• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጌቶች እና ሌሎች

November 20, 2015 02:50 am by Editor Leave a Comment

ባገራችን አብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ አማርጠው ይበላሉ፡፡ አማርጠው ይለብሳሉ፤ በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ አምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ጌቶች ያስንቀናል ብለው የሚያስቡትን ነገር በሙሉ ጠምድው ይይዙታል፡፡ ይዋጉታል፡፡ ኢትዮጵያ፡- ጌቶች ለኩራታቸው፤ ዜጎች ለራታቸው የሚታገሉባት መድረክ ናት፡፡

ብዙ ጊዜ ረሀብ ሲከሰት ጌቶች ራብተኛውን ሁሉ ሰብስበው ጎተራ ውስጥ ሊደብቁት ይቃጣቸዋል፡፡ የድሆች የተራቆተ ሰውነት የገጠጠ አጥንት፤ የጌቶችን የመከበር ፍላጎት ያከሽፈዋል፡፡

ባንድ ወቅት በቦሌ መዳኒያለም ዳርቻ ስራመድ አካባቢው አለወትሮው በለማኞች አለመሞላቱን ታዝቤ ተገረምሁ፡፡ ያዲሳባ አስተዳደር ፤ ለማኞችን “በጥቃቅንና አነስተኛ” አደራጅቶ ያሳለፈላቸው መስሎኝ ነበር፡፡ እንደተሳሳትሁ ለመረዳት ጥቂት ደቂቃ በቦታው መቆም ነበረብኝ፡፡ አንዲት ተመጽዋች ሴት ልጇን ይዛ ከቅጽሩ ስር ለመቀመጥ ስታነጥፍ ፖሊስ በቆረጣ ገብቶ “ዞር በይ ነግሬሻለሁ” እያለ ሲያዋክባት ተመለከትሁ፡፡ የደነገጠ ልጇን እየጎተተች ተወገደች፡፡

ከዚያ ወዲያ ከአቡነ ጳውሎስ ሃውልት በቀር ባካባቢው ደፍሮ የቆመ አልነበረም፡፡ ወደ ቤቴ ከመሄዴ በፊት ያቡኑን ወፍራም ሀውልት ዞር ብየ ሾፍኩት፡፡ እጁን እንደ ራሱ ሀይሉ ሙርጥ ገትሮ ከፊትለፊት ያለውን “ሬድዋን ህንጻ” ሲባርክ ነበር፡፡

“ገጽታ ግንባታ?”

በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን የፍርድ ሚኒስተር የነበሩት አፈንጉስ ነሲቡ የሌባ ብዛት ቢያስቸግራቸው አንድ መላ መቱ፡፡ ሲሰርቅ የተገኘ ወሮበላ ግንባሩ ላይ በጋለ ስለት ምልክት እንዲደረግበት ደነገጉ፡፡ ታድያ ሌቦች የዋዛ ስላልነበሩ ሻሽ በመጠምጠም የግንባራቸውን ጠባሳ ሊሰውሩት ሞክረዋል፡፡ በጊዜው ደግሞ ሻሽ መጠምጠም ካክሱም ዘመነ መንግስት ጀምሮ የወረደ የነገስታቱና የመሳፍንቱ ወግ ነበር፡፡ ጮሌ ሌቦች ውርደታቸውን ከመሸፈን አልፈው የንጉስ ገጽታ ተላብሰው ብቅ አሉ፡፡

በዘመናችን የተራቡ ዜጎችን መደበቅ እንደ ገጽታ ግንባታ የሚቆጥሩ ሰዎችን ከባለሻሽ ሌቦች ለይቼ አላያቸውም፡፡

በነገራችን ላይ፤ ብርቱካን አሊ ግለሂስ ያደረገችበትን ዘገባ ካየሁ በኋላ ለጊዜው ለመናደድ እንኳ ቸግሮኝ ነበር፡፡ ዘገባውን የሠራው ጋዜጠኛ እንዲህ አይነቱን ካንድ ድንጋይ የተጠረበ ደደብነት ተሸክሞ የመኖር ችሎታው በጣም አስደነቀኝ፡፡ በዚህ በሰላቢው ቀን ይቅርና፤ በደህናው ቀን እንኳ የባላገሩን ራብና መከራ ከጉያው የበቀልን ልጆቹ እናውቀዋለን፡፡ አስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል፡፡ መፍትሄው በተቸገሩ ሰዎች ጫማ ቆሞ ነገሮችን መመልከት ነው፡፡ ለነገሩ ችግርን ያልቀመሰ ሰው ለችግረኛ መራራት እንዴት ይቻለዋል?

አብን ተውትና፤ ንገሩት ለወልድ

ተገርፏል ተሰቅሏል፤ እሱ ያውቃል ፍርድ

እንዲል ባላገር፡፡

በእውቀቱ ስዩም


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
Copyright © 2026 · Goolgule