• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“… መብከት፣ መበስበስ ከአንዴ በላይ ይደብራል …” ሕዝብ

September 6, 2016 08:41 pm by Editor 2 Comments

ከመተካካት አልፈው ራሳቸውን “recycle” ያደረጉትን የህወሃት/ኢህአዴግ ሹሞች ያካሄዱትን ውይይትና የሕዝቡን አስተያየት የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ዘግቧል – “የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ሁኔታ” በሚል ርዕስ የታተመው ዘገባ እንዲህ ይነበባል:-

ኢትዮጵያን የሚመራዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በቅርቡ ካካሔደው ግምገማ በኋላ በሥራ አስፈጻሚዎቹ ዘንድ ሹም ሽር ሊያካሂድ መሆኑን እየተናገረ ነው። የገዢው ግንባር ሹም ሽርም ይሁን ግምገማ ግን ለውጥ ለማምጣቱ በርካቶች ጥያቄ አላቸው።

ከሩብ ምዕተ-ዓመት በላይ በስልጣን ላይ የቆየው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት ተሿሚዎቹን ሊገመግም እንደሆነ አስታውቋል። ከጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ አማካሪዎች መካከል አቶ አባይ ፀኃዬ ግንባሩ የመንግስት ተሿሚዎችን «አመኔታ በሰራተኛ፤ በሕዝብ በፓርቲ ዘንድ አለው ወይስ የለውም? ውጤታማ ነው? ውጤታማ አይደለም?» ብሎ ሊገመግም እንደሆነ ጠቁመዋል። ሌላዉ የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን በበኩላቸው «የመንግስት አስፈጻሚ አካላትን በአዲስ መልክ እናደራጃለን» ሲሉ ተደምጠዋል።

የዶይቼ ቬለ የፌስቡክ ገፅ ተከታታዮች ግን የኢህአዴግ ሹም ሽር ለውጥ ማምጣቱን ይጠራጠራሉ። አስተያየት ከሰጡት አንዱ፤ ጌትነት በላይ «ኢህአዴግ እኮ በ1993 በክቶ እንደገና ታደስኩ ብሎ መቅረቡ ይታወሳል። መብከት፣ መበስበስ ከአንዴ በላይ ይደብራል። አሁን እኮ በህዝብ ላይ ጦርነት በይፋ ታውጇል። ማንን ለማስተዳደር ነው መታደስ የሚያስፈልገው?» ሲሉ ይጠይቃሉ። «አንድን ጥያቄ መፍታት ጥያቄውን በቅጡ ከመረዳት ይጀምራል» የሚሉት ዮሐንስ አያሌው «ገዢው ፓርቲ የሚያልመው ለውጥ ከሕዝብ መሰረታዊ የለውጥ ጥያቄ» ጋር እንደማይጣጣም ፅፈዋል። ቹቹ ደግሞ «ላይኛውን ማን ያደራጀው? ሁሌ ታችኛው አመራር ጥፋተኛ ከተባለ የሱ አለቃስ ላይኛው ጤነኛ ይሆን?» ብለዋል።

ኢህአዴግ ‘ተሐድሶ’ ያስፈልገኛል ያለው የአስራ አምስት አመታት የስራ ክንውኑን በአራት ቀናት ከገመገመ በኋላ ነው። ግንባሩ ከዚህ ቀደም የገጠሙትን ፖለቲካዊ ቀውሶች በግምገማ ለመፍታት ቢሞክርም መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት ግን የቻለ አይመስልም። የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ቻላቸው ታደሰ ኢህአዴግ የሚከተለውን የዴሞክራሲ ማዕከላዊነት መርሕ «ያልተቀደሰ ጋብቻ» ይሉታል።

ይህ የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርሕ በአባል ድርጅቶች እና በግንባሩ መካከል ያለውን ግንኙነት ሚዛን አዛብቶት ቆይቷል። አራት ፓርቲዎችን የያዘው ኢህአዴግ በሥራ አስፈጻሚነት የሚያካሂዳቸው ሹም ሽሮች ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ናቸው እየተባሉ ይተቻሉ። ሰሞኑን ከከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትርነታቸው የተነሱት አቶ መኩሪያ ኃይሌ መልሰው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አማካሪ ሆነዋል። ኢህአዴግ አባል ያልሆኑ ግን ደግሞ በሙያቸው ብቁ ግለሰቦችን በሥራ አስፈጻሚነት ለመሾምም ዝግጁ አይመስልም።

ባለፈው ዓመት የተካሔደውን አገር አቀፍ ምርጫ በየክልሎቻቸው መቶ በመቶ ድምፅ በማግኘት ያሸነፉት ብአዴን እና ኦህዴድ ዘንድሮ የተቀሰቀሰባቸውን ጥያቄዎች መመለስ የሕግ የበላይነትን ማስጠበቅ እና ሕዝባቸውን ማረጋጋት ተስኗቸዋል። ሁለቱ ፓርቲዎች በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ተዓማኒነትም ጥያቄ ውስጥ የወደቀ ይመስላል። በዶይቼ ቬለ የፌስ ቡክ ገፅ አስተያየታቸውን ያሰፈሩት አባ ጨብሳ «ሁለቱም ዱቄት ናቸው።» ይላሉ። ጃክ ካሬስ በበኩላቸው «ሁለቱም እኮ አቅም የላቸውም በራሳቸው በራሳቸው ምንም ነገር መወሰን አይችለም ስለዚህ በህዝቡም ዘንድ ተቀባይነታቸው አይታየኝም» ብለዋል። ሳዴን ሳዶ ሳዴን ፓርቲዎቹን «የህወሃት ጉዳይ አስፈፃሚዎች» ይሏቸዋል። ይነጋል በሚል ሥም አስተያየት ያሰፈሩ ሌላ ግለሰብ «የሞግዚት አስተዳደር እንዴት ተቀባይነት ይኖረዋል?» ብለው ጠይቀዋል። አቶ ቻላቸው ታደሰ የኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎችን የሚያስተዳድሩት ኦሕዴድ እና ብአዴን እና በግንባሩ መካከል ያለው የስልጫን ክፍፍል ፍትኃዊ እንዳልሆነ ይናገራሉ።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Ayu asfaw says

    September 7, 2016 06:07 am at 6:07 am

    Gulcha bikeyayer Wot Ayataftem !!!

    Reply
  2. Lusif says

    September 9, 2016 10:57 pm at 10:57 pm

    What they do not understand is that they are products of the sixties communist conflict ideologists who strongly believe domination of a group over the masses. The strategic means to this domination is political and economic power through violence and animosity They only feel they are only responsible to their close relatives and group. That is why they call themselves a dominante group/ party.
    Such mentality has overlived it’s time and became morbid. The new generation has already acquired a new different political, economic and social order. Unity with mutual respect and equality, economic self interest with equal opportunity, compassionate individual with social responsibility.There is a clear generational gap.
    These two understandings are mutually exclusive. The group mentality can only survive by suppressing and undermining the new mutual social responsibility. The new social responsibility paradigm can only grow upon the grave of group mentality. So the struggle is between the old dieing status quo and the new embryo of freedom, equality, justice and democracy. The old relays on relative peace managed by force, the new one on enduring peace managed by consensus and democracy.
    It is a historical fact and inevitable the ruling party with its old garbage, must go unless it makes informed and wise decision and make a U turn.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule