ታህሳስ 19 ቀን በቅዱስ ገብርኤል ስም የሚታሰበው በዓል፤ እግዚአብሔር ሥነ ባህርይን (ሞራልን) እንዲያከብር ቅዱስ ገብርኤልን የላከበት ቀን ነው።
ማሳሰቢያ፦ በቅዱስ ገብርኤል ስም በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን ከፍተው ህዝብን በመዝረፍ ላይ የሚገኙት ብዙዎቹ “ቅዱስ ገብርኤል ተከበረ እንጅ አከበረ ” የሚለውን ሰምተውት ስለማያውቁ፤ “ቅዱስ ገብርኤል አይከበር አለ ” እያሉ፤ አንብበው ከእውነቱ
መድረስ የማይችሉትን አንዳንድ የዋሆችን ውዥንብር ውስጥ መክተታቸው አይቀርም።
እኔ ኢትዮጵያን በመምራት ያሉ ፖለቲከኞችና በየስርቻው ቤተ ክርስቲያን የሚከፍቱትን የአስመሳይ ነጋዴዎች ባህርይ፤ አባቶች ስለበዓሉ አላማና ምክንያት ካስተማሩኝ ጋራ ሳንጻጽረው፤ ቅዱስ ገብርኤል ካከበረበት ምክንያትና ዓላማ ጋራ ምንም ግንኙነት
እንደሌለው ገለጽኩ እንጅ ቅዱስ ገብርኤልማ ክብር ይገባዋል ።
መግቢያ:ታሕሳስ 19 አስርቱ ቃላት የተጻበት ጽላት ከመንበሩ የሚንቀሳቀሰው ቅዱስ ገብርኤል ያከበረውን ሥነ ባህርይ (ሞራል) በቅርብና በሩቅ ላለ ሁሉ ለማንጸባረቅ ነው። ይሁን እንጅ ይህን ማስተጋባት የሚጠበቅባቸው መንፈሳውያን መሪዎችም ሆኑ ዓለማውያን መሪዎች በዚያ ወቅት በአገርና በወገን የፈጸሙት በደልና ግፍ፤ ለተከበረው በዓል ተቃራኒ ነበር። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply