መገለጹ ይታወሳል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply