በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሕዝብ ትግልና እንቅስቃሴ ሲካሄድ ቆይቷል። ከተካሄዱት ትግሎች ውስጥ የአገርን ነጻነት በማስከበሩ ከውጭ ወራሪ ሃይሎች
ጋር የተደረገ የነጻነት ትግል የሚያኮራ ውጤት ሲያመጣ በውስጥ አስተዳደር ዙሪያም ለዘመናት ተንሰራፍቶ የነበረውን ባላባታዊ ስርዓት ለመለወጥ የተደረገ ትግል ሙሉ ለሙሉም ባይሆን መለስተኛ ድሎችን አስመዝግቦ አልፏል። ከአርባ ዓመት በፊት በተፈጠረለት አጋጣሚ ለአስራ ሰባት ዓመት በስልጣን ላይ በቆየው፣ በአምባገነኑ የደርግ
የገዳዮች ስርዓት ላይ ያነጣጠረ ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ ለውጥ የተደረገው ህብረብሔራዊ እንቅስቃሴ ከሽፎ በውጭ ሃይሎች የታገዘ አገር አፍራሽ የሆነ ሃይማኖትንና ጎሳን (ብሔርን) ያማከለ ታጣቂ የጎሳ ስብስብ ስልጣኑን ቀምቶ እስከአሁን
ለመቆየት ችሏል። ምንም እንኳን ሕብረብሔሩ ትግል በገጠመው ውስጣዊና ውጫዊ ችግር በመዳከሙ የስልጣን ዘንጉን የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ከጥቂት አጃቢ ጎሰኛ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ቢወስድም፣ በፈለገው መንገድ አገሪቱን ለማስተዳደር
አልቻለም። ከመጀመሪያው እለት ጀምሮ ሕዝቡ እምቢባይነቱን በልዩ ልዩ መልክ ሲገልጽ ቆይቷል። አሁንም እየገለጸ ነው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply