• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በጅዳ እና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ክራሞት

January 7, 2014 12:24 am by Editor 1 Comment

ካሳለፍነው ወር ጀምሮ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች ባቀረቡት ቅሬታ “ወደ ሃገር እንዳንገባ ተደርገን እየተጉላላን ነው!” ብለውኛል። በቀን በሚሰጠው ደረቅ ብስኩትና ጥራቱ ባልተጠበቀ ሩዝ መጉዳታቸውን የገለጹልኝ ሲሆን መፍትሔ የሚሰጠን የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ተወካዮች አጥተው ቀን በጸሃይ ፣ ማታ በብርድና በቁር እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ወደ ሃገር እንግባ ብለው በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡት መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች እዚህ በጅዳ ሽሜሲ ብቻ ሳይሆን በሪያድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንግልት እየደረሰብን ያሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸውልኛል።

ሁከት በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ-

ከጅዳ መካው የሽሜሲ መጠለያ ተነስተው ወደ ሃገር ለመሳፈር  በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አየር መንገድ ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ቁጥራቸው 1500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን “የያዛችሁት እቃ ከሚፈቀደው ኪሎ በላይ ነው!” በሚል የተፈጠረው አለመግባባት  ማክሰኞ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ እንደነበር እና ከሰአታት በኋላ መረጋጋቱን ተደጋጋሚ መረጃ ደርሶኛል።  የማክሰኞው ሁከት መነሻ የተመላሾችን የተከማቸ እቃ ለማየት ወደ ቦታው የደረሱትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊ በቦታው መድረሳቸውን ተከትሎ ሲሆን በእንግልቱ የተበሳጩት ዜጎች ሁከት መቀስቀሳቸው በአይን እማዘኞች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ  ለመረዳት ችያለሁ። የአይን እማኞች አክለውም ዜጎች ከሃላፊው ጋር ሊጋጩ ሲሉ በጸጥታ አስከባሪዎች ብርታት መትረፋቸውን ከቦታው  በሰአቱ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ግርግሩ ለሰአት ያህል የቀጠለ ቢሆንም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም። ሁኔታውን ለማረጋጋት በቦታው የተገኙ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ማረጋጋት ከፈጠሩ እና ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ የአየር መንገዱን ሃላፊ ለጥያቄ ወስደዋቸው እንደነበርና ሃላፊውን ለማስለቀቅ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና ጅዳ የመጡት የሪያዱ አንባሳደር ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ከሰአታት በኋላ ሃላፊውን ይዘው ምሽት ላይ መመለሳቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል።saudi ethio j1

የሃላፊውን ለጥያቄ መቅረብ ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው አንድ ውስጥ አዋቂ ሲናገሩ ”  በአውሮፕላን አቅርቦት እጥረት እና እቃችን ሳንይዝ ወይም በአደራ ተቀብሎ ወደ ሃገር የሚያስተላልፍልን እስካላገኘን ወደ ሃገር አንገባም ያሉትን ዜጎች ጉዳይ እንዲመለከቱ በቆንስላው ጥያቄ ወደ አየር ማረፊያው ያቀኑት የአየር መንገዱ ሃላፊ ስለ ዜጎች መጉላላት መረጃ እንዳልነበራቸውና በቦታው ሲደርሱ ከሁከቱ ጋር ተያይዞ ግራ ተጋብተው ታይተዋል።” በማለት ሲያስረዱ በቆንሰሉና በአየር መንገዱ ሃላፊዎች መካከል የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገላልጠው አጫውተውኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ከ40 ኪሎ በላይ እቃ መውሰድ አትችሉም የተባሉ ዜጎች እቃ ሃጅ ተርሚናል በሚባለው የአየር መንገዱ ማረፊያ ቦታ በብዛት ተዝረክርኮ እነወደሚገኝና የብዙዎች እቃ አድራሻ እንደሌለው የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።  “አድራሻ ያለውን እቃም በሚመለከት የጅዳ ቆንስል ሰብስበን እንልከዋለን የሚል ቃል ከመስጠት ባለፈ ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ እንዳልወሰዱም” በማለት እማኞች ገልጸውልኛል።

ከአስር ቀናት ያላነሰ እንግልታቸውን  በማስረዳት የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማላቸው እንባቸውን እያዘሩና በብስጭት ያስረዱኝ ወገኖች በበኩላቸው “የአውሮፕላኑን ወጭ የሳውዲ መንግስት ከቻለ የኢትዮጵያ መንግስት እቃችን ይዘን እንድንገባ ለምን አላመቻቸልንም?  ሌላው ቢቀር መንግስት በሻንጣው መጫንና ለሳምታት ብስኩት እየተሰጠንና በውሃና ምግብ ግዠ የያዝነውን ገንዘብ ስናጠፋና ስንሰቃይ በዚህ ካልረዳን ወገኖቸ ማለቱ አልገባንም! ዜጎች አይደልንም?” ሲሉ በማጠየቅ በተጎዳ ሰሜት ገልጸውልኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወንድም እንደገለጹልኝ  ዜጎችን ማጓጓዙ እንደ በፊቱ በፍጥነት ባይከወንም አልፎ አልፎ መቶና ከመቶ በላይ ዜጎች በተገኘ የበረራ ክፍት ቦታ እየተላኩ መሆኑን በማስረዳት  ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር የቆንስሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ለቆንስል ሃላፊዎች ማሰማታቸውን በመግለጽ መፍትሔ ግን እስካሁን አለመሰጠቱን አክለው ገልጸውልኛል።

የካርጎ መዘጋት መዘዝና የነዋሪዎች ሮሮ-saudi ethio j2

የአየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት ለወራት መሰናከል ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በእቃ አቅራቢ የካርጎ ኤጀንቶች በደል ደረሰብን የሚሉ ዜጎች  ቅሬታ እያሰሙ ነው። ይህ ችግርም በነዋሪዎችና በካርጎ ኤጀንሲ ሰራተኞች መካከል ውዝግብ ማስከተሉ አልቀረም። የአየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ከስድስት ወራት በላይ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከተዘጋ በኋላ ሰሞኑን ስራ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ያም ሆኖ በጅዳ ዙሪያ ያሉ የካርጎ ኤጀንሲዎች “ወደ ኢትዮጵያ የካርጎ ግልጋሎት በተለያዩ አቅጣጫዎች እንሰጣለን!” በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ለእቃው ማስጫኛ እየተቀበሉ እቃውን ቢረከቡም ከስድስት እሰከ አስር ወራት ለሚቆይ ጊዜ እቃውን በመጋዘ ቃላቸውን ጠብቀው እንዳላደረሱላቸው የመጫኛ ማስረጃቸውን እያሳዩ ቅሬታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ዎች ናቸው። የሳውዲ ውጡ ህግ ከተነገረ ጀምሮና ከዚያም ወዲህ በተሰጠው የሰባት ወር የምህረት ጊዜ ጠቃሚ የሚሏቸውን ጥሪት እቃቸውን ለካርጎ ቢያስረክቡም አንድም በካርጎው መዘጋት በተጓዳኝ በካርጎ ኤጀንሲዎች ለአንድ ኪሎ እስከ 10 ሪያል በመክፈል እቃቸውን ቢያስገቡም እቃቸውን ደህንነት በማያውቁበት ደረጃ በንብረታቸው ላይ ብክነት እንዳስከተለባቸው እያዘኑ ሮሯቸውን አጫውተውኛል።

በጀዛን የዜጎች እንቢታ እና የህግ ታሳሪዎች ሮሮ –

በጀዛን “ወደ ሃገር እንግባ!” የሚሉ ነዋሪዎችን ጥሪ ተከትሎ የመጓጓዣ ሰነድ ለመስራት የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ተወካይ ዲፕሎማት ወደ ቦታው ያቀኑ ቢሆንም “ድረሱልን!” ሲሉ የነበሩ ዜጎች የውሃ ሽታ መሆናቸውን የኮሚቴውን በፊስ ቡክ መኖሩን የሚያሳውቀን የወገን ለወገን saudi ethio j3የህዝብ ግንኙነት ፊስ ቡክ ጠቁሞናል።  በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞችም በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ዛሬም አላቆመም። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል!” እያሉ ነው!  በጀዛን ዙሪያ ባሳለፍነው ሳምንት መረጃ ያቀበለን የወገን ለወገን ደራሽ የህዝብ ግንኙነቱ ገጽ ባስተላለፈው መረጃ ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ሰላላሳዩት ዜጎች ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ወደ ሃላፊዎች ለመቅረብ እና ለመሸኘት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ሲገልጽም “እነሆ ግዜው ደረሰና የሁለቱም ሃገር መንግስታት ሁኔታዎችን አስተካክለው በሰማት (አሻራ) የሚሰጡበት ቦታ ተበጅቶላቸው ከቆንስላ ፅ/ቤት ተወካይ በቆንስል አህመድ የሚመራ ቡድን ለዜጎቻችን እዚያው እንዲሰራላቸው በማሰብ ወደ ጂዛን ተጓዙ። አሁንም እዚያው ናቸው። ነገር ግን ነገሮች እንደታሰቡ እየሄዱ አይደለም። ታስቦላቸው የተሄደላቸው ወገኖች እየወጡ አይደለም የሚል አሳሳቢ ዜና ሰማን። አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ማቆያ የሚገቡት ሰዎች በቀን መቶም እንደማይደርሱ ተገለፀልን። ከጂዳ ለዚህ ጉዳይ የተንቀሳቀሰው ልኡካን አሁንም ለማገልገል ይጠብቃል፡ ምንም የሚታይ ነገር ግን የለም። በጂዛን አጎራባች ወደ ሆኑ ከተሞችም ከአካባቢው ማህበረሰብ አምስት አምስት ሰዎች ለቅስቀሳ ተልከዋል። ቢሆንም ወገናችን ዜጎቻችን የሚወጡ አይነት አይደለም። በጣም ሚገርም ነው።” ይላል።  የህግ ታሳሪዎች በበኩላቸው የቆንስል ሃላፊዎችን አነጋግረዋቸው “ለእናንተ ጉዳይ አልመጣንም!” እንዳሏቸው ገልጸውልኛል። የህዝብ ግንኙነቱ ዜጎች ወደ ኋላ ስላፈገፈጉበት ጉዳይም ሆነ በደል ደረሰብን ስለሚሉ ህጋዊ ታራሚዎች የሰጠው መረጃ የለም ። በወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴ ለአንድ ወር በስራ አስፈጻሚነት የሰራሁ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ለቆንስል ሃላፊዎች ያቀረብኩት የዜጎች አቤቱታ እንዲታረም በተደጋጋሚ አሳስቤ የነዋሪውን አቤቱታ በጀርመን ራዲዮ በማቅረቤ በተወሰደ የ “በዲሲፕሊን!” እርምጃ ከኮሚቴው አባልነት በተጽዕኖ መነሳቴ ይታወሳል!

የውጭ ጉዳይ ልዑካን በጅዳ:-

በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡድን ከሶስት ቀናት በፊት ጅዳ ገብተዋል። ልዑካኑ በእስካሁኑ ቆይታቸው የኢህአዴግ የድርጅት አባላትንና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎችን በዝግ ያነጋገሩ ሲሆን የውይይታቸው ትኩረት በመጡበት የዜጎችን ወደ ሃገር መግባት ጉዳይ የማፋጠን ስራ ይሁን በሌላ ተዛማጅ ጉዳይ የሚታወቅ ነገር የለም። የልዑካን ቡድኑsaudi ethio j4 አባላት በእስካሁን ቆይታቸው አደጋውን ለመከላከል በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች የተቋቋመውን የወገን ለወገን ደራሽ ጊዜያዊ ኮሚቴ እስካሁን ያላነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። የልዑካኑ ቡድንን ኮሚቴውን አለማነጋገሩ ቅያሞት የገባቸው አንዳንድ አባላት በበኩላቸው የዜጎች እንግልት በቅንጅት ጉድለት እየተበራከተ በሄደበት በዚህ አጋጣሚ ኮሚቴው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ላልቻለበት ሁኔታ የቆንስሉ እና የአመራሩ ድክመት እንደሆነ በማስረዳት እያደር ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ ወገንን ለመርዳት ከመካዝን ያለውን ውሃ ለማደል እንኳ አቅም አጥቷል በሚል ከማህበረሰቡ ወቀሳ እየቀረበበት መሆኑን በግልጽ አጫውተውኛል።

በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑክ በጅዳ ቆንስል የመንግስታችን ተወካዮች ለተጠቀሱትና በከባቢው ላሉ ችግሮች አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰዱ አደጋውን መታደግ ከማንችልበት ደረጃ እንዳይደረስ የብዙ ነዋሪዎች ስጋት ሆኗል። የሳውዲ መንግስትን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስል በማስታወቂያ ብቻ የተደገፈ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ “ሰነድ የሌላችሁ ዜጎቸወ ከሳውዲ ውጡ!” በሚል ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። ያም ሆኖ ነዋሪው በርካታ ያልተሟሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማቅረብ ለመውጣቱ ጥሪ “አሻፈረኝ!”  ያሉትን በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሮሮ እና ጥያቄ ለመስማትና አፋጣኝ የመፍየትሔ እርምጃ ለመውሰድም የመንግስት ሃላፊዎች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት መፍትሔ ያመላክቱ ዘንድ ደግሜ ደጋግሜ እመክራለሁ!

ዛሬም የመረጃ ክፍተቱ ይዘጋ፣ የምንናገረው ተጨባጭ መረጃ መሆኑን አጣርታችሁ መፍትሔ አፈላልጉ ስል ደጋግሜ “ጀሮ ያለው ይስማ!” እላለሁ !

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Sara says

    January 11, 2014 02:53 am at 2:53 am

    In my view these people at the king’s should thank God for the opportunity to save their life not grumble about their belongings. They are so ungrateful.

    All these folks at the king’s airport are delaying those who have not yet had the opportunity like those Ethiopians in Hospitals, Prison etc. You have to realize even a flight you paid for does weight limit. In the time you wasted arguing about your belongings, more people like those in prison and hospitals could have been helped. I say shut up, don’t be selfish and go back home.

    I suggest first of all praise your God , thank the Ethiopian Authorities, all other organizations such as the Red Cross and your Ethiopian brothers and sisters who were fasting and praying crying out to God for your safety.

    I su

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule