• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወድያ

January 15, 2018 03:49 am by Editor Leave a Comment

ሰሞኑን አየሩን የሞላው “የበላይነት” የሚለውን ጽንሰሃሳብ በመለጠጥና በማጥበብ ዙርያ ሆኗል። የህወሃት የበላይነት፣ የትግራይ የበላይነት፣ የትግራይ ህዝብ የበላይነት በሚሉ ብዙም በማይራራቁ ጽንሰ ሃሳቦች ዙርያ ከዝንብ መላላጫ የማውጣት ያህል ከየአቅጣጫው እየተሰነዘሩ ነው። እነዚህ እሰጥ አገባዎች አብዛኛውን ጊዜ ስሜታዊነትና ጥላቻም ተቀላቀሎባቸው  ሶሻል ሚድያውን፣ የርስ በርስ ውይይቱንና መገናኛ አውታሮችን ያጣበቡ ሲሆን በጣም ጥቂቶች በአጋጣሚው የጠለቀ ትንተና በመስጠት በነገሮች ላይ ያለንን እይታ እንዳሰፉት እሙን ነው። ወያኔም ህብረተሰቡ በዚህ ስሜታዊ እንካስላንትያ ሲጠመድ ሊያገኝ የሚችለውን እፎይታና የተቃውሞው ጎራ መከፋፈል ሊያተርፍበት ሲንደፋደፍ ይታያል።

ለእኔ ደግሞ “የበላይነት” አለ፣  የለም የሚለው ጉንጭ አልፋ ውይይት ላይ ጊዜና ጉልበታችን ሲጠፋ አግባብ ሆኖ አይታየኝም። የነኢህአፓና መኢሶን “እናቸንፋለን” ና “እናሸንፋለን” ተራና መናኛ ቃላት ብዙ ሺህ የአገሪቷን ዜጎች እንዳጋደለና የትግሉን አቅጣጫ እንዳሳተ አይተናል።

ዛሬም የቃላት አዙሪት ውስጥ ሳንገባ በኢትዮጵያ ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍክፍል አለመኖሩን፣ ህዝቡ የስልጣኑ ባለቤት እንዳልሆነ፣ የህግ የበላይነት እንደሌለና አገሪቱ ህልውናዋ አዳጋ ላይ መውደቁን ከተስማማንበት፤ ለዚህ ሁሉ ዳፋ ተጠያቂ የሆነው ዘረኛና ዘራፊ የህወሃት ቡድን መሆኑን አምነን ስርዓቱን ለመጣል ጊዜ፣ ጉልበትና ሃብታችንን  በዚያ ላይ ማዋል እንጂ “የበላይነት” ቲዎሪ ስንሰነጥቅ የምንውልበት ፋይዳ የለውም። አባቶች “ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ” ያሉት ይህንን ዓይነቱን ዓላማውን የሳተ ድርጊት ነው።

ወያኔ ጉልህ በሆነ ሁኔታ ፊታችን ላይ ቆሟል። ቅዝምዝሙን ከወያኔ አሻግረን አርቀን አንወርውረው። ወያኔ ሲጠፋ የበላይነቱ ይጠፋል። ጉልበታችንንና ጊዜያችንን ወያኔን ትተን ጥላውን ስናባርር መዋል አዋቂ አያደርገንም።

አንተነህ መርዕድ

amerid2000@gmail.com


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions Tagged With: eprdf, Left Column, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule