ይኸ መጣጥፍ መጀመሪያ የተጻፈውና በኢትዮመዲያ፣ በኢካዲኤፍ፣ በአዲስ ቮይስ፣ በኢኤምኤፍ እና በጎልጕል ድረ-ገጾች የተበተነው በእንግሊዝኛ ተደርሶ ነበር። በጣም ብዙ አስተያየት ሰጪዎች፣ በዩኒቨርሲቲዬም ኢ-ሜይል ሳይቀር የተሰማቸውን አካፍለውኛል። ሁሉም ወደ አማርኛ እንደመልሰውና ብዙ ኢትዮጵያውያን ለማንበብ ዕድል እንዲያገኙ አጥብቀው ስለአሳሰቡኝ ጥይቄአቸውን ተቀብዬ ወደ አማርኛ መለስኩት።
ከኢትዮጵያ የሚደርሱን ቀልዶች ለዛቸው ጨምሯል። ሰሞኑን፣ አንድ ከአገር ቤት የመጣ እንግዳ፣ የወያኔ ባለሥልጣናት፣ ዲያስፖራን “ላሜ ቦራ” እያሉ እንደሚሾፉብን አጫውቶን አዝናንቶናል። እውን እኛ በተለያዩ ምክንያቶች ከኢትዮጵያ የተሰደድን ኢትዮጵያውያን ያለማቋረጥ የምንታለብ የካሽ ጥገቶች ነን?
መቼም በኔ ዕድሜ ትምህርት ቤት የሄዳችሁ ሁሉ፣ስለላሜ ቦራ የተተረከ የልጆች ጣፋጭም አሳዛኝም ታሪክ ሳታነቡ ወይም ሳይነበብላችሁ አልቀረም። የላሜ ቦራ ታሪክ እጅግ አንጀት የሚበላ ተረት ነው። ነገሩ እንዲህ ነው። አንዲት ሁለት ሕጻናት የነበሯት እናት በጣም አሟት በአልጋዋ ላይ ሁና ትጣጣራለች። እሷ ስትሞት ባሏ ሌላ ሚስት ካገባ፣ የእንጀራ እናት በልጆቿ ላይ ለታደርስ የምችለውን ጭካኔ ስትገምተው ከራሷ መሞት በላይ አስጨነቃት። ከዚህም የተነሳ፣ ሰው አላምን ብላ (ሰው ምን ይታመናል? ዛሬ እዚህ ብታስቀምጠው ነገ ሌላ ቦታ ተንሸራትቶ ታገኘዋለህ) የምትወዳትን ላሜ ቦራ የተባለችውን ላሟን አልጋዋ ድረስ አስመጣቻት። “ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የልጆቼን ነገር አደራ” ብላ አዜማ እንደ ጨረሰች ሞተች። ሟቿ እናት እንደገመተችውም፣ የልጆቹ አባት፣ ብዙም ሳይቆይ ሌላ ሚስት አገባ። እንጀራ እናቲቱ ሕጻናቱ የሷ ልጆች ባለመሆናቸው በጣም ጨከነችባቸው። በረሀብ መንምነው እንዲሞቱ፣ ምግብም ትከለክላቸው ገባች። ልጆቹ ሲርባቸው፣ በቀጥታ ወደላሚቱ እየሄዱ፣ “ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የእማምዬን አደራ” ብለው ሲያዜሙላት፣ ላሜ ቦራ እግሮቿን ፍረክረክ አድርጋ ከጦቶቿ በቀጥታ ወተት እንዲጠቡ ታደርግ ነበር። ቀሪው ታሪክ ገብስ ነው። የሚገርመው ነገር፣ ላሜ ቦራ ያለመንጥፏ ነው። ክረመቱንም በጋውንም ዓመቱን ሙሉ ብትታለብ፣ ብትታለብ የማትነጥፍ የወትት ጅረት ናት ተብሎ ነው የሚገመተው!
ወያኔዎች፣ በሚያስገርም አኩኋን ታርኩን ዲያፖራው ላይ ደገሙልን። ታዲያ ታሪኩ በዲያስፖራው (ውጭ አገር ኗሪውን ኢትዮጵያዊ) ላይ መሆኑ አያንገበግብም? ያርገበግባል ኢንጂ። “ዲያስፖራ – ላሜ ቦራ” አሉን? ዕውነት አላቸው። ምን ያድርጉ! “አረሱት! አረሱት! የመተማን መሬት! የአርማጨውን መሬት፣ ያውም የኛ ዕጣ፣ እነሱ ምን ያርጉ ከኝ ሰው ሲታጣ!” ብሎ ደምድሞት የለ ዘፋኙ! ወያኔዎች፣ የወጭ ምንዛሬ በደረቀባቸው ቁጥር ጨርቄን ማቄን ሳይሉ፣ ባዶ ሻንጣቸውን አንጠልጥለው ወደ ዲያስፖራ – “ካሽ ጥገት”፣ ከተር ነዋ! ከዚህ ቢታለብ-ቢታለብ ከማይነጥፈውን ጥገት ዲያስፖራ በተለያየ ምክኒያት ተሰዶ በብዛት ከሚኖርበት የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች፣ እንደለነድንና ዋሽንግተን ካሉት ከቸች ነዋ! ለዚህ እንዲመቻች ደግሞ፣ ከዚህ በፊት እንዴት ተደርጎ ዲያስፖራው ሊጠመድ እንደሚችል፣ 52 ገጾች[1] በፈጀ ምርምር ጥናትና ዕቅድ ተነድፎ የወያኔ ኤምባሲዎች ሥልጠና አግኝተዋል። ላሜ ቦራን እያጠመዱ ይዞ ድርቅ እስክትል ድረስ እልብ ነዋ! ቅርብ ጊዜ ከተፈጥሩት ወጥመዶች መሀል፣ “የሕዳሴ ደደብ” (ይቅርታ፣ “ግድብ” ማለት ፈልጌ አዳልጦኝ ነው) ቦምብ፣ ውይ በሞቴ -ቦንድ ሽያጭ ነው።
“አባይን ለደፈረ መንግስታችን ገንዘብ?” እንዴታ! ሌላው፣ የተለያዩ ለጥቅም የተደለሉ ላሜ ቦራዎችን እየሰበሰቡ፣ በየዘር ሀረጋቸው የሌማት – ይቅርታ ኦሆሆ ምን ነካኝ ዛሬ! – “ልማት” ማኅበር ማደራጀት ነው። ሌላው “ኢንበስተሮች” የሚል ሹመት ብጤ ስጥቶ፣ ላሜ ቦራዎቹ አድረገዋቸው አገር ቤት ንዋይ እንዲያፈሱ አግባብቶ ጠልፎ ማለብ ነው። ሰሞኑን ደግሞ ሌላ ያማረች አሽክላ ፈጥረው መጥተውልናል። 40/60 የሚሉት በአቋራጭ የቤት ማግኛ ፎርሙላ ወይም ቀመር ነው። አንድ ሎንደን ውስጥ ቤተክርስቲያናችንን ካዘጉት ካህናት መሀል፣ ሰሞኑን በዚያ ፎርሙላ ተጠቃሚ ለምሆን ሌሎቹን ጓደኞቹን አስከትሎ ሲሂድ፣ ጥግብ ያሉት የወያኔ እልፍኝ አስከልካዮች፣ “አንተ የላሜ ቦራን መስፈርት አታሟላም” ብለው ሲከለክሉት ሰድቦአቸው እንደሂደ ሰምተን ስንስቅ ነበር። አይ መሪጌታ! ቅኔውናንና ዜማውን እንደ ጅረት ስታወርድለት ወዶህ የነበረ አምላክ አዝኖልህ፣ እስክትደርቅ ከመታለብ አተረፈህ! ይልቁንስ ነዴቱን ትተህ “ሐሌ ሉያ” በል!
ወያኔዎችን የሚያዋጣቸው ፍቱን ዘዴ ሁኖ የተገኘው አንዳንድ ጅላጆሎችን በብሔር ብሔረሰባቸው አደራጅቶ የልማት ማኅበር ማቋቋም ነው፡፡ ዘረኝነት ደግሞ አንዴ ከተጠናወተ የማይለቅ ውርዴ ነው። በዚህ መንገድ፣ “የአማራ የልማት ማህበር፣”፣ “የኦሮሞ የልማት ማህበር፣” “የሲዳማ የልማት ማህበር” ወዘተ እያሉ መድበዋቸው ወይ ያልቧቸዋል፣ ወይ አሰልጥነው ሌሎቹን ላሜ ቦራዎች ያሳልቧቸዋል። ከየብሔረሰቡ የተገኙ ጥቂት ሆድ አደሮች ካልሆኑ በስተቀር፣ ተደጋግመው ማህበራቱን የሞሉት እነዚያው የፈረደባቸው ጥቂት የማይባሉ ከትግራይ የተገኙ “የወርቅ” ዝርያ አባሎች ናቸው። የአማራ በዓል ላይ እነሱ ናቸው “እስክስ” የሚሉት! የኦሮሞው በዓል ላይም እነዚህው ናቸው “ሆ!” የሚሉት! የትግሬም በዓል ላይ እነሱው ናቸው “አጅዋ!” የሚሉት።
በዚህ ወር ላሜ ቦራን የማለቡ ተራ፣ ወያኔ ኤምባሲ ግቢ ተወልዶ ፍርፋሪ እየበላ ያደገው “የአማራ የልማት ማህበር” ነው። “በአማራው ማኅበር” ሥር የተደራጁት ዕውነተኛ አማሮች ሳይሆኑ በሙሉ ቁጭአማሮች ናቸው። የዘር ሐረጋቸውን እንደውያኔዎች ከቆጠርን፣ አማራ ሳይሆኑ የአማሩ ማለት ነው። እርግጥ አንዳንድ እንደያለው ከበደ ያሉ ወዶ ገቡች አይጠፉም። እነዚህ ማህበራት “የልማት” (የ”ጥፋት” ማህበራት ማላቱ ይቀላል፟)፣ ለማወናበድ እንዲመች ስማቸው ተቀየረ እንጂ፣ ወያኔ ለየአንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ በአገር ቤት ለለጠፋላቸው ዋና ዋናዎቹ የወያኔ አገልጋይ ተለጣፊ የፖሊቲካ ድርጅቶች “የድጋፍ ኮሚቴዎች” ናቸው። እንደ ኦሕዴድ፣ ብአዴን … ምናምኖች ማለቴ ነው።
እስቲ ከነዚህ በዘር ከተደራጁት አንዱን የአማራን ብሔረሰብ እንዲቀብርላቸው የፈጥሩትን ተለጣፊ የአማራ ድርግጅት ቀርብ ብለን እንይ! ይኸምውም “የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (ብአዴን) ነው። ለአማራው ሕዝብ ለመቀጥቀጥ የተጠፈጠፈለት መዶሻ ነው። (አንጽሮዕተ ስሙ ሲደብር!) ይኸን ድርጅት ወያኔዎች ጠፍጠፈው የሠሩት፣ በትቅምት ወር ፲፱፻፸፪ ዓ› ም› (Nov. 1980) ኢሕአፓን በድንገት ደርሰውበት አባላቱን ከጨፈጨፏቸው በኋላ፣ ከሞት ካተረፏቸው ምርኮች ሰብስበው “ተክራርዉሀ” በተባለ ስፍራ ነበር። ድርጅቱም የኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ (ኢሕድን) ነበር። ዕውነትም፣ በጊዜው ኢሕአፓ አባላቱ ዘር ቆጥረው የተደራጁ ሳይሆኑ ከሁሉም ብሔረሶቦች የተወጣጡ ነበርና ምርኮኞች ቢሆኑም ስሙ ትክክለኛ ነበር። ወያኔ ግን “ኢትዮጵያ” የሚለውን ስም መስማት ስለማይፈልግ፣ በዘዴ “ብሔር አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ” (ብአዴን) ብሎ እንደገና አጠመቀው። አርማም ቀርጾ ሰጠው። ታዲያ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ አመራሩን የያዙት ቁጩ አማሮች እንጂ አማራ በመብራትም ቢፈልግ አመራሩ ውስጥ አይገኝም።
በመጀመሪያ ረድፍ የሚገኘው ቁጩ አማራ፣ አማራን በጣም የሚጠላ፣ አማርኛን መናገር የሚጠይፍ፣ ሻቦ ባንዳ፣ እናቱም አባቱም ከኤርትራ የፈለቁ፣ ጎንደር የተወለደ “በረከት ስምዖን”፣ ሕወነተኛ ስሙ ግን መብራቱ ገብረሕይወት የተባለው ነፍሰ ገዳይ ነው። ሒላዊ (ዕውነተኝ ስሙ “ፍቅሬ”) ዮሴፍ ወይ የእርትራ፣ አለበለዚያም የትግራይ ትግሬ እንጂ፣ አንዲት ጠብታ ደም በደም-ሥሩ ውስጥ የማትዘዋወር ቁጩ አማራ ነው። ታደሰ ጥንቅሹ (ዕውነተኛ ስሙ ታደስ ካሳ) ስሙን ቢያምር እንጂ፣ የትግራይ ትግሬ በመሆኑ፣ አማራነቱ በዲ ኤን ኤ ኤክስፐርትም ቢመረመር አይገኝበትም። ተፈራ ዋልዋ፣ ጊሚራ ነው። አማራና ጊሚራ ድምጹ ለጆሮ ቢመሳሰል እንጂ፣ አምሮም አያውቅም። ተፈራ ዋልዋ አማራ ነው የሚለኝ ሰው ካለ እራሱን የስነ አዕምሮ ሐኪም ጋ ሂዶ ይመርምር። ያስ ደግሞ፣ በአማራነት ሲያጭበረብረን የኖረ ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ? ስማቸውን እየቀየሩ እኮ ነው የሚያምታቱን። ለመሆኑ ጌታቸው ማሞ ዋቅኬኔ መሆኑን ስንታችሁ ናችሁ የምታውቁት? ስለዋኬኔ አማራነት እናንተው መርምራችሁ ድረሱበት።
አዲሱ ለገሰ፣ ሰሙ ነው እንጂ አማራ፣ የሐረር ቆቱ ነው። አያሌው ጎበዜስ ቢሆን አማራ ነው? በአማራና በአገው መሀል ብዙም ልዩነት ባይታይም፣ ለሥልጣን የበቃው በአማራነቱ ሳይሆን ነገሩ ሌላ ነው። ቁጩ አማሮች በመሆናቸው አይደል፣ የአማራው መሬት ከጎንደር ተነጥቆ ለትግራይ፣ ከወሎ ተቆርጦ ለትግራይ ሲሰጥ፣ ጭጭ ብለው የተቀበሉት! እሱስ ይሁን ትግራይ የኛ ናት! የአማራው መሬት ተቦድሶ ለሱዳን ሲሰጥ የማያማቸው ቁጩ አማሮች በመሆናቸው አይደል! ቁጩ አማሮች ቢሆኑም አይደል፣ የዋልድባ መነኩሳት ሲደበደቡ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የተቀመጡት። ቁጩ አማሮች ቢሆኑ አይደል፣ አማሮች ከየክልሉ ቁምጥና እንደያዘው ከቄዬአቸው ተፈንቅለው ሲባረሩ፣ ከየክፍለ ዞኖች ከቤታቸው ተመንግለው ሲሰደዱ የማያማቸው? ቁጩ አምሮች በመሆናቸው እኮ ነው፣ የወያኔ መሠሪዎች አማሮች እንዳይወልዱ በኪኒን ስያመክኗቸው በዓይናቸው ብሌን እያዩ ትንፍሽ የማይሉት። ውጪ አገር በአማራ ልማት መልክ የተደራጁትም እንግዲህ የዚያው መልክ የተጠፈጠፉ ተቀጥሎች ናቸው! ሌሎችም ብሔረሰቦችን እነወክላለን የሚሉት፣ ቁጩ ኦሮሞዎች፣ ቁጩ ጉራጌዎች … በዚህ አኳኋን ነው የተፈጠሩት።
ወደ ላሜ ቦራችን ስንመለስ፣ ላሜ ቦራዎችን ለማለብ የተደራጁት፣ “የአማራ ልማት ማህበር – ዩኬ” (“Amhara’ Development Association – UK”) የተብለው ነው። እነማን እንደሆኑ ለማወቅ፣ ከፈለጋችሁ፣ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር 2011 የገነዘብ ማሰባሰቢያ በዓላቸውን ሲያከብሩ የተቀዱትን ፊልም አብረን እንይ። http://www.youtube.com/watch?v=8fmeHCLPgpU።
መቼም ለንደን የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እዚያ ፊልሙ ላይ ከሚታዩት ማን ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ። ከተሳሳትኩ አርሙኝ። እንደ አለማየሁ (አሌክስ) ብርሀኑ ያሉ የለየላቸው ትግሬዎች ናቸው። አለበለዚያ ጃማይካኖች ናቸው (ጀማይካኖቹ ቁጩ አማሮ ሲሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ ነው)፣ እንግዲህ በጣት የሚቆጠሩ የሌሎች ብሔርሰቦች (ሞቅዲሾ ሶማሌዎች ሳይቀሩ) አባላትና ሆዳደር አማሮች ሊታዩ ይችላሉ። የለየለት ሆድ አደር አማራ፣ ያለው ከበደ በር ጠባቂ በመሆኑ አታዩትም። ታዲያ ያ ሆዱ የተቀፈደደው፣ እንግዶቹ በልተው፣ ጠጥተው ጠግበው ሲሄዱ ቀሪውን ፍርፋሪ እየበላ መሆን አለበት።
በዚህ ዓመት ሎንደን ውስጥ፣ ዲያስፖራ ላሜ ቦራን ለማለብ የታቀደው 28 September 2013 ነው። መግቢያው በነጻ ነው። ሁላችንም ተጋብዘናል። ምግብ መጠጥም በሽበሽ ነው። ለምን ሁላችንም ግልብጥ ብለን ሂደን አንጋበዝላቸውም? ታዲያ ኪሳችሁንና ሆዳችሁን ባዶ አድርጋችሁ ነው መሄድ! በመተት እንዳትታለቡ! ሌላ የረሳሁት! የቁጩ አማሮችን የገንዘብ ማሰባሰቢያ በዓል ማን እንዳስተዋውቅላቸው ታውቃላችሁ? http://www.tigraionline.com/’Amhara’-ada-event-uk.html! ሌሎችማ ድረ-ገጾች ምን ቁርጥ ቢያደርጋቸው ነው የቁጩ አማሮችን ዝግጅት የሚያስተዋውቁላቸው!
ቁጩ አማሮች መቼም ሕሊና የምትባል አልተፈጠረችባቸውም። ወያኔዎች የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሲደርቅባቸው ነው የሚፍልጓቸው። ቢሞቱ ይሻላቸዋል። የላሜ ቦራ አላቢዎች ናቸው። ቁጩ አምሮች ካልረዷቸው በስተቀር፣ የወያኔ አምባሳደሮችማ ሥራቸውን መሥራት አቅቶአቸው፣ ሰሞኑን ከየኤምባሲው እየተባረሩ ነው። ኢትዮጵያዊው በየከተማው ውርደት እያከናነባቸው፣ ባዶ ኮሮጆአቸውን እያሸከማቸው ወደመጡበት ስለመለሳቸው፣ ያላቸው ምርጫ፣ ቁጩ አማሮችን የሙጥኝ ይዘው ወራዳ ሥራቸውን እንደሠሩላቸው ማሠማራት ነው። ውሻ በር በድንብ እንዲጠብቅ ከተፈለገ፣ በየጊዜው ልፋጭ ይወረወርለታል።
አሁን በጥሩ ሁኔታ ወያኔዎች ላሜ ቦራን ለማለብ የፈበረኩት ዘዴ፣ ይኸ 40/60 የተባለው ቀመር ነው። ፎርሙላው የሚሠራው፣ እንዲህ ነው። ታላቢው ላሜ ቦራ ዲያስፖራ 40 ከመቶውን በውጭ ምንዛሪ ይከፍላል። 60 በመቶውን ወያኔ በብድር መልክ ይሸፍል። 100% በዶላር፣ በዩሮ፣ በፓወንድ (ሀርድ ከረንሲ) ለሚከፍል ቅድሚያ ይሰጣል። ለዚህ ተብሎ የተሠሩ ቤቶች አሉና፣ ዲያስፖራ ሆዬ በቀጥታ አዲስ አበባ ሂዶ መረከብ ነው ተብሎ ተሰብኳል። ለዚያ የሚጣደፉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሞልተዋል። ምነው ቢባሉ፣ “እንዴ ለወያኔ ብቻ ማን አጋሪቱን ሰጣቸው፣ እኛም እመሀላቸው ገብተን ቦርቡረን ከውስጥ ገዝግዘን እንጣላቸው” የሚሉ ወንድሞች አጋጥመውኛል።
ወያኔ ከግምታችን በላይ ተንኰለኛ ነው። አባላቱ ሲፈጠሩ እኮ ተንኰልን ከሆድ ተምረው ነው የሚወጡት። እነሱ ዕቅዳቸው ላሜ ቦራን አስጠግተው፣ ሙልጭ አድርገው በደርቁ ሊያልቡ እንጂ ሊታለቡ እንዳልሁነ ማወቅ ይኖርብናል። ሌባን ደህና ሰው ሊሰርቀው፣ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። ቤት አዲስ አበባ ይኖረኛል ብሎ ወያኔን መጠጋት፣ አንደኛ፣ አድራሻ ለመስጠት፣ ከዚያም ወያኔን ለመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ላለመውጣት፣ ከዚያም አሻራ ሰጥቶ የወያኔ ንብረት ለመሆን ነው። ወያኔ አልቦህ ሲጨርስ፣ እንደማስቲካ መጥቶ፣ “ኪራይ ሰብሳቢ” ብሎ ይተፋሀል። የኢትዮጵያ መሬት እንዳለ የወያኔ ንብረት መሆኑን ለአንዳችም ደቂቃ አንዳንስት። ወያኔ ሲፈልግ፣ “መሬቱ ለልማት ይፈለጋል፣ ሞርታርህንና ጡብህን ይዘህ ብትፍልግ አንጨቆረር ውረድ” ብሎ ያሾፋል። ነገሩ ከዚህ በፊት ስለደረሰ ነው እንዲህ የምላችሁ፣ ያጣ ወሬ ሁኖብኝ አይደለም። ሰዎች ሲሸወዱ አይቼ ነው። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽም አይክፋሽ ከመባል አምላክ ያድናችሁ።
ከወያኔ ጋራ ሕሊና ሳይሸጡ ቢዝነስ መሥራት አይቻልም። ሥርዓቱ የነቀዘ ሥርዓት ነው። በጥቅም ተስባችሁ ወደወያኔ ስትቀርቡ የሞቱትን እንኳን ባትስቡ፣ እስቲ እስር ቤት በግፍ የሚማቅቁትን እነ ርዕዮት ዓለሙን፣ አንዱዓለም አራጌን፣ እስክንድር ነጋን፣ ናትናኤል መኰንንን፣ ክንፈሚካኤል ደበበን፣ ዮሐንስ ተረፈን፣ ሻምበል የሺዋስ ይሁናለምን፣ አንዱዓለም አያሌውን፣ በአሥርት ሺህ የሚቆጠሩትን የኦሮሞ ብሔርሰብ አባል እስረኞችንና፣ የእስልምና ሀማኖት መሪዎችን ስቃይና እንግልት አስቡ። ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በመሆናቸው ጥቃታቸው ይሰማን።
ዲያስፖራ ስደተኛ ወንድሞቼና እህቶቼ! አታስፎግሩን (በአራዳ አማርኛ)! እሺ ለታሠሩት፣ ለሚንገላቱ የሚራራ አንጀት ባይኖራችሁ፣ ላማንም ደንታ እንኳን ባያኖራችሁ ለራሳችሁ አስቡ። ገንዘባችሁን እየወሰዳችሁ አታስረክቡ። ወያኔ አምጣ-አምጣ እንጂ ሕንካ-ሕንካ የሚል አማርኛ መዝገበ ቃላቱ (ድክሺነሪው) ውስጥ የለም። ሰዶ ማሳደድ ካላማራችሁ፣ ገንዘባችሁን ሌላ ቦታ ብታስቀምጡ ደህና ገቢ ይኖራችኋል። አለበለዚያም፣ እናንተው በገንዘባችሁ እንደፈለጋችሁ የፈለጋችሁን ግዙበት፣ ብሉበት፣ ጠጡብት፣ ልበሱበት። ላሜ ቦራ መባል ይቅርባችሁ። ዛሬ አንዳንድ ላሜ ቦራዎች እንኳን ነቅተው የራሳቸውን ወተት ለራሳቸው መጠጣት ለምደዋል። እምቧ ከምትለዋ ላም ታንሳላችሁ? እስቲ የላሜ ቦራን ብልጠት በዝህች ፊልም ተመለክቱ!http://www.youtube.com/watch?v=E5DDT5qdHDE&feature=related
አበጀሽ ላሜ ቦራ! ጎበዝ ላሜ ቦራ! አንቺ እንኳን ከአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ተሽለሽ ተገኘሽ!
The Fake ‘Amharas’ – To milk “Lamie Bora – ላሜ ቦራ”
Recently, someone one visited Britain from home on business tour and entertained us with an amusing story of Lamie Bora, the fictional character in the children’s stoy. Woyyane officials call us, Diaspora Lamie Bora (ላሜ ቦራ)። Are we really that “milka-cow?”
I am sure everyone who went to school in Ethiopia at my age knows the children story of Lamie Bora. Lamie Bora is a very touching story. The story goes like this. A dying mother entrusts her two children unto a cow, called “Lamie Bora.” Just before she died, she sung to the cow: “Lamie Bora! Lamie Bora! I leave my children’s well being to you” (ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ! የልጆቼን ነገር አደራ). After a while the children’s father remarried another woman, who turned out to be a cruel stepmother. Every time she denied them food, the two children would go to Lamie Bora and sing “Lame bora! Lamie Bora! Don’t forget Mammie’s plea (ላሜ ቦራ! ላሜ ቦራ የእማምዬን አደራ!) Then Lamie bora would let the children suckle directly from the tits on her breast. Lamie Bora is supposed never to stop giving milk all year round.
This story is now retold among Woyyane agents referring to Diaspora as Lamie Bora, for the simple reason that whenever Woyyane runs out foreign currency it runs to the Diaspora – a cow full of milk all the year round. Every year, Woyyane officials fly to London, Washington and other major cities of the world, where exiled Ethiopians live in abundance with the hope of harvesting cash from the unsuspecting Diaspora – the cash cow. Their embassies have been instructed to implement the design for the purpose using various tactics. One such means is the Millennium Dum, (sorry I meant Dam), development associations, “Investors” and the recent 40/60 formula to own a house in Ethiopia! Recently, one of our church clergy renegades went for it, but fell out with the guys doing the business on some procedural grounds.
A good way of milking the milka-cow is to organise the Lamie Bora’s along their ethnic blood lines – such as the ‘Amhara’ Development Association, the Guragea Development Association, etc. This time, it is the ‘Amhara’ Lamie Bora’s turn to be milked in Queens capital city. The fake ‘Amhara’s (ቁጩ አማሮች)[1], are used as tools for the purpose. You rarely find any ‘Amhara’ among their leaders. Their organisation, The ‘Amhara’ National Democratic Movement (ANDM) was found in November 1980 in Tigray, at a place known as Tekrarwuha. The mission of ANDM – It’s all about shutting down the ‘Amhara’ threat. ANDM was the favoured puppet organization. They leadership was made up of various ethnic groups, but ‘Amhara’! They were then and are now actually predominantly Woyyanes disguised as Amaras. They are all fake-fake-fake to the root third rated ‘Amharas’. Take for Example, Bereket Simon. He is a Shabbo-banda whose mother and father hail from Eritrea. Hilawi Yosef is either a Tigre or a Shabo-Banda like Bereket, but has no drop of ‘Amhara’ blood in him. Tefera Walwa is a Gimira. Well at least Gimira sounds like ‘Amhara’. The only ‘Amhara’ thing in Addisu Legesse is his name. He is an Oromo from Harar. Did you know who Tamirat Layne was before he became Tamirat Layne? His real name was Getachew Mamo Waqkenie. Go and figure out that. Tadesse Tinqishu, regardless of his beautiful name, is a Tigre? Is Kassu Ilalla sound ‘Amhara’? Give me a break! All the ethnic based organisations, except the TPLF were formed using the same formula. Their extensions in the Diaspora are called “development associations” followed by the appropriate suffixes. The “associations” are kind of support groups for the “forged” ethnic groups.
Coming back to the Lamie Bora story, the fake ‘Amharas’ in London are organised under “‘Amhara’ Development Association – UK”. Do you want to see, who they are exactly, from their 2011 fund raising event? (Watch it here) Those of you who reside in London should be able to tell who is who in that video. The majority are Tigres, followed by Jamaicans and then some hod-aders like Yalew Kebede. Gondares have yet to tell us about the ethnic background of Yalew Kebede. Could he be another fake ‘Amhara’ like Bereket from Gondar?
This year, Lamie Bora – Diaspora is planned to be milked on 28 September 2013 at the Ethiopian Embassy. The entrance fee is free. Why not invite ourselves to the abundant food and drink? Oh, one more thing. Where are they advertising their event? Not of course mainstream websites, but Tigrai Online. This is yet another proof that this is another Woyyane organisation camouflaged as ‘Amhara’s! See for yourself. (click here to read)
The forged Amaras are disgusting who trade in the name of ‘Amhara’ to milk the Diaspora, to fill in the never quenching thirst of Woyyane for hard currency. It looks like its recent attempt to milk Lamie Bora did not work at fund raising events for the millennium dam, so they are punishing their Ambassadors for failing to trap Lamie Bora – the milka-cow. Many lost their jobs this week. May be the 40/60 formula for owning a house in Addis might attract some fools to sacrifice their hard earned currency. The idea is the Diaspora would pay 40% down payment in hard currency. The 60% would be lent in birr by the TPLF. Don’t you even think of owning the land on which the house is going to be built. It belongs to the TPLF. Whenever the TPLF wants the land, it will ask you to carry away your bricks and mortars as the land is needed by the landlord to be sold to foreign investors!
The Diaspora has to cease being treated like Lamie Bora. It has to distance itself from these corrupt and human rights abusers. Whenever one needs to do business with the TPLF, it is that person’s morale obligation to remember prisoners like Reyyot Alemu, Andualem Arage, Eskinder Nega, Nathnael Mekonen, Kinfemichael Debebe, Yohannes Terefe, Shambel Yeshewas Yehunealem and Andualem Ayalew, tens of thousands of members of the Oromo ethnic group and the illegally imprisoned Muslim leaders.
The Woyyane is a No. 1 corrupt regime in Africa. One would better avoid dealing with Woyyane at all levels unless that person wants to be milked dry. One can invest his/her money elsewhere, where a good return is expected without risk of being fleeced. The least, if you don’t want to invest, just drink your own milk rather than giving it to the Woyyane. Even some cows have become smarter and drinking their own milk rather than giving it away. Don’t you believe me? Watch the next cliphere
Good for you, cow! Well done! You are much better than some Ethiopians that are regularly milked dry by the Woyyane!
(Wondimu Mekonnen – London)
Leave a Reply