ዶ/ር ሰይድ ሃሰን (መሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ) መስከረም 1፣ 2009 በሲንሲናቲና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ያቀረቡት አጭር የንግግር ንጥረ ሀሳብ (ተቀርፎ የወጣ)
የንግግሬ ንጥረ ሀሳቦች በ4 ይከፈላሉ፡
- በኢትዮጵያ የተከሰተው ሙስና ምን ይመስላል? እንደትስ ማስወገድ ይቻላል?
- ሙስናው በኤኮኖሚው ላይ ያመጣው ክስረት፤የሙስና ንቅዘት የሕዛባዊ አመፁ አንዱ ምክንያት መሆኑ፤
- የህዝባዊ አመፁ በኤኮኖሚው ላይ እያደረሰ ያለው ክስረት፤
- ከኛ (ከዲያስፖራው) ምን ይጠበቃል?
ሀ) በኢትዮጵያ የተንሰራፋው የሙስና ንቅዘት ጠባይ ምን ይመስላል?
- የኢትዮጵያን ሙስና በሚመለከት በርከት ያሉ ጽሁፎችንና ንግግሮችን አድርጌአለሁ። በዚህ ጉዳይም እቀጥላለሁ። በኢትዮጵያ ኢላይ ተንሰርፍቶ ያለው ሙስና ተመሳሳይነቱ በዩክሬይን፤ በራሽያና ተመሳሳይ ሀገሮች የተከትሰተውን አይነት አይን ያወጣ ዝርፊያ መሆኑን አመላክቻለሁ። በነዚህ ሀገሮች ከተከሰተው ሙስና የጣም የከፋ መሆኑንም አሳይቻለሁ። እሱም የገዥዎች ነጠቃ የሙስና ንቅዘት (state capture)-ይባላል። እንደዚህ ያለው ሙስና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንን በማቋቋም ሊወገድ አይችልም! ሙስናው ከነሥርዓቱ መወገድ አለበት።
- ባሁኑ ጊዜ ተጧጡፎ የሚገኘው ሕዝባዊ አመጽ በሀገሪቱ ላይ የተንሰራፋው ሙስና ነጸብራቅ ነው። ያመጸውም ሕዝብ የሚያስተጋባው መፈክር ይህንኑ ያለመክለክታል። “ዎያኔ ሌባ፤!” “ዎያኔ ውሸታም!” … እያለ ያስተጋባል መፈክሩ!
- የህዋሀት/ኢሕአደግ መንግስትያለ ሙስና ሊኖር አይችልም። ምክንያቱም፤
- የሕወሃት/የኢሕአደግ ቁንጮ መሬዎች በሙሉ ዘራፊዎችና በሙስና የተዘፈቁ ስለሁኑ ከነሱ በታች ያለው ሁሉ የዝርፊው ተጋሪ መሆን አለበት፤ ይጠበቅበታልም፤
- የአናሳ ቡድን መንግስት እንደመሖኑ፤ የሌላ ብሄር አባጋዞችና ተጠቃሚዎችንም ወደ ሙስናው አስገብቶ በማነቆ ማስገባት አለበት። ይህንንም አድርጓል። (አንጋፋው የኢሳትጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንዳሳየንና እንዳስገነዘበን ሁሉ).
በነገራችን ላይ፤ አስፈሪዉ ሙስና ከፊታችን ነዉ!!!!
ምክንያቱም፡
- መንግስቱ ሲዳከም እና ግጭቱ ሲባባስ ዘረፋው ይጨምራል (በጣም!) Corruption will intensify as the regime disintegrates;
- በኢትዮጵያ ሙስና ብሄራዊ ባህል ሆኗል፣ ሥርቆትንና ሸጥን በሚያስፈራና በሚዘገንን መልኩ እንደ ብልጠተኝነት እንዲቆጠሩ አድርጓል።
ለ) ሙስናው በፖለቲካውና በኤኮኖሚው ላይ ያደረሳቸው አባዜዎች፡
በየትም ሀገር ታይቶ በማይታወቅ መልክ የፓርቲ ኩባንያዎችና ዖሊጋርኪ እንዲፈጠሩ አድርጓል። የኢትዮጵያ የእስትራቴጂያዊ የኤኮኖሚ አውታሮች በሶሥት ኦሊጋርኪዎች ቁጥጥር ስር ሆኗል። እነሱም፡
- ኢፎርት (በዋናነት) እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች፤፡
- በወያኔ ጀኔራሎች የሚመራውየብረታ ብረት ኮርፖሬሽንእና፤
- የሸህ መሃመድ አላሙዲ ሚድሮክ ኮርፖሬሽን ናቸው።
እነዚህም ድርጅቶች፤
ሀ. ለሙስናው ሥር መስደድና መስፋፋት ምክናያት ሆነዋል። በዚህ ተግባር ላይ ቀዳሚ ሚናውን እየተጫወቱ ያሉት ኢፈርትና የበረታ-ብረት ኮርፖሬሽን ናቸው። በወያኔ ጀኔራሎች የሚመራው የብረታ-ብረት ኮርፖሬሽን ከፀረ-ሙስና ምርመራ ነፃ እንዲሆን፤ ፓርላማው ሕግ ማውጣቱ ነው! ይህ ድርጅት በከፍተኛ ሙስና ከመዘፈቁም በላይ፤ የአገሪቱ ኤኮኖሚ እንዳያድግ ጠፍሮ ይዟል።
ለ. የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በሞኖፖሊ በመቆጣጠርና ከመንግሥት መሪዎች ጋር በመተባበር የግል ባለሀብቶች እንዲደጫጩ በማድረግ ኤኮኖሚውን ተፎካካሪነት (ተወዳዳሪነት) አልባ እንድሆን አድርገዋል፤
ሐ. የሀግሪቱ ኤኮኖሚ እንዲሽመደመድም ምክንያት ሆነዋል።
በኢትዮጵያ ላይ የተዘራፋው ሙስና፡
ሀ. የሀብት ወደውጭ አገር ማሸሽ እንዲስፋፋ አድርጓል (Illicit financial flows). አሁን ያለው አለመረጋጋትና ሕዝባዊ አመፅ የሀብ ማሸሹ ከመቸውም በበለጠ እንደሚስፋፋ ጥርጥር የለውም now and then; more so now than in the past!
ለ. በድሃውና በሀብታሙ መካከል ያለውን የህብት ልዩነት በጣም ለጥጦታል። ቅራኔውንም እንዲሁ አካሮታል።
ሐ. መንግሥት “ልማታዊ መንግሰት ነኝ”፤ “ልማታዊ ዴሞክራሲየሀግራችን ፈውስ ነው” ኒዮ-ሊበራሊም ለኢትዮጵያ አያዋጣም” … ወ.ዘ.ተ. እያለ እነዚህን መፍክሮች የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማጭበርበርና ለማማለል ያወጣቸው ቢሆኑም፤ እንዚሁኑ መፈክሮችን ደጋግሞ ሲናጋር ሀይማኖቱ ሆነውበት የየጭንብል ፈተናው ሆነዋል። (ከአመታት በፊት የኢትዮጵያ የአለም ባንክ ተወካይ የነበሩት ኬን ኦሃሺ ይህንን ችግር አስጨብጠው ነበር)።
ለማንኛውም ግን፤ የሙስናው ንቅዘትና ጭቆናው፤ አይን ያወጣ የአድሎ ሥርዓቱ ተጨምሮበት ወያኔ ከሕዝብ ጋር እንዲጋጭ አድርጎታል። ሕዝቡም እምቢ አልገዛም፤ “ወያኔ ሌባ ነህ” እያለው ነው መፈክሩን የሚያሰማው። እነዘህ መፈክሮች የሕዝባዊ አመፁ አንዱ መንስኤ የሙስና ንቅዘት መሆኑም ያመክታሉ።
ሐ) ሕዝባዊ አመፁ የሚከተሉትን አባዜዎች አስከትሏል (ባጭሩ)፤
- “ለደህንነትና” ለፀጥታ ጥበቃ ብዙ ገንዘብ መንግስት እንዲያፈስ አስደርጓል። ለምሳሌ፤ (1) በርካታ ሰላዮችን እንዲቀጥር አድርጎታል፡ (2) ካድሬውን ለማባብል ሲል ለካድሬውች የሚከፈለው ገንዘብ እንድንር እያስደረገው ነው፤
- የወታደራዊ ወጭውን በጣም እያናረው ነው፤
- የሥራ ማቆምና የኤኮኖሚ እቀባው የመንግሥትን የገቢ ግብርበመቀነስ የመንግስቱን አውታር በገንዘብ እጥረት እያስራበው ነው፤
- በከፍተኛበግሽበት አዙሪት (Inflationary cycle) ተዘፍቃ የነበርችውን ኢትዮጵያን ይህ አዙሪት እንዲባባስ ማድርጉ አይቀርም፤ ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ያለውን ቅሬታም ያባብሳል።
- ብጥብጡና አመፁ በርካታ ኢኮኖሚያዊ አውታሮች እንዲወድሙ አድርጓል፤
- የከተማ መሬትን ዝርፊያው በጣም እንዲቀንስ አድርጎታል። ይህ ከቀጠለ መሬትን በመዝረፍ የሚባበለው/የሚማለለው እናልቦናውን የሸጠው ካድሬ ማክረፉ አይቀርም!
- የመሬት ቅርምቱን (ወረራውን) ቀንሶታል፤በከፊል እንዲገታ አድርጓል፤ ይህም የምንግሥቱን ገቢ እየቀነሰው ይገኛል።
- የሀገሪቱ የውጭ ንግድ በእርሻ ምርቶች ላይ ያተኮረ ስለሆነ፤ ከውጭ የሚገኘውን የመንግሥት ገቢ የበለጠ እንዲዳከም፤ እንዲንኮታኮት እያደርገው ይገኛል፤ በፊት የነበሩትን ችግሮች እንዲባባሱ አድርጓል (ለምሳሌ አገሪቱን ጠፍረው የያዟት የሎጂስቲክና የትራንስፖርፖርቴሽን ችግሮች)፡
መረጃ፡ [የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ ነው። የኤክስፖርት ምርቱ በከፍተኛ ደረጃ ወርዷል። ሀገሪቱ የውጭ ብድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። በመጀመሪው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የታቀዱት እቅዶች በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን የእቅድ ዘመን እንኳን የሚሳኩ አይመስሉም። በውጭ አገር ንግድ የገቢና የወጪው ክፍተት በከፍተኛ ደረጃ እያባባሰው ነው። የሰደቅ ጋዜጣ ዘጋቢ ፀጋው መላኩ እንዳቀረቡት፡ “የ2007 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኤክስፖርት መጠን 4 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ይህ የኤክስፖርት መጠን ከዓመት ወደ ዓመት የመሻሻልና እድገት ማሳየት ቢጠበቅበትም በሳለፍነው 2008 በጀት አጠቃላይ የኤክስፖርቱ መጠን ወደ 2 ነጥብ 856 አሽቆልቁሏል። በ2008 በጀት ዓመት ከኤክስፖርት ለማግኘት ታቅዶ የነበረው የውጭ ምንዛሪ መጠን 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ሆኖም ከተያዘው እቅድ አንፃር የተገኘው የገቢ መጠን በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ብሎ ታይቷል። ይህም ከቀደመው በጀት ዓመት የ2008 የኤክስፖርት መጠን አንፃር በ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉን ያሳያል። የኢትዮጵያ የኤክስፖርት አፈፃፀም በጀት ዓመት መጨረሻ 2 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ለፓርላማ የቀረበው የመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያመለክታል። ይህ ገቢ መጠን የዛሬ ስድስት ዓመቱን ሪፖርት ያመለክታል። ከስድስት ዓመታት በኋላ በ2008 በጀት ዓመት ከተመዘገበው የ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር አንፃር ሲታይ የኤክስፖርት ገቢ የእድገት ልዩነቱ የዜሮ ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር ብቻ ሆኖ ይታያል። የሀገሪቱ የኤክስፖርት እድገት በተገቢውና በተፈለገው መጠን ማደግ ይቅርና የመቀነስ ሁኔታን እያሳየ ባለበት ሁኔታ የኢምፖርት ፍላጎቱና እድገቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር ላይ ነው። ይህም የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን ክፍተት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሰፋው ይገኛል። ይኸው ለፓርላማ የቀረበው ሪፖርት “ኢኮኖሚያችን በፍጥነት እያደገ ባለበት በኤክስፖርትና በኢምፖርት መካከል ክፍተት መኖሩ የሚጠበቅ ቢሆንም ጉድለቱ እየሰፋ መጥቶ የተጠቀሰው ደረጃ ላይ መድረሱን ግን አሳሳቢ ያደርገዋል” በማለት የገለፀ ሲሆን፤ ሪፖርቱ አያይዞም “የኤክስፖርት አፈፃፀም አስተማማኝ የውጭ ምንዛሪ ግኝት በማረጋገጥ ለፈጣን እድገታችን አስፈላጊ የሆኑ መሳሪያዎችና ዕቃዎች ከውጪ በማስገባት ዕድገታችን ለማስቀጠል እና ከውጭ ብድርና ዕርዳታ ጥገኝነት ለመላቀቅ ትልቅ ማነቆ ሆኗል” በማለት የችግሩን አሳሳቢነት ያብራራል። ሀገሪቱ የውጭ ሸቀጥን ማስገባት የምትችለው በኤክስፖርት ገበያ በምታገኘው ገቢ ደረጃ ነው።”]
- መንግስት ትኩረቱን ወደ ጸጥታ ጥበቃ እንዳያዙርና ኤኮኖሚውን ዘርፍ እንዲረሳ አድርጎታል፤
- ባጠቃላይ፤ የኤኮኖሚ እንቅስቃሴውን በጣም አዳክሞታል፤ የኢኮኖሚ እድገት እንዲንሸራተት እያደርገው ነው።የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ “እደገ ተመነደገ” እያለ መኮፈሱን (በዉሸት የተሞላልውን ኳስ) እንድተነፍስ አድርጎታል/እያደረገው ነው፤
- ብዙ የመንግሥት ተቋማት እንዳይንቀሳቀሱ እያደረገ ነው (ጀኔራል ፃድቃን በቅርቡ ባሰራጩት በጽሁፋቸው እንዳመለከቱት)፤
- ሀገሪቱም ሆነ መንግሥት የብድር እደኝነት እንዲሰፋ እያደረገው ነው።
ተጨማሪ ችግሮችን አንርሳ!
ሀ. ድርቁ ያመጣው ጣጣ፡ባለፈው በጀት ዓመትም 10 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎችን ለከፋ የምግብ እህል ውሃ እጥረት ዳርጓል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ለተረጂ ዜጎች እህልን ለማቅረብ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር አስፈልጓል።ባለፈው በጀት ዓመትም 10 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎችን ለከፋ የምግብ እህል ውሃ እጥረት ዳርጓል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ለተረጂ ዜጎች እህልን ለማቅረብ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር አስፈልጓል። መንግስት ይህንን ያህል ገንዘብ ወጪ በማድረግ ለዜጎች የምግብ እህል ለማቅረብ አቅሙ እንደሌለው በመግለፅ ለለጋሽ አካላት የእርዳታ ጥያቄን ቢያቀርብም የተገኘው ምለሽ ግን የታሰበውንና የተጠየቀውን ያህል አመርቂ አልነበረም።
ለ. የሕዝብ ብዛት፤የህዝቡ ቁጥር በ25 ዓመታት ውስጥ ከሁለት እጥፍ በላይ አድጓል።
ሐ. የትምህርት ጥራት ያመጣው ጣጣና ከዚህም ጋር የተፈጠሩት አባዜዎች፤
- ምርታማነት አለመሆን፤
- የዲፕሎማ ምርት ቁለላውን አስታኮ የተከሰተው ሥራ አጥነትና የተሻለ ሥራ ፍላጎት ያለማግኘት፤ በወጣቱና በመግሥት መካከል ያለውን ቅራኔ ማባባሱ፤
መ. ስደተኝነቱ ኢትዮጵያን አዕምሮዋ እንዲደማ አድርጓል። በመከከለኛው ምስራቅ በተነሳው የሕዝብ ፍሰት
(1) የአውሮፓንና የሰሜም አሜሪካን የፖለቲካ በስደተኛው ላይ ያለውን እይታ በመቀየሩ፤
(2) የነዳጅ ዋጋ መንኮታኮት እና ሥራ የማግኘቱ ችግር፤ የሠራተኞች መባረር፤
(3) ስደተኛው ላይ የባሕር አሣ ምግብ መሆኑ የበለጠ በጋዜጠኞች በሰፊው መዘገቡ፤
(4) በስደት ላይ ባሉ ወጣቶች ላይ የሚደርሰው ሞት በሰፊው እየተዘገበ በመሆኑ፤ የኢትዮጵያው ወጣት ስደት እንደማያዋጣ በከፊልም ቢሆን እያሳየው ይገኛል። ለሕይወቱ እና ለኑሮው እዚያው ሀገሩ መፍትሄ እንዲፈልግ እያስገደደው ይገኛል።
ከላይ የጠቀስኳቸው ክስተቶች ወያኔ ሰውን እንደ እቃ እየሼጠ የሚያገኘውን እንዲቀንሱበት ምክንያት ሆነዋል። እንዚህ ክስተቶችና ችግሮች ወደፊትም ይቀጥላሉ።!
ሠ. የንግድ ክስረቱ ከመቸውም በከፋ ሁኔታ ላይ መሆኑ፤ Shortage of foreign exchange; የውጭ ምንዛሪ እጥረትና ንግዱ አንዱ የችግር ምንጭ ሙስና እና ኪራይ ሰብሳቢነት ነው። የሀገር ቤት ጋዜጦች እንደዘገቡትም፤ የ2007 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኤክስፖርት መጠን 4 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ይህ የኤክስፖርት መጠን ከዓመት ወደ ዓመት የመሻሻልና እድገት ማሳየት ቢጠበቅበትም በሳለፍነው 2008 በጀት አጠቃላይ የኤክስፖርቱ መጠን ወደ 2 ነጥብ 856 አሽቆልቁሏል። በ2008 በጀት ዓመት ከኤክስፖርት ለማግኘት ታቅዶ የነበረው የውጭ ምንዛሪ መጠን 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ነበር። ሆኖም ከተያዘው እቅድ አንፃር የተገኘው የገቢ መጠን በ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ብሎ ታይቷል። ይህም ከቀደመው በጀት ዓመት የ2008 የኤክስፖርት መጠን አንፃር በ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ማሽቆልቆሉን ያሳያል።
ረ. መሬት አሁንም ላራሹ ባለመሆኑ የተነሳ እየተወሳሰቡ የመጡት የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካን ማሕበረሰባዊ ችግሮች።
የኛ አስተዋፅዖውች፤ ከኛ ምን ይጠበቃል?
ሀ. ጩኸቶቻችንን በተቀናጃና በመተባበር ሳናቋርጥ መቀጠል፡ ይህ ካልተቻለም አለመጠላለፍ፤
ለ. በመግሥቱና በተባባሪዎቹ ላይ የኤኮኖሚ እቀባ ማድርግና ድርጊቱን ማስፋፋት፤
ሐ. ኢትዮጵያ የከተማ መሬት ባመግዛትና በንግድ ባለመሳተፍ የሙስናው ተካፋይ እና ተባባሪ መሆናችንን ማቆም፤
መ. ወደ ኢትዮጵያ የምናደርገውን የሽርሽር ጉዞ ጨርሶ ማቆም። አላስፈላጊ ጉዞ በሚያደርጉት ላይ ተፅእኖ ማድረግ፤ ማሳፈር/ማሸማቀቅ!
ሠ. የውጭ መንግሥታት እርዳታ እንዲቆም ተጽእኖ ማድረግ። በስልጣን ላይ ያለው መግንሥት ሌባም፤ ለማኝም ነው; ከዲያስፖራ የሚአገኘውን ገንዘብ ማድረቅ ባንችልም፤ በጣም እንዲቀነስ ማድረግ እንችላለን! በተለይ በልመና የሚያገኘውን ማድረቅ ይቻላል። እነዚህ ቅነሳዎችም እየታዩ ነው! ወያኔ ሌባም፤ ለማኝም ነው። ከፍተኛ ወጭውን የሚሸፍንለት የውጭ እርዳታ ነው። ይህንን አጥብቀን እንወቅ! በልመና የሚአገኘው የገንዘብ በጣም ከቀነሰ ወያኔ ባጭር ጊዜ እንኮታኮታል! ኸውጭ የሚአገኛቸው እርዳታዎች እየቀነሱ እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶችም እየታዩ ነው!
ትብብራችን እና ጩኸታችን የውጭ ኢንቨስተሮች ከኢትዮጵያ እንዲሸሹ/እንዲበረግጉ ማድረግ ያስችለናል። መበርገግም ጀምረዋል!
ረ. ለህሊና እስረኞችና ለተጎዱ ቤተሰቦች እርዳታን ማድረግና እስካሁን እይተደረጉ የነበሩትን እርዳታዎች በሰፊው ማስቀጠል (መተግበር)።
የወያኔ መንግሥት የመውደቂያው ጊዜ በጣም እየቀረበ ነው። ከሁን በኋላ የወያኔ መንግስት ያ የምናውቀው መንግሥት አይደለም! መውደቂያው እንድፋጣንና እንዲምር እንተባበር! ሁላችንም የምንችለውን በማድረግ!
ስላዳመጣችሁኝ አመሰግናለሁ።
አላህ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
Leave a Reply