• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሞረሽ የዐማራ ድምፅ የሬድዮ ጣቢያ ማቋቋም ለምን አስፈለገ?

March 17, 2016 01:58 am by Editor Leave a Comment

ባለፉት ፳፭(ሃያ አምሥት) ዓመታት በዐማራው ላይ የሚፈጸመው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከችግሩ ሥፋት እናጥልቀት አንፃር ተመጣጣኝ የሆነ የሚዲያ ሽፋን አልተሰጠውም። በ«ኢትዮጵያዊነት» ስም በተቋቋሙት ድርጅቶችም ሆነ በተለያዩ አገሮች መንግሥታት ሥር የሬድዮ እና የቴሌቪዥን መርኃ-ግብሮችን በአማርኛ ቋንቋ የሚያሠራጩ ሚዲያዎች በዐማራው ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና በደል የዓለም ማኅበረሰብ እንዲያውቀው የማድረግ ፈቃደኝነታቸው እጅግ ውስን መሆኑን በተደጋጋሚ ታይቷል። ይህም «ችግሩ ችግራችን ነው» ብሎ የሚይዝ ሚዲያ አለመኖሩን ያረጋግጣል። ስለሆነም እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አባሎች እና ደጋፊዎችለመላው የዐማራ ሕዝብ ድምጽ የሚሆን የሬድዮ ጣቢያ ለማቋቋም ቆርጠን ተነስተናል። ዐማራው በተገንጣይ እና ጠባብ የጎጠኞች ቡድኖች የተክፈተበትን የሥነ-ልቦና ጦርነት ተመጣጣኝ በሆነ ኃይል በመመከት እውነተኛውን ገፅታ ለማሣየት፣ የሚያስችል የአጸፋ ፕሮፓጋንዳ እና ቅስቀሣለመሥራት፣«ሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ» በአየር ላይ መዋል ለነገዳችን ህልውና በጣም አስፈልጓል።

ለሩብ ምዕተ-ዓመት በዘለቀው የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ፣ ክ፭(አምሥት) ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን በልዩ ልዩ መንገዶች ከምድረ ገፅ እንዲጠፉ ተደርጓል። ይህን ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ለፍትኅ ለማቅረብ የተቀነባበረ የመረጃ ልውውጥ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም። የዐማራውን ነገድ ለመታደግ የሚቻለው ዐማራው ተደራጅቶ በኅብረት ጥቃቱን ሲመክት ነው። ሰለሆነምዐማራው የሚፈጸምበትን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ለመቋቋም የሚችለው፣በጠንካራ መሠረት ላይ ተደራጅቶ የሚደርስበትን ጥቃት ለመቋቋም ሲዘጋጅ መሆኑን መቀመበል ያስፈልጋል። ለዚህም ተጣጣኝ የሥነ-ልቦና ትጥቅ ለመታጠቅ የሬድዮ ድምጽ አስፈላጊ ነው። በዚህ ረገድ የዐማራው ልጆች «የወገናችን ችግር ችግራችን ነው፤ ብሦቱም ብሦታችን ነው፤ ከሁሉም በላይ ዘራችን መጥፋት የለበትም» ብለን ከተነሣን፣ እንኳንስ እንዲት የአጭር ሞገድ የሬድዮ ጣቢያ ማቋቋም ቀርቶ፣ ሁሉን-አቀፍ የሆነ የዐማራ ሚዲያ ማዕከል ለመመሥረት መቻላችን ጥርጥር የለውም።

በመሠረቱ የዐማራው ሕዝብ ጠላቶች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች ናቸው። ዐማራው እንዲጠፋ የተወሰነበት አብይ ምክንያት በታሪኩ የሚተማመን፤ አትንኩኝ ባይ፤ለነፃነቱ ቀናዒ፤ለህልውናው እና ለአገር ዳር ደንበር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ሟች ፍፁም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነው። በዐማራው ነገድ ላይ ጥቃት የተጀመረው ዛሬ ሣይሆን ከ፭፻(አምሥት መቶ) ዓመታት በፊት በቱርኮች እና በአረቦች ድጋፍ ግራኝ አሕመድ ካካሄደብን የጅምላ ጭፍጨፋ ጀምሮ እንደሆነ ይታወቃል። ከግራኝ ጭፍጨፋ ተከትሎ የኦሮሞዎች ወረራ ተከተለ፤ ከዚያም በዘመነ-መሣፍንት ከፍተኛ የሆነ ዕልቂት የደረሰው በዐማራው ላይ ነበር። ፋሽስት ኢጣሊያም ከአንዴም ሁለቴ ከፍተኛ ጥፋት ያደረሰችው በዐማራው ላይ ነበር። ደርግ ገና ሥልጣን ከመያዙ አስቀድሞ የዘመተው በዐማራው ላይ መሆኑ የቅርብ ዘመን ትውስታችን ነው። የትግሬ-ወያኔ ዘረኞች ገና ከጠዋቱ በርሃ ሲገቡ ጀምረው በፕሮግራማቸው ያሰፈሩት ዋና ጠላታቸው ዐማራ እንደሆነ እና ከተቻለም ከኢትዮጵያ ምድረ ገጽ እንዲጠፋ፣ካልሆነ ደግሞ አቅመቢስ ባርያቸው አድርገው ለመግዛት መሆኑ ግልፅ ነው። ይህንን ጽኑ ፍላጎታቸውን እውን ለማድረግ ከበረሃ ጀምረው በዐማራ ሕዝብ ላይበፍርሃት ተጨምድደው በመሠረቱት ጥላቻ፣ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስሙን ጥላሸት ቀብተውታል፤ መሬቱን ቀምተውታል፤ በአገሩ ላይ ሁለተኛ ዜጋ በማድረግ ከኖረበት ቀዬው እንዲፈናቀል አድርገውት እናያለን። ለዚህም ማረጋገጫው ላለፉት ፶(ሃምሣ)ዓመታት በሻቢያ፣ በትግሬ-ወያኔ እና  በኦነግ አማካይነት በዐማራው ሕዝብ የተፈጸመው የሥነ-ልቦና ጥቃት ሕዝባችንን ከነበረበት በራስ የመተማመን ደረጃ አወርዶት ይገኛል። ዐማራው ይህን በረቀቀ እና በግልፅ በተቀነባበረ ሥልት የሚፈፀምበትን አደገኛ የሥነ-ልቦና ምት፣ ሁለገብ የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ሊቋቋም የሚችለው በአንድ ዐላማ ሥር አንድ ሆኖ ሲቆም ብቻ ነው።ሰለሆነም «ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምፅ» የተጎዳውን የወገኖቻችን ሥነ-ልቦና ለማደስም ሆነ የወንድማማችነት  መንፈስ ለማጎልበት ያገለግለናል።

ለአንድ ዓላማ ግብ መምታት በሥርዐት ላይ የተመሠረተ ዝግጅት እና መሠናዶ እጅግ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ይህ አካሄድ በግል ሕይዎታችንም ስኬት ለማግኘት ያስችላል። ለመዘጋጀት እና ለመስናዳት ደግሞ ቅንብር እና ድርጅት ያስፈልጋሉ። መደራጀት ጠላትን ለይቶ ለመመከት እና አሸንፎ ለመውጣት ያግዛል።

መደራጀት ተመጣጣኝ ኃይል ፈጥሮ በማናቸውም ጊዜ እና ቦታ  ለድርድር ያበቃል። ስለሆነም የሬድዮው ድምጽ በትግሬ-ወያኔ የተመዘዘበትን የጥፋት ሰይፍ ወደ አፎቱ ለማስገባት ዐማራው ለአንድ ዓላማ፣ በአንድ ልብ፣ በፍጹም የወንድማማችነት መንፈስ መነሣት እንዲችል፣በእውነት እና በእውቀት ላይ የቆመ የፕሮፓጋንዳ እና የቅስቀሣ ስራዎችን ለማክናወን የሚያስችል ፍቱን መሳሪያ ነው። ሞረሽ የዐማራ ድምጽ ሬድዮ«ዐማራው ከገባበት አጣብቂኝ ወጥመድ ሰብሮ ለማምለጥ ምን ማድረ አለበት? እንዴትስ በይፋ በአገር አቀፍ ከታወጀበት የዘር ማጽዳት ሤራ እርምጃ ሊተርፍ ይችላል?» የሚሉትን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በመዳሰስ በኢትዮጵያ ምድር እንደስፌድ ቆሎ ተብትኖ ለሚገኙት ዐማራ ወገኖቻችን ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን እንዲደርስ ያደርጋል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የካቲት1 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥር ሞወዐድ 000100-08 «ሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ጥሪ» በዓለም ለሚገኙ ዐማራ ወገኖች እና ወዳጆች ማቅረቡን በዚህ አጋጣሚ ለማስታወስ እንወዳለን። «ለወገን ችግር ፈጥኖ ደራሹ ወገን ነውና» በሜልበርን (አውስትራሊያ) እና በካልገሪ (ካናዳ) የሚገኙ የሞረሽ-ወገኔ  መሠረታዊ ማኅበራት አባሎች እና ደጋፊዎች የጉዳዩን አጣዳፊነት እና አስፈላጊነት ጠንቅቀው በመገንዘባቸው፣እሑድ የካቲት27 ቀን 2008ዓ.ም. የመጀመሪያ ዙር የገንዘብ እርዳታ ማሰብሰብ ዝግጅት አከናውነዋል። ይህ ጥረት በሚገባ ተጠናክሮ በሁሉም የዓለማችን ክፍሎች ሊቀጥል ይገባዋል።ዐማራው ከገባበት የሚያባራ ጥቃት እና ሰለባ ሊያመልጥ የሚችለው፣ በንጹህ የመላው ዐማራ የወንድማማችነት/እህትማማችነት መንፈስ በአንድነት ቆሞ በምድር ውስጥ የቁም ስቃይ እና መከራ ለሚበላውወገናችን ድምፅ ሲሆን ብቻ ነው። በመሆኑም «ሞረሽ የዐማራ ድምጽ ሬድዮን» ተረባርበን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአየር እንድናበቃው በዐማራነታችን የሚጠበቅብንን ግዴታ እንድንወጣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ለመላው የዐማራ ሕዝብ ያስተጋባል።

የዐማራው ኅልውና ጉዳይ ለዐማራው ብቻ ሊተው አይገባም። የእንቁጣጣሽ በግ ሲታረድ የመስቀሉ በግ ይስቃል እንዳይሆን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከአገራችን ምድረ ገጽ እንዲጠፋ ከተበየነበት የዐማራ ሕዝብ ጎን በመቆም የዜግነት እና የንፁህ ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት ድርሻ ሊወጣ ይገባዋልና ሞረሽ የዐማራ ሬድዮ ድምጽ እንድትረዱ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ እናቀርባለን።

በግፈኛ ዘረኞች ድምፁ ለታፈነው ዐማራ ድምፅ እንሁነው!
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በጀግኖች እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule