• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ቁልቁል የመንሸራተት አንድምታ!

February 21, 2016 09:01 pm by Editor Leave a Comment

በኢትዮጵያ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ማለት፤ የአገሪቱ የህግ ማስፈጸሚያ የመጨረሻው ችሎት ነው። ከዚህም በተጨማሪ፤ የአገሪቱ ፕሬዚዳንትም ሆነ ጠቅላይ ሚንስትር እንዲሁም የፓርላማ አባላት ስራቸውን ከመጀመራቸው በፊት፤ ቃለ መሃላ የሚያስፈጽመው የዚህ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት መሆናቸው ይታወቃል። የህገ መንግስት ወይም የህግ ትርጉም የሚሰጠው የመጨረሻ አካል ነው – ጠቅላይ ፍርድ ቤት። ከዚህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች በላይ ደግሞ፤ ፕሬዚዳንታቸው አለ። እስከቅርብ ግዜ ድረስ ፕሬዚዳንቱ አቶ ተገኔ ጌታነህ ነበር። እናም በቅርቡ “የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ፤ ስልጣኑን በገዛ ፍቃዱ ለቀቀ” ሲባል፤ እንደማንኛውም ዜና ሰምተን ዝም የምንለው ሊሆን አይገባም።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ወይም ቃልአቀባዮች መግለጫ ባለመስጠታቸው የተፈጠረ ክፍተት አለ። ይህን ክፍተት በመጠቀም እኛም የራሳችንን መላ ምት እንሰጣለን። ከዚያ በፊት ግን ስለዳኛ ተገኔ የየራሱን ትንሽ ትንሽ ማለቱ አይቀርም። እኔ ከትንሽም ባነሰ መልኩ… በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት – የቀኝ ዳኛ በነበረበት ወቅት ነው፤ ከጥቂት በታች በጥቂቱም ቢሆን ሰብዕናውን ለማወቅ የቻልኩት።

በፐሬስ ክስ ጉዳይ ስከሰስ… ለመጀመሪያ ግዜ የቀረብኩት፤ ዳኛ ተገኔ ጌታነህ ቀኝ ረዳት በነበረበት 1ኛ ችሎት ነበር። ከሁሉም የከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ 1ኛ ችሎት ትንሽ ቀለል ያለ ነበር። ለንፅፅር እንዲረዳን ከጎኑ ወዳለው 2ኛ ችሎት ልውሰዳቹህ።

2ኛ ችሎት ውስጥ የግራ እና ቀኝ ዳኞች ቢኖሩም፤ ጎልቶ የሚታወቀው – ሃጎስ ወልዱ የሚባለው ከሰይጣን ቁራጭ የተሰራ የሚመስለው ቀይ ሰውዬ ነው። በተለይ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች ካጋጠመው፤ በቁጣ እና በስድብ ያንቀረቅባቸዋል። እነፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ እነዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት፣ ታምራት ላይኔ እና በሌሎች ታዋቂ ሰዎች ላይ ምንም ቅም ሳይለው ስድብ አቅምሶ፤ ፍርዱን በፖለቲካ ጭቃ ለውሶ ፈርዶባቸዋል።

በደርግ ዘመን የአዲስ አበባ ከተማ ዳኛ የነበረው ግለሰብ፤ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ … በአንድ ግዜ ተስፈንጥሮ የፌዴራሉ ፍ/ቤት መሃል ዳኛ እስከመሆን የደረሰው፤ በችሎታ ሳይሆን በፖለቲካ ሹመት በመሆኑ አብረው የሚሰሩት ጭምር ይፈሩታል። ችሎቱ በታጠቁ ፖሊሶች የሚጠበቅ ቢሆንም፤ ዳኛ ሃጎስ ወልዱ ግን የራሱን ሽጉጥ ታጥቆ ነበር – ችሎት የሚሰየመው። በዚያ ላይ ስድብ እና ጩኸቱ አይጣል ነው። ከድሮ ጋዜጠኞች መካከል አበራ ወጊ፣ አክሊሉ ታደሰ፣ ተፈራ አስማረ፣ ዘገየ ሃይሌ፣ እስክንድር ነጋ እና ሲሳይ አጌና ላይ ያለ ምንም ግርግር እስር እንደፈረደባቸው አስታውሳለሁ።

በ2ኛ ችሎት ከታዩት ክሶቹ መካከል አበራ ወጊ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ጦርነት ሊጀመር መሆኑን በመዘገቡ፣ አክሊሉ በሰሜን ሸዋ ስለነበረው ወታደራዊ እንቅቃሴ በመጻፉ፣ እክንድር የኤርትራውን ፕሬዚዳንት በካርቱን እባብ አስመስሎ በመሳሉ “የፕሬዘዳንቱን ክብር ነክተሃል” ተብሎ … ብቻ በትንሽ እና በትንሹ ሰበብ ሁሉ ዳኛ ሃጎስ ወልዱ የስርአቱ ‘አፋሽ አጎንባሽ’ ሆኖ ንጹሃንን በእስር ቀጥቷል። እናም የ2ኛ ችሎቱን ሃጎስ ወልዱ የሚያውቅ ሰው… እሱ ፊት አለመቅረቡ በራሱ ደስ ያሰኘዋል።

በመጨረሻም በዚህች ቀልድ መሰል የፍርድ ቤት ገጠመኝ ሁለተኛ ችሎትን እንሰናበት። አንድ ተከሳሽ በችሎት ቆሞ ዳኛው ሃሳቡን እንዲረዱለት በተደጋጋሚ “ክቡር ፍርድ ቤት! ክቡር ፍርድ ቤት!” እያለ አቤቱታውን ያሰማል።

በዚህ የተናደደው ዳኛ ሃጎስ ወልዱ፤ “አስሬ ክቡር ፍርድ ቤት! ክቡር ፍርድ ቤት አትበል።” ይለዋል።

ተከሳሽ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ “ክቡርነትዎ … ክቡር ዳኛ!” ብሎ ይጀምራል። በዚህ ግዜ ዳኛ ሃጎስ ወልዱ ተናዶ፤ “አንተ ሰውዬ ተወኝ!” ሲለው ተከሳሹ ደንግጦ፤ “ወይ እግዚአብሄር?!” ይላል። በመጨረሻ ዳኛ ሃጎስ በንዴት፤ “ይሄ ፍርድ ቤት እንጂ ቤተክርስቲያን አይደለም። እግዚአብሄር እዚህ የለም!” ብሎት አረፈ – እየተባለ፤ በቀልድ እየተዋዛ ብዙ ግዜ ይነገር ነበር።

የኔም የመጀመሪያ ክስ ሃጎስ ወልዱ ጋር ባለመሆኑ፤ ‘እንኳን ደስ ያለህ’ ያሉኝ ጋዜጠኞች አልታጡም። በነገራችን ላይ የሃጎስ ወልዱን ቤት ሰዎች አቃጥለውበታል። (የተናደዱበት ሰዎች እንዳደረጉት ይወራል)። ይህ ግን ለተሻለ ደረጃ አሳጨውና ወደ ጠቅላይ ፍርድ ተዛወረ። ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ብዙ አልቆየም፤ እዚያ ካሉት ሰዎች ጋር አብሮ መስራት አልቻለም። በመሆኑም ሁሉንም ዳኞች ከማባረር እሱን በጡረታ አሰናበቱት። ከአገር ከወጣሁ በኋላ ይህ ሰው መሞቱን ሰምቼ፤ ‘በቃ ያ ሁሉ ነገር፤ ለዚሁ ነው?’ ብዬ ያልኩበት አጋጣሚም ነበር። “ሙት ወቃሽ” እንዳንባል፤ ሃጎስን 2ኛ ችሎት ትተን ወደ አንደኛ ችሎት እንመለሳለን። ከዚያ በፊት ግን ዳኛ ሃጎስ ወልዱ ችሎት ያጋጠመ አንድ ቀልድ፤

1ኛ ችሎት ውስጥ በቀኝ በኩል የሚታደመው፤ ዳኛ ተገኔ ጌታነህ ምን አይነት የፖለቲካ አቋም እንዳለው ባላውቅም፤ ችሎት ላይ ግን ረጋ ያለ ሰው ይመስላል። ቢያንስ ሲቆጣ ወይም ሲሳደብ አይቼው አላውቅም። እርግጥ ነው። በስንት ንጹሃን ሰዎች ላይ ያለ አግባብ እንደፈረደ ወይም ስንት ንጹሃንን ነጻ እንዳወጣ ላናውቅ እንችላለን። ሆኖም በጋዜጠኞች ላይ ጠንከር ያለ ፍርድ ሲጠየቅባቸው፤ “ይሄማ ፕሬሱን ማሸማቀቅ ነው” ብሎ በችሎት ውስጥ የተናገረ ሰው ነው። የዛሬ 15 አመት ሌሎች ችሎቶች (በዚያን ዘመን ገንዘብ) ሃያ እና ሰላሳ ሺህ ብር ሲያስከፍሉን፤ 1ኛ ችሎት ግን የ500 ወይም አንድ ሺህ ብር ዋስትና ከፍለን እንድንወጣ ያደርግ ነበር። እናም በሃሳብ አንደኛ ችሎት ውስጥ ስንታደም፤ የክስ መዝገቡ ላይ ማስታወሻ መጻፍ የሚያዘወትረው፣ ቀኝ ዳኛ ተገኔ ጌታነህ በሃሳባችን ውልብ ማለቱ አይቀርም።

እኔ ለመጀመሪያ ግዜ 1ኛ ችሎት ስቀርብ፤ እልህና ጉርምስናው ተቀላቅሎ ፍርድ ቤቱን በመድፈር ሊያስቀጣኝ የሚችል ድርጊት ፈጽሜ፤ በተግሳጽ የታለፍኩት እነ ተገኔ ጌታነህ ፊት ስለቀረብኩ ይመስለኛል። በወቅቱ የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ሆኜ ሳለ፤ “የተከሰስኩበት የፕሬስጉዳይ ወንጀል ስላልሆነ፤ የክስ ወረቀቱን አልቀበልም” በማለት ከተላላኪው ጋር ስከራከር፤ የተከሳሽ ሳጥን ጋር ወርወር ሲያደርግልኝ፤ የክስ ወረቀቷ ተንሸራትታ መሬት ትወድቃለች።

የክሱ ወረቀት የወደቀው በክርክር መሃል ስለነበር፤ ወረቀቱን እኔ የወረወርኩት ነበር የሚመስለው። ይዞኝ ከቀረበው ፌዴራል ፖሊስ ጀምሮ እስከ መሃል ዳኛው ድረስ፤ በድንገት ሁሉም ነገር ጸጥ አሉ። (ከዚህ በኋላ የሆነውን መዘርዘር የወጋችንን ደረጃ ዝቅ ስለሚያደገው እንለፈው) ይህን ግድፈት የፈጸምኩት ዳኛ ሃጎስ ወልዱ በሚገኝበት 2ኛ ችሎት ውስጥ ቢሆን ኖሮ፤ እንኳንስ በተግሳጽ ልታለፍ ቀርቶ “ሳንጃ ባፈሙዝ” ገብቶ አሳሬን ልቆጥር እችል ነበር።

ከአገሬ ከወጣሁ በኋላ፤ የቀኙ ዳኛ ተገኔ ጌታነህም የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እንደተቀላቀለ ሰማን። ብዙም ሳይቆይ የጠቅላዩ ፕሬዚዳንት ሆነ። በስልጣን ዘመኑ ሟቹን ጠ/ሚንስትር መለስ ዜናዊ እና የአሁኑን ጠ/ሚንስትር ስልጣን ሲረከቡ፤ ቃለ መሃላ አስፈጽሟቸዋል። በዚህ ላይ እያለን ነው እንግዲህ … ፕሬዚዳንት ተገኔ ጌታነህ -የአገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቀ … የሚለውን ዜና የሰማነው።

የሰው ልጅ ከፊቱ ልዩ ልዩ ፈተናዎች ሲያጋጥሙት፤ ለራሱ መላ መምታቱ የሚከፋ አይደለም። አሁንም ዳኛ ተገኔ ጌታነህ ስልጣኑን ሲለቅ፤ “ለምን?” ብለን የመጠየቅ ሰብአዊ የማወቅ ጉጉት ያድርብናል።

በመግቢያችን ላይ እንደገለጽነው … የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን የፕሬዚዳንትነት መንበራቸውን ሲለቁ የተሰጠ መግለጫ ስለሌለ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ የራሳችንን መላምት ልናቀርብ እንችላለን።

የመላምታችን መነሻ የሚሆነው አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ነው። ህዝቡ ከላይ ጀምሮ እስከታች ድረስ እንደሸረሪት ድር በተተበተበ የሸፍጥ እና የጉልበተኞች አገዛዝ ስር ወድቋል። እንዲህ አይነቱ አገዛዝ፤ ህግ እና ደንብ ለሱ እስከጠቀሙት ድረስ ብቻ ነው የሚገለገልባቸው። ከዚያም አልፎ የዜጎችን ነጻነት ለማፈን፤ በህግ ሽፋን አደናቃፊ ጉድጓዶች ይቆፍራል። ህግ አውጪውም ሆነ አስፈጻሚው አንድ የፖለቲካ አካል በመሆኑ፤ ያሻውን ይፈጽማል ያስፈጽማል። እንዲህ አይነቱ አካሄድ ሁሉንም ዜጋ እኩል ሊያስደስተው ስለማይችል፤ በተለይ ለህሊናቸው ተገዢ የሆኑ ሰዎች ስርአቱን በመክዳት ሰላማዊ ኑሯቸውን ይመርጣሉ።

አሁን በኢትዮጵያ ያለው መንግስት አፋኝ ስርአት በመሆኑ፤ የህዝብ አጋር የሆኑ… ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ እና ሃይማኖት መሪዎች ቁጥር ጠላቶቹ ናቸው። እነዚህ ሁሉ “አሸባሪ” ተብለው እድሜ ልካቸውን በእስር ቤት ቢማቅቁ፣ ቤተሰባቸው ቢበተን፤ የሚበሉትና የሚይርጡት ቢያጡ የስርአቱ አዳማቂዎች ደንታቸው አይደለም። ህሊና ያላቸው ሰዎች ግን ይህንን ተሸክመው ለመሄድ አቅም ያንሳቸዋል። እናም አንድ በአንድ ይህን ስርአት ይከዱታል።

እንደነጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ድረስ፤ የታሰሩት በ’ርግጥም በአሸባሪነት መሆኑን ለማሳመን፤ ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ እስከፓርላማ አባላት – ከዚያም ታቹን ለግልገል ካድሬዎች ጭምር የውሸት ታሪክ ይነገራቸዋል። እነሱም ውሸት መሆኑን እያወቁ ‘በክርስቶስ ነኝ’ ከሚለው ጠቅላይ ሚንስትር ጀምሮ ሌሎች ሚንስትሮች የተሳተፉበት የቅጥፈት ዘመቻ ሲያከናውኑ ይሰነብታሉ። ይህን ለሚያስፈጽሙላቸው የደህንነት፣ የፖሊስ እና የአቃቤ ህግ ሰዎች ገንዘብ በቁና ይሰፍሩላቸዋል። ህዝቡን ሰጥ ለጥ ለማድረግ እንዲቻል እንደ ፌዴራል ፖሊስ አይነት፤ ህሊና ቢስ ሰዎችን ያሰማራሉ።

ፌዴራሎችም በጭካኔ ለመደብደብ እና ለመግደል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ሆነው፤ በደም ጥማት ይክለፈለፋሉ። ጭካኔያቸውን ለማሳየት እንደቀልድ ተደርጎ የሚወራ ነገር አለ። የአድማ በታኝ ሃላፊው ፌዴራሎቹን ይሰበስብና በቅርቡ የሚነሱትን አመጾች በእሳት አደጋ ውሃ ጭምር ለመበተን ዝግጅቱ አልቋል። ስለዚህ ጥይት ከማባከን ይልቅ በውሃ እንበትናቸዋለን። እያለ ካብራራ በኋላ፤ የፌዴራል ፖሊሶቹ ጥያቄ ካላቸው እንዲጠይቁ ይፈቅድላቸዋል። በዚህ ግዜ አንዱ ፌዴራል ፖሊስ ብድግ ብሎ እንዲህ አለ።

“ሃሳቡ ጥሩ ነው። ውሃው ግን የፈላ ቢሆን የተሻለ ውጤት እናገኛለን።” ሲል ሌሎች የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሃሳቡን በጭብጨባ ደግፈው ሲያበቁ፤ “የፈላ ውሃ ከሌለ አሲድ ብንጨምርበትስ?” እያሉ ሃሳቡን አዳበሩት እየተባለ ይቀለዳል። እንግዲህ ስርአቱ በዚህ አይነት ጨካኝ ሰዎች የተገነባ ነው። የስርአቱ ደጋፊዎች የተባሉትን የሚያደርጉ፣ የተሰጣቸውን የሚያነቡ ለመሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም። የፌዴራል ፖሊሶች ብቻ ሳይሆኑ፤ የፌዴራሉ አቃቤ ህጎችና ዳኞች ጭምር አይናቸውን በጨው ታጥበው፤ ንጹሃን ሰዎች ላይ ፍርድ ሲሰጡ ይስተዋላል።

ለምሳሌ የአንድነት ፓርቲ አመራር የነበረው ሃብታሙ አያሌው፤ በሃሰት የአሸባሪነት ክስ ተመስርቶበት፣ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት “አሸባሪ” ተብሎ፤ እስር ተፈርዶበት ከቆየ በኋላ፤ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “ይግባኝ” ብሎ ነጻ ወጥቷል። ሌሎችም የነሃብታሙን ፈለግ ተከትለው “ይግባኝ” በማለት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነጻ ሊያወጣቸው ይችል ይሆናል። ይህ አካሄድ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እና ጠቅላይ ሚንስትሩን እንደሚያቃቅር ግልጽ ነው። ጫናው እየበዛባቸው ሲሄድ የባለስልጣናቱ ምርጫ፤ አንድም ማጎብደድ ወይም ስርአቱን መክዳት ሊህን ይችላል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት “በገዛ ፈቃድ የመልቀቅ ውሳኔ” የመነጨው፤ አንድም አጎብዳጅነትን መሸከም የማይችል ትከሻ ባለመኖሩ መሆኑ ግልጽ ነው።

እዚህ ላይ ሌላም ምሳሌ ጠቅሰን እንለፍ። በቅርቡ የአድማ በታኝ ሃላፊ የሆነውን የየማነ መንጁስን ነገር እንመልከት። የማነ መንጁስ የህወሃት አገልጋይ በመሆን፤ ብዙዎች እንዲታሰሩ እንዲደበደቡ ብሎም እንዲገደሉ ያደረገ ሰው ነው። ሰሞኑን በተደረገው ኢህአዲጋዊ ግምገማ ግን፤ ግለሰቡ ግዴታውን በብቃት እንዳልተወጣ ይነገረዋል። እንደማስረጃም አሁን በኦሮሚያ ያለውን አመጽ መቆጣጠር አለመቻሉ ሲነገረው፤ ሰውየው እራሱን መቆጣጠር ተስኖት … የራሱን ህይወት ለማጥፋት ሽጉጥ ጠጥቶ፤ በሞት እና በሞት መሃል ሆኖ ሆስፒታል መሄዱን ሰምተናል። ይሄ ሁሉ እንግዲህ ስርአቱ በሰዎች ላይ የሚፈጥረው ጫና ውጤት መሆኑ ነው።

ለማጠቃለል ያህል … እንደ ዳኛ ተገኔ ጌታነህ በእውነት እና በቅጥፈት መካከል ሆነው፤ ምርጫቸው መኖር ወይም አለመኖር፤ ቅንጦት ወይም እጦት ሆኖ ህይወታቸውን የሚገፉ ብዙ ናቸው። ለሙያቸው እና ለህግ ልዕልና ሲሉ ለሃቅ የሚሞቱ እንዳሉ ሁሉ፤ በአሳዛኝመልኩ ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ ፍርድ የሚያዛቡ፤ የእለት እንጀራቸው ደም ደም የሚላቸው ብዙዎች ይኖራሉ። ፈላጭ ቆራጭ ስርአት እስካለ ድረስ የሁለቱ ወገኖች ሽኩቻ መቼም አያቆምም። እንደ’ውነቱ ከሆነ… አሁን በኢትዮጵያ ባለው እውነታ፤ የህግ ፍርድ ሰጪ አካል መሆን ማለት፤ በእሳት ላይ እንደተጣደ ገበር-ምጣድ ነው። ከላይም ከታችም እሳት ይነድበታል።

ወደፊት የአንዳርጋቸው ጽጌን የሞት ፍርድ የሚያጸና ብርቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ያስፈልጋል። ይህ ብቻ አይደለም። በኦሮሚያ ውስጥ የተለኮሰው፤ የዘረኝነት እሳት ከመጥፋቱ በፊት ጥፋተኛ የተባሉትን ግለሰቦች ወደ ፍርድ ቤት በማምጣት በህግ ሽፋን የሞት ቅጣት ሊሰጣቸው ይችላል። አወዛጋቢ የሆነው የኦሮሚያ እና የአዲስ አበባ ጉዳይ፤ የህገ መንግስት ትንታኔ ሲያስፈልገው፤ ከፌዴሬሽን ምክር ቤቱ ቀጥሎ … መፍትሄ ሰጪው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነው።

ህሊና ላለው ሰው … ይሄን ሁሉ የሚንቀለቀል እሳት ተሸክሞ መሄድ ይከብደዋል። ሌላም እንጨምርበት። አሁን በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚታዩ ትላልቅ ጉዳዮች ወደፊት በይግባኝ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲመጡ፤ ከመጨረሻው የፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ የመጨረሻውን ፍርድ መስጠት ይከብዳል። ለምሳሌ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ መሪዎች እና የሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ሰዎች አሸባሪ ተብለው ተከሰዋል። ይህ ክስ እውነት እንዳልሆነ፤ የታችኛውም ሆነ የላይኛው ፍርድ ቤት ሁሉም ያውቀዋል። ለዚህ አይነቱ የፖለቲካ ክስ፤ፍትሃዊ ውሳኔ መስጠት ሁሌም አስቸጋሪ ይሆናል። ያለምንም ማወላወል አይንን ጨፍኖ “አዎ ጥፋተኛ ነህ” ብሎ ተሳድቦ፤ “ወስደህ እሰረው!” ለማለት እንደ-ዳኛ ሃጎስ አይነት፤ እዝነ- ህሊና ያልፈጠረበት አይነት ሰው መሆን የግድ ነው።

በሚገርም ሁኔታ ለህሊናቸው ተገዢ የሆኑ ሰዎች፤ ስርአቱን በዚህ መልኩ ሲሰናበቱ፤ ህሊናቸውን ለፍርፋሪ የሸጡ ሰዎች ደግሞ ለአዲስ ሹመት የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ ደጅ ሊጠኑ ይችላሉ። እነሱም ለጠቅላይ ሚንስትርነት ከመሰየማቸው በፊት ለኢህአዴግ የሰጡት አገልግሎች ግምት ውስጥ ገብቶ ይመረመራል። በዚህ አይነት በሙያ ሳይሆን የፖለቲካ አቋምህ እየታየ ዳኛ ትሆናለህ። የዚህ አይነት የፖለቲካ ሹመኞች በበዙ ቁጥር፤ ቁልቁል እየወረደ ያለው ፍትህ፤ ልጓሙ እንደተበጠሰ መንኮራኩር እታች ወርዶ እንክትክቱ ይወጣል። አሁን የዳኛ ተገኔ ጌታነህን ከስራ መልቀቅ ለግል ህሊናው ተስማሚ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ የሚሾመው ግለሰብ ፍትህን ሳይሆን፤ ስርአቱን ለማገልገል ከቆመ፤ ለኢትዮጵያ ዘላቂ የፍትህ ተቋም መገንባት አይቻልም። “ለሁሉም ግዜ አለው” እንደሚባለው፤ መጪውን ጊዜ አብረን የምናየው ይሆናል። እስከዚያው ግን የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ፕሬዚዳንት ውሳኔ ከማድነቅ ውጭ ለመውቀስም ሆነ ለማሞገስ ጊዜው ገና ይመስላል።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule